በጋምቤላ ክልል የኦነግ አባላት ናችሁ በሚል እና ህወሀትን ትረዳላችሁ በሚል የታሰሩ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ። ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል የእስረኞች አያያዝ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ሊሻሻል እንደሚገባም አሳስቧል። ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በጋምቤላ ክልል ያለው የእስረኞች አያያዝ እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ በታኅሣሥ ወር በጋምቤላ ከተማ እና በአኝዋህ ዞን በመገኘት፣ በአካባቢው ስላለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ክትትል አድርጎ ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን ገልጿል። ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የክልሉ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች አያያዝና ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው። በተለይም በኦነግ … [Read more...] about በጋምቤላ ህወሃትንና ኦነግ ሸኔን ትረዳላችሁ ተብለው የታሰሩ እንዲፈቱ ተጠየቀ
Gambella
በጋምቤላ በ10 ሺህዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ተፈናቅለዋል
ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ውስጥ በጎርፍ መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ። የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የተከሰተበት ወረዳው ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስን አካባቢ ነው። የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ ቤት ከተፈናቃዮች መካከል ወ/ሮ ኛዳክ ፓችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ ምክናያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከነቤተሰቦቻቸው በትምህርት ቤት አጥር ጊቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። መንግሥት የአልባሳትና የምግብ አቅርቦት ባለማድረጉም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ወ/ሮ ኛዳክ ተናግረዋል። በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊች ቢየል በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ሱዳንንና ኢትዮጵያን የሚያዋስነው ጂካዎ ወንዝ ሞልቶ በተፈጠረው ችግር ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ የሚኖሩትም … [Read more...] about በጋምቤላ በ10 ሺህዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ተፈናቅለዋል
ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ
ተጠናቀቀ በተባለው የጋምቤላ ክልል ግምገማ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ለመሾም የገንዘብ ኃይል ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረገ መሆኑ ተሰማ። ግምገማውን እንዲመሩ የተመደቡት ግለሰቦች የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ምደባ በተመለከተ ከሌሎች ጋር በመሆን በገንዘብ ኃይል የሚፈልጉትን ለመሾም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው እየተነገረ ነው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ማለታቸውን ጠቅሶ በክልሉ የተንሰራፋውን ግፍና ሙስና (ሌብነት) በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ ካወጣ በኋላ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ለመሾም በታቀደው ድብቅ አጀንዳ ላይ ችግር መፈጠሩ ተሰምቷል። ለአሥር ቀናት የተካሄደውን ግምገማ የመሩትን በተመለከተ ጎልጉል ዘገባውን ሲያቀርብ “ግምገማውን እንዲመሩ ከፌዴራል መንግሥት የተወከሉት ፈቃዱ ተሰማ እና ተፈራ … [Read more...] about ገንዘብና ሥውር እጆች ተዋናይ የሆኑበት የጋምቤላ የርዕሰ መስተዳድር ምደባ
“ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ዑመድ ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን “የቀድሞ ደጃዝማቾች ካባቸውን አውልቀው ለሚፈልጉት በመስጠት እንደሚሾሙት ጋትሉዋክም ለዘመዱ የስልጣኑን ካባ ያጎናጸፈበት ቀልድ ነው” ሲሉ አውግዘውታል፤ ይልቁኑም ጋትሉዋክ ቱት በበርካታ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ ስለሆነ ሌሎቹንም አመራሮች ጨምሮ ሁሉም “ለፍርድ መቅረብ … [Read more...] about “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
“እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”
እነዚህም የህወሓት ነፍሰበላዎች ይፈለጋሉ! የሰላም ሰዎች የሆኑት አኙዋኮች ከህወሓት ጋር መቃቃር ውስጥ የገቡት ገና ከጅምሩ ነበር። የቀድሞው የአኙዋክ ምክርቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ኦባንግ ሜቶ እንደሚሉት ችግሩ የተያያዘው ህወሓት የጋምቤላን ለም ምድር የራሱ ለማድረግ ከመፈለጉ ጋር ነው። ህወሓት ሥልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ የጋምቤላን ብቸኛ ጄኔሬተር በመንቀል ከመውሰድ አልፎ በአሎሮ ግድብ ላይ የነበሩትን ወደ 400 የሚሆኑ ማሽነሪዎች እና የእርሻ መሣሪዎች በምሽት ወደ ትግራይ ነቅሎ ወስዷል ይላሉ አቶ ኦባንግ። በመቀጠልም ተዝቆ የማያልቀውን የጋምቤላን ድንቅ ሃብት በረኸኞቹ ህወሃቶች ለመዝረፍ ውሳኔያቸው አደረጉ። “መሬቴን አላስነካም” በሚለው አኙዋክና ህወሓት መካከል ያለውን መቃቃር አንድ “ዕልባት” ላይ ለማድረስ በሚል አኙዋክን ማጥፋት የህወሓት ቀዳሚ ሃሳብ ሆነ እንደ አቶ … [Read more...] about “እንጨርሳቸው፤ አንድም አኙዋክ መትረፍ የለበትም”