በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ "Bicycle" ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ "Bicycle" ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር። አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ … [Read more...] about የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
hailemariam
ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ኢ.ቢ.ሲ. በሰበር ያስተናግደውን የኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ፤ ዞምቢዎቹ ተሯሩጠው ለማጽደቅ ግዜ አልወሰደባቸውም። እሳቸውም ልክ ስልጣን እንደነበረው ጠቅላይ ሚኒስትር "ስልጣን አስረክቢያለሁ" ሲሉ እፍረት የሚባል ነገር ፊታቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር። ሹመት እንጂ ሕገ-መንግስቱ የሚፈቅደው ስልጣን እጃቸው ላይ እንዳልነበር ሕጻናትም ያውቁታል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መልቀቅያቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲያጸድቀው፤ ድርጊትዋን ከደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዙማ ክስተት ጋር ለማመሳሰል የተተወነች ድራማም አስመስሏታል። ስልጣን ሳይኖር “ሰላማዊ ሽግግር” የሚሏት ፌዝ … ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሸክመውት የነበረው ሹመት ይሁን ስልጣን ሲለቅቁ፤ "ከደሙ ነጻ ነኝ" ብለው ለተሰራው ወንጀል ሁሉ እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ሊታጠቡ እንደማይችሉ ግን እርግጥ ነው። ከዚህ ባለፈ ግን የእሳቸው መውረድ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ ለምን ለቀቁ?
ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?
ከወራት በፊት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባውን አባዱላ ገመዳ የኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚ ጥያቄውን አጽድቆለታል ተብሏል። ከዚህ ጋር ተከትሎ በቀጣይ ኃይለማርያም ከ“ሥልጣን” ይወርዳል የሚለው ጉዳይ በስፋት በሁሉም ዓይነት ሚዲያ እየተስተጋባ ነው። በተያያዘ ወሬ አዲስ አበባ ላይ ያለውና ሰሞኑን በመጠኑ ሥራውን መሥራት የጀመረውን “ፓርላማ” ህወሓት ሊበትነው እያቀደ ነው የሚል መረጃ ተሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪም ከትግራይና ሌሎች ታማኝ ክልል/ሎች በስተቀር በክልል የሚገኙ ምክርቤቶችን በሙሉ ህወሓት ሊበትናቸው አሢሯል የሚል መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እየተሰማ ነው። ከገቢ አንጻር የሰበር ዜና ልክፍት የተጠናወተው ሚዲያ ይህ መሰሉን “መረጃ” ሲያስተላልፍ ከመረጃው ጋር ሕዝብ ማወቅ ያለበት ምንድነው የሚለውን ኃላፊነት የዘነጋው ይመስላል። ኃይለማርያም ደሳለኝ በሟቹ መለስ ተመልምሎ ወደ … [Read more...] about ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?
ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ? የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውም ጊዜ ለህገመንግስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል። ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዝቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል። ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ … [Read more...] about ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል
የኦሮሚያን ክልል በውክልና የሚያስተዳድረው ኦህዴድ አቶ መለስ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የቆየው የድርጅቱ “የመስመር” ችግር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በተፈጠረ ስጋት የኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ ተወርዋሪ ሃይል እንደ ቀድሞው እንደማይታመን ተጠቆመ። ሲቪል ሆነው በብርጋዴር ጀኔራልነት ስውር ማዕረግ የኦሮሚያን ፖሊስ ሲመሩ የነበሩት አቶ ደምመላሽ ገብረሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ የማዕከላዊ መረጃና የወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነርነት ቢዛወሩም አሻራቸው ኦሮሚያ ፖሊስ ውስጥ እንዳለ የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች፤ ክልሉ በፌዴራል ፖሊስ ደረጃ ያዋቀረው ተወርዋሪ ሃይል እየተደረገበት ያለው ክትትል ጥርጣሬው ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። አቶ ደምመላሽ አሁን በፌዴራል ደረጃ ያላቸው ኃላፊነት ቀድሞ በኦሮሚያ ከነበራቸው ሥልጣን ጋር ተዳምሮ የተወርዋሪው ልዩ … [Read more...] about የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል
ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ?
አገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አስር የሚሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አስተዳድረዋታል፡፡ ከእነዚህ መካከል በተለየ ሁኔታ ከሚወሱት አንዱ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው፡፡ በጣልያን ወረራ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ በአውሮጳ ያደረጉት ተጋድሎ እጅግ ከፍተኛ ለመሆኑ በተለያዩ ቦታዎች ሲጠቀስ የሚሰማ ነው፡፡ አርበኞቻችን በአገር ውስጥ የሕይወት መስዋዕትነት ሲከፍሉ አክሊሉ ሃብተወልድ በአውሮጳ የከፈሉት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያን ለማዳን የሠሩት ሥራ ተጽፎ የማያልቅ ታሪካቸው ነው፡፡ ያላንዳች ማጋነን የዲፕሎማሲውን ሥራ ያለመታከት ከግብ ያደረሱት አክሊሉ ነበሩ፡፡ በተለይ “የአክሊሉ ማስታወሻ” በተባለው የራሳቸው ታሪክ በከፊል የተወሳበት መጽሐፍ ላይ የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆር እና የፈረንሣዩ ጠ/ሚ/ር ላቫል ከኢትዮጵያ ክፍላተሃገራት አብዛኛው የሆነው ሐረር፣ ሲዳሞና ባሌን ጨምሮ … [Read more...] about ኃይለማርያም ደሳለኝ – እንደ ዳንኤል፤ እንደ አክሊሉ ወይስ እንደ መለስ?