“ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እንዲያስፈራ ተደርጎ ተሰርቷል” በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሐምሌ 26/2011ዓም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋዜጠኛ ምህረት ሞገስ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። “ድንቁርና እና ድህነት እሳት ነው፤ አገር ያቃጥላል” በሚል ርዕስ የወጣውን ቃለምልልስ ከዚህ በታች አስፍረነዋል። በዚህ ጥያቄና መልስ አቶ ኦባንግ ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መልሶችን ሰጥተዋል፤ ጎሰኝነትን፣ ብሔረተኝነትን፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ወዘተ በመሳሰሉ ርዕሶች ላይ ሊነበብ የሚገባው መልሶችንና ዕምነታቸውን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን፡– የካናዳ የትምህርት ህይወት እንዴት … [Read more...] about “ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
Ethiopia
“የቻይና ጅብ” ክፍል ፪፡ በብድር ያነክሳል! በዕዳ ጫና ይነክሳል! በወታደር ይጨርሳል!
ቻይናዎች “አንድ ሀገር መበልፀግ ከፈለገ መንገድ መገንባት አለበት” የሚል አባባል አላቸው። በዚህ መሰረት ሀገሪቱ በየብስና ባህር ላይ “የሀር መንገድ” (Silk Road & Silk Maritime) ለመገንባት አንድ (1) ትሪሊዮን ዶላር በጀት መድባለች። ይህ የሀር መስመር በሚያልፍባቸው 68 ሀገራት ውስጥ 900 የሚሆኑ ትላልቅ የአስፋልት መንገዶች፣ የባቡር መስመሮች፣ የአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የባህር ወደቦች፣ የመብራት ማመንጫ ግድቦችና ማሰራጫዎች፣ የጋዝ (ነዳጅ) ማስተላለፊያ ትቦዎች ለመገንባት ወይም ለመዘርጋት የተመደበ ከፍተኛ በጀት ነው። ይህ አንድ ትሪሊዮን ዶላር የሚገኘው ከቻይና ልማት ባንክ (China Development Bank CDB), ከቻይና ኢምፖርት-ኤክስፖርት ባንክ (China Ex-Im Bank)፣ ከኢሲያ መሰረተ-ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ (Asia … [Read more...] about “የቻይና ጅብ” ክፍል ፪፡ በብድር ያነክሳል! በዕዳ ጫና ይነክሳል! በወታደር ይጨርሳል!
“የቻይና ጅብ”- ክፍል ፩: አሜሪካና ቻይና ጅቡቲ ውስጥ ምን እየሰሩ ነው?
1. የአሜሪካ ሃያልነት ከጃፓን እስከ ቻይና ላለፉት አንድ መቶ አመታት አሜሪካ የዓለም ልዕለ-ሃያል ሀገር መሆኗ እርግጥ ነው። የአሜሪካ ሃያልነት ግን ያለ ተቀናቃኝ በብቸኝነት የዘለቀ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በየግዜው ከሚመጡ ተቀናቃኝ ሀገራትና ቡድኖች ጋር ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጦርነት ውስጥ ገብታለች። ስለዚህ የአሜሪካ ሃያልነት እነዚህን ጦርነቶች በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ላይ የተመሰረተ ነው። ባለፉት መቶ አመታት ከአሜሪካን ጋር የሃያልነት ትንቅንቅ ውስጥ ከገቡት ሃይሎች መካከል የመጀመሪያው ከ1930ዎቹ ጀምሮ ከጃፓን ጋር የተደረገው ነው። በዘመኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደው ትንቅንቅ በመጨረሻ ጃፓንን ለኒኩለር ቦንብ ዳርጓታል። ይህን ተከትሎ ደግሞ አሜሪካ ከሶቬት ህብረት ሩሲያ ጋር የሃያልነት ትንቅንቅ ውስጥ ገባች። የሶቬት ህብረት ተቀናቃኝነት እ.አ.አ. በ1989 ዓ.ም … [Read more...] about “የቻይና ጅብ”- ክፍል ፩: አሜሪካና ቻይና ጅቡቲ ውስጥ ምን እየሰሩ ነው?
ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!
