በተከታታይ በቲውተር ገጹ መረጃ የሚያሰራጨው የአሸባሪው ትህነግ አባል ጌታቸው ረዳ ትግራይን እንደማይመራ ክርክር ተነስቷል። የራያ ልጅ የሆነውና ፍጹም የአማራ ደም ያለው ባንዳው ጌታቸው ቀደም ሲል በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ወቅት በረኸኞቹን ትህነጎች “ህግ የማያውቁ፣ ደደቦች፤ ምንም የማይገባቸው፤ መሃይም ደናቁርት” እያለ ክፍል ውስጥ ሲያንኳስስ እንደ ነበር የሚናገሩት ተማሪዎቹ የትህነግ አባል መሆኑ ይፋ ከሆነ ማግስት ጀምሮ ግን ለትህነግ አጎብዳጅና ተገዢ እየሆነ መምጣቱን እነዚሁ ተማሪዎችና በቅርብ የሚውቁት ይመሰክራሉ። “እዳ በዝቶበት መክፈል ሲያቅተው የትህነግ አባል ሆኖ ማገልገል ጀመረ፤ ለፕሮጀክት የተሰጠውን ገንዘብ ሙልጭ አድርጎ በላው፤ ወሰበበት፣ ጠጣበት፤ ትህነጎችም በስልት አበሰበሱት” ሲሉ ጌታቸውን በቅርብ የሚውቁት ይናገራሉ። በቀጣይም “ዕዳ ስረዛ ተደርጎለት … [Read more...] about “አማራው ጌታቸው ረዳ ትግራይን አይመራም” በረኸኞቹ ትህነጎች
getachew
ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”