አገርን ከጥፋት ህዝብን ከፍጅት ለማዳን ዛሬውኑ በጋራ እንነሳ

በአገራችን ውሰጥ የሰፈነው ከፋፋይ ሥርዓት እነሆ ህዝባችንን እርስ በርስ የሚያጋጭና የአገሪቱንም አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የጣለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ሕዝባችን በየዕለቱ ከአንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ ይገኛል። የቀውሱ አድማስም በአንድ ቦታ የተወሰነ ሳይሆን በየጊዜው እየሰፋ ትላንት ሰላም ነው ይባል የነበረን ቦታ ዛሬ የቀውስ ማዕከል እያደረገው ሁሉንም የኅብረተሰባችንን ክፍል፣ ሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪ እየነካ ይገኛል። በቀላል አነጋገር አገሪቱ ከዳር አስከ ዳር በቀውስ አየተናጠች መሆኗ በገሃድ አየታየ ነው።

ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ላለፉት 26 ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን አመቃ፣ ምዝበራና ንቅዘት በመቃወም የተነሳው ህዝባዊ አንቅስቃሴ በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን፣ ይህን ተቃውሞ ተከትሎ የተከሰተው የሥርዓቱ ውስጣዊ መፈራረስ ያስከተለው መዘዝ መሆኑን መታዘብ ይቻላል። የዚህ ሁሉ ውጤት ደግሞ፣ ሁላችንንም ሊያሳስብ የሚገባ ነገር፣ የሥርዓቱ መፍረስ በህዝባችን ደህንነትና በአገራችን ህልውና ላይ የሚድቅነው አደጋ ነው።

በሀገራችን ውስጥ የሚታዩት ችግሮች ዘርፈ-ብዙና ውስብስ ቢሆኑም በዋናነት ሥርዓቱ ከሚያራምደው ህዝብን እርስ በርስ በጠላትነት እንዲተያይ ከሚያበረታታው፣ የጋራ እሴቶችን ማጉላትና ማጠናከር ሳይሆን ሆን ብሎ በሚያዳክመው፣ ዴሞክራሲያዊነት የሌለው የሀገሪቱን ችግሮች በሸፍጥና በጉልበት ለመፍታት ከሚጥረው አምባገነን አሸባሪ ሥርዓት ፖሊሲና ተግባር ጋር የተዛመደ ነው።

ኢትዮጵያ ዛሬ በአራቱም ማዕዘናት ህዝብ ለዘመናት ከኖረበት ቀየው የሚፈናቀልባት፣ ዜጎች “ይህ ድንበር የኔ ነው ያ ደግሞ ያንተ አይደለም” እየተባሉ እንደውጭ ዜጋ ከሚገለሉበትና ከሚባረሩበት፣ በሀገራቸው ጉዳይ ያላቸውን አመለካከት በነፃነት የማይገልጡበት፣ የሥርዓቱ ባለሥልጣኖችና ታማኞቻቸው ደግሞ በማንኛውም ኢትዮጵያዊና በንብረቱ ላይ እንደፈለጉ የሚያዙበት፣ ህዝብም ከግፉ መብዛት፣ ከዋስትናና ፍትህ ማጣት የተነሳ በራሱ አገር ውስጥ በሞትና በሕይወት መኖር መሀል ያለው ትርጉም የጠፋበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል።

(ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Speak Your Mind

*