ከወራት በፊት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባውን አባዱላ ገመዳ የኢህአዴግ ሥራአስፈጻሚ ጥያቄውን አጽድቆለታል ተብሏል። ከዚህ ጋር ተከትሎ በቀጣይ ኃይለማርያም ከ“ሥልጣን” ይወርዳል የሚለው ጉዳይ በስፋት በሁሉም ዓይነት ሚዲያ እየተስተጋባ ነው። በተያያዘ ወሬ አዲስ አበባ ላይ ያለውና ሰሞኑን በመጠኑ ሥራውን መሥራት የጀመረውን “ፓርላማ” ህወሓት ሊበትነው እያቀደ ነው የሚል መረጃ ተሰምቷል። ከዚህ በተጨማሪም ከትግራይና ሌሎች ታማኝ ክልል/ሎች በስተቀር በክልል የሚገኙ ምክርቤቶችን በሙሉ ህወሓት ሊበትናቸው አሢሯል የሚል መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እየተሰማ ነው። ከገቢ አንጻር የሰበር ዜና ልክፍት የተጠናወተው ሚዲያ ይህ መሰሉን “መረጃ” ሲያስተላልፍ ከመረጃው ጋር ሕዝብ ማወቅ ያለበት ምንድነው የሚለውን ኃላፊነት የዘነጋው ይመስላል። ኃይለማርያም ደሳለኝ በሟቹ መለስ ተመልምሎ ወደ … [Read more...] about ኃይለማርያም ከየት ይለቃል? ያልነበረ “ፓርላማ” ወዴት ይበተናል?