አፍቃሪ ህወሓት የሚዲያ ተቋማት የማኅበራዊ ድረገጽ ተዋናዮቹን ጨምሮ “ቀለበት ውስጥ ገብተናል” በማለት የተጀመረውን ለውጥና ከኤርትራ ጋር የተያዘውን አስደማሚ የሰላም ሂደት ሲቃወሙ ሰንበተዋል። አሁንም ምክንያት በመለጣጠፍ እየተቃወሙ ነው። ድርጅታቸው ህወሓት የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አራት ኪሎ ላይ ከወሰነ በኋላ ትግራይ ገብቶ ውሳኔውን የማያውቀው እስኪመስል ድረስ እየሸራረፈ ሲቃወም ሰንብቷል። በመጨረሻ ባወጣው መግለጫ የሰላም ድርድሩ ግልጽነት የጎደለውን መሆኑንን ለምክንያትነት ካወሳ በኋላ በዋናነት በድንበር ላይ ያለው የመከላከያ ኃይል እንደማይነሳ አቋሙን አስታውቋል። መከላከያ ሠራዊት የአገር ሃብትና ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥት ነው። ታማኝነቱ ደግሞ ለሕዝብና ለሕገመንግሥቱ ሲሆን ዋና አዛዡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው። በዚህ እውነትና … [Read more...] about ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!
“ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን
በባድመ ጉዳይ የሰሞኑ የህወሓትና የደጋፊዎቹ የማደናገሪያ ጉንጭ አልፋ ሙግት ብዙዎችን ያሰገረመ ከመሆኑ አልፎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን በፓርላማ በሚያስጠይቅ መልኩ የቀረበ ትዕይንት ሆኖ አልፏል። ራሱ ህወሓት በቆሰቆሰው እሣት የኢትዮጵያን ሕዝብ በ“ድንበር ተደፈረ” ማጭበርበሪያ ካስማገደ እና የፈንጂ ማምከኛ ካደረገ በኋላ አልጀርስ ላይ የአሸባሪና ወንበዴው ህወሓት መሪ በነበረው መለስ ዜናዊ አማካኝነት ባድመን ለኤርትራ አስረክቧል። ከዚያም አልፎ በሌላው ወንበዴ ስዩም መስፍን የኢትዮጵያን ሕዝብ በመዋሸትና ባድመ የእኛ ሆነች ብሎ በይፋ በመናገር አገር የመክዳት ወንጀል ፈጽሟል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያኔ መለስ እንደፈለገ ይነዳው በነበረው ፓርላማ አማካኝነት ህግ አርቅቆ በነጋሪት ጋዜጣ አስወጥቶ ባድመን ለኤርትራ አስረክቧል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ባድመን አስረክቡ ሲባሉ የህወሓት አሸባሪ … [Read more...] about “ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን
የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?
በሙስና ወንጀል በሚል በርካታ የሳዑዲ ባለሃብቶችን ዘብጥያ የጣሉት የዙፋን ተስፈኛው የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን በሳዑዲ ሚዲያ ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል። በአንዳንዶች ግምት በቤተመንግሥት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ይባላል። አልጋወራሹ በህይወት ከሌሉ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ አላሙዲንን “አስፈትተው” የመጡት ማንን አነጋግረው ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የሳዑዲ መንግሥት አልጋወራሹ በሥራቸው ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን፤ ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት … [Read more...] about የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?
ነፃ ያልወጣች ሠንደቅ
አዎ፤ አውሮፓዊው ቅኝ ገዢ ጣሊያን አድዋ ላይ ድል ሆኗል በ1888 ዓ/ም። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በሚወክለው ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋ ላይ ግን ከትውልድ የዘለለ ቂም ቋጥሮ የደማ ልቡን በመዳፉ ደግፎ በተቆረጠው ቋንጃው እያነከሰ አንድ እግሩን ኤርትራ ላይ ልብና ሌላ እግሩን ጣሊያን - አውሮፓ ላይ አድርጎና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍራንቺስኮ ክሪስፒን ከሥልጣን አባርሮ ድፍን ጣሊያን ሀዘን ተቀመጠ። አርባ ዓመት ሲታመምና ሲያገግም ኖረ። ጣሊያን በኢትዮጵያና በሠንደቋ ላይ ለአርባ ዓመት ያረገዘው ቂም ዱቼንና ፋሽስት ፓርቲን ወለደ። ለጣሊያን ትንሳዔ ኢትዮጵያ መሥዋዕት መሆን አለባት ሲል እነሆ ዱቼ በሮም አደባባይ ተጣራ። ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነት ለተዋረደችው ጣሊያን ትንሳኤ አቀረበ። አውሮፓ አጨበጨበ፤ ቪቫ ዱቼ ሲል ደገፈ። ጥቁር ለባሽ የፋሽስት ጦር ከጣሊያን ጫፍ እስከ ጫፍ … [Read more...] about ነፃ ያልወጣች ሠንደቅ
ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተስፋን-በጥንቃቄ (cautious optimism) ካነገቡት ሰዎች አንዱ ነኝ። የተስፋዬ መሠረቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ፣ የገቧቸው ቃልኪዳኖች እና አሁን የታየው መረጋጋት ናቸው። አሁን የታየው መረጋጋት ስል የቄሮዎች የአደባባይ ተቃውሞ መቆሙን ማለቴ አይደለም። ተቃዋሚዎችን እያሳደዱ መከታተል፣ ማዋከብ እና ማሰር ርቀን ሳንሔድ አምና ከነበረው አንፃር እንኳ ልዩነቱ የትየለሌ ነው። ለዚህ የራሴን ስሜት እና ተሞክሮ ነው በምሳሌነት የማቀርበው። በፊትም አሁንም ሐሳቤን በነጻነት እገልጻለሁ። ነገር ግን አምና እና ካቻምና ከያንዳንዱ ጽሑፎቼ/ንግግሮቼ ቀጥሎ እስር ይመጣል እያልኩ እየሰጋሁ ነበር የማደርገው። አሁን ምን ያክል ይዘልቃል የሚለው ቢያሰጋኝም እታሰራለሁ እያልኩ በየደቂቃው አልባትትም። በፊት ሲያስሩ፣ ሲያዋክቡ እና ሲከስሱ ከነበሩት … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከራሳቸው ማዳን!
