ከየአቅጣጫው ከተለያዩ ምንጮች ገንዘብ እንደሚለገሰውና የውክልና ፕሮፓጋንዳ እንደሚሠራ ይፋ የተደረገበት ኢትዮ 360 ሚዲያ ይህንኑ ለማስተባበል የገንዘብ ችግር አንቆናል፤ ዋናው ችግሬ ብር ነው እርዱኝ ሲል ባወጣው መግለጫ የልመና ድምጹን አሰማ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በውስጥ በተከሰተ መከፋፈል ምክንያት የተለያዩ ምሥጢሮች እየወጡበት የተቸገረው ኢትዮ 360 አሁን ካለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ራሱን መገምገሙን በመግለጫው ጠቁሟል። ቅዳሜ ዕለት መግለጫው እንደወጣ በዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ (በተለምዶ ዲኤምቪ በሚባለው) የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያነጋገረችው የጎልጉል መረጃ አቀባይ እንዳለችው መግለጫው ሌላ ገንዘብ የመሰብሰቢያ ስልት ነው በማት አስተያየት ሰጪዎች መናገራቸውን ገልጻለች። “ሁሉንም እኮ እናውቃቸዋለን፤ ኮትና ከረባት አሳምረው ሲታዩ … [Read more...] about ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ
Ethio 360
እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!
አምስተርዳም (በቪቫ ምኒልክ) ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በኢትዮ 360 በሰሞኑ የኢትዮጵያን መከላከያና ደህንነት ክፍል አስመልክቶ የቀረበው ውይይት እጅግ ስለ አስደነገጠኝ ነው። ከውይይት ጭብጥ እንደተረዳሁትም ከመከላከያና የደህንነት መስሪያቤት ከፍተኛ አመራሮች በደረሰን መረጃ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አገራችንን ለአረቦች አሳልፎ በመስጠት የእስልምና ሐገራት አባል ለማድረግ እየሰራ ነው የሚልና የምእራብ እዝን ወደ ወለጋ ያዛወረው የኦሮሞን ልዩ ሃይል ለማደራጀት እንዲመቸው ነዉ የሚል በጥላቻ ላይ ብቻ የተመሰረተው ክሳችሁን መሉ ለሙሉ የምቃውምበትን ነጥብ ከዚህ በታች በአጭሩ ዘርዝር አድርጌ ለማስተላለፍ እሞክራለሁ። የውይይት ሃሳባችሁ መነሻ ያደረጋችሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሰይፉ ጋር ያደረጉት ዉይይት ላይ ስለ አረብ አገራት ለኢትዮጵያ በሚሰጡት የገንዘብ … [Read more...] about እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!