ጎሳን ለይቶ የሚደረግ ጥቃትን ለማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ያሻል

የሸንጎ መግለጫ

አንድ መንግስት ልማታዊ ሊባል የሚችለው የሚመራውን ሕዝብ ከዃላ ቀርነትና ከድህነት ኣሮንቓ መንጥቆ ሲያወጣ፣ የህዝቡን ኣንድነትና መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር፣ የኣገርን ብሔራዊ ጥቅምና ዳር ድንበር ሲያስከብር ነው።

ሕዝብ በኑሮ ክብደት የሚሰቃይበትና የበይ ተመልካች በሆነበት፣ ወጣቱ ተስፋ ቆርጦ ለስደት ሲዳረግና እግረመንገዱን ለተለያዩ ኣደጋዎች የሚጋለጥበት፣ የጎሳ ስሜት ነግሶ ኣንዱ ሌላውን እንዲጠላና ሰላም እንዲናጋ፣ ዜጋ ለዘመናት ከኖረበት ቦታና መሬት በሃይል እየተፈናቀለ እንዲበታተን የሚያደርግ ስርