ለበርካታ ጋዜጠኞች ከሥራ መፈናቀል፤ ከአገር መሰደድ ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ የነበረው ዘርዓይ አስገዶም ከሥልጣኑ ተነስቷል። አንደበቱ በቅጡ ያልተገራና ፍጹም የህወሓትን ዓላማ በአደባባይ በማስፈጸም የሚታወቀው ዘርዓይ፤ ከዚህ እንደፈለገ ከሚነዳው መ/ቤት መልቀቁ በሚዲያው ማኅበረሰብ ዘንድ እንደ ታላቅ አዎንታዊ እርምጃ ተወስዷል። አንዳንድ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በላይ በቀለ፣ መሠረት አታላይ፣ ዮናስ ዲባባ፣ አስካለ በላይ፣ ካሳሁን ፈይሳ፣ እና ሌሎችም የሙያው ሰዎች በዚሁ የህወሓት ተጋዳላይ ትዕዛዝ ከሥራቸው እንዲለቁ መገደዳቸው ይታወቃል። ዘርዓይ በሥልጣን በቆየባቸው ዓመታት ሦስት ብቻ በአማርኛ የሚታተሙ ጋዜጦች የነበሩ ሲሆን በክልላዊ ነጻነት የሚንቀሳቀሱትን የአማራ ሚዲያና የኦሮሚያ … [Read more...] about የሚዲያው “እንቦጭ” ዘርዓይ አስገዶም ተነቀለ