የክልሉ መንግስት ምላሽ ቢጠየቅም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ትላንት አምስተኛ ቀኑ አልፏል በትግራይ ክልል የሕንጣሎ ወረዳ ነዋሪዎች በአዲሱ የአስተዳደር መዋቅር ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን ተቃውመዋል። “በአቅራቢያችን መተዳደር እንፈልጋለን” በማለትም ከመቀሌ ከተማ ወደሳምረ በሚወስደው ደንጎላት በሚባል አካባቢ መንገድ ዘግተው የክልሉ መንግስትን ምላሽ በመጠባበቅ አራተኛ ቀናቸውን ደፍነዋል። ለመንገዱ መዘጋት ምክንያቱ የ“ወረዳችን ይመለስልን” ጥያቄ በማቅረብ ከህብረተሰቡ በተወከሉ ነዋሪዎች አማካኝነት ላለፉት ስድስት ወራት ያክል ወደክልል አስተዳደር ተመላልሰው ቢጠይቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ምክንያት የተነሳ መሆኑን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪ አቶ መሀሪ ገብረ፤ “ህብረተሰቡ ሌላ ሃሳብ የለውም፣ ዓላማው ወደክልሉ ቢሮ … [Read more...] about አምስተኛ ቀኑን ያሳለፈው የሕንጣሎ ወረዳ ተቃውሞ ቀጥሏል