አሁንም ይፈለጋል!

የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው – ኦሞት ኦባንግ !!

ኦሞት የዛሬ 14ዓመት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኙዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑን ከአገራችን የቀበሌ ነዋሪ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ በማስረጃ የሚታወቅ ነው። ኦሞት በጋምቤላ ለፈሰሰው የንጹሃን ደም “ነጻ” ሊሆን የሚችልበት አንድም አግባብ የለም።

ኦሞት ኦባንግ ኦሉም አሁንም ይፈለጋል!

የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤት!

Speak Your Mind

*