አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለምርጫ ያነሳሁትን ፎቶ ወስዶ የተጠቀመበትን መንገድ እንዲያስተካክል የተቻለውን ጥረት አድርጎ የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን በተመለከተ ተቋሙን ለመክሰስ እገደዳለሁ ሲል የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አማኑኤል ስለሺ አስታወቀ። ጋዜጠኛ አማኑኤል በጉዳዩ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረው፤ አምንስቲ ኢንትርናሽናልን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ነው። "በስልክና በኢ-ሜይል ለማግኝት ጥረት እያረግን ቢሆንም እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጡንም። አሁን 22 ሰዓታት አልፎታል። በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ይህንን የተቀናበረ ምስል ተቀባብለውታል። ለራሳቸው ዓላማ የሚያውሉት እንኳን ቢሆን መቀየር የተከለከለ ነው" ሲል ተናግሯል። አምነስቲ ለመረጃው የተጠቀመውን ፎቶ ግራፍ በተመለከተ በውይይት ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ … [Read more...] about የፎቶ ሌብነትና የአምነስቲ ቅሌት
amnesty
ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ
በኔዘርላንድ በሚደረግ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ለመገኘት ተጋብዞ የነበረው እስክንድር ነጋ ሐሙስ ሌሊት ለአርብ ጠዋት ቦሌ ላይ ከአገር እንዳወጣ ታግቷል። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት ጉዳዩ ህወሓትን ትልቅ ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት ይህ ፈጽሞ መከሰት ያልነበረበት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚ/ር አብይ በጉዳዩ ላይ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል። ሌላው ለጉዳዩ ቅርበት ያለውና ክስተቱ እንደተፈጸመ አጭር ዘገባ ያሰራጨው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ “ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም” ብሏል። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከቦሌ አካባቢ ባገኘው መረጃ መሠረት እስክንድርን … [Read more...] about ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