የዶ/ር ዓቢይን “መጨረሻ ለማየት ቢያንስ ስድስት ወራት እንጠብቅ”
ዶር. ዓቢይና አቶ ለማ መገርሳ በኢትዮጵያ መድረክ ላይ መታየት ሲጀምሩ ኢትዮጵያ የተአምር አገር መሆንዋን አስታወስሁና እግዚአብሔር ፊቱን ወደኢትዮጵያ መመለሱን ተረዳሁ፤ ከዚያም በላይ ያለፈው ጠቅላይ ሚኒስትር እናቱን በመውቀስና በመመጻደቅ ጀመረ፤ አዲሱ ደግሞ እናቱን በማወደስ መጀመሩ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነት በአደባባይ ደጋግሞ በመግለጹ አከበርሁት፤ አከብረዋለሁ። ከዚህ በፊት ሦስት ጊዜ በፌስቡክ የጻፍሁትን ልድገመው፤ አንድ፤ በ1965 በወሎ ችጋር ዘመን በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች እርዳታ ለማድረግ በምንሯሯጥበት ጊዜ አንዳንድ የኢሕአፓ አባሎች ለተራቡት እርዳታ መሰብሰብ አብዮቱ እንዳይመጣ ማድረግ ነው እያሉ ይቃወሙን ነበር፤ ነፍሱን ይማረውና አብርሃም ደሞዝና እኔ ተቆጥተንና አስፈራርተን አደብ እንዲገዙ አድርገናቸው ነበር፤ ዛሬ ደግሞ … [Read more...] about የዶ/ር ዓቢይን “መጨረሻ ለማየት ቢያንስ ስድስት ወራት እንጠብቅ”
አብይ አህመድ፤ ለክፉ ቀን የታሰበ የኦሮሞ ወጣቶች ብሶት ማስታገሻ?
የዶ/ር አብይ መሾም “ይህንን ክፉ ቀን የኦሮሞ ወጣቶችን አስታግሶ ለማለፍ” ይሆን? የዶ/ር መረራ ጥያቄ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ቃለምልልስ የሰጡት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በአዲሱ ጠ/ሚ/ር ሹመትና የወደፊት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካሄድ ከኢህአዴግ ድርጅታዊ አሠራር አንጻር ትንታኔ ሰጥተዋል። “ኢህአዴግ ለምን ተዘጋጅቷል?” የሚሉት መረራ ቀለል ያሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ያስከትላሉ፤ “ለነጻና ፍትሃዊ ምርጫ፤ ለሃቀኛ የፖለቲካ ውድድር (ኢህአዴግ) ተዘጋጅቷል ወይ?” በማለት ይጠይቃሉ። ራሳቸው ሲመልሱትም “ይህንን ካሁኑ ለመገመት ያስቸግራል” ይላሉ። የጠ/ሚ/ሩ ተስፋ የተሞላበትን ንግግሮች ሁሉ መልካም መሆናቸውን ቢገልጹም እርሳቸው እንደ ዜጋ እና ድርጅታቸውም እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ የአብይ አህመድን ንግግሮችና የወደፊቱን ሁኔታ “ጥንቃቄ የተሞላበት … [Read more...] about አብይ አህመድ፤ ለክፉ ቀን የታሰበ የኦሮሞ ወጣቶች ብሶት ማስታገሻ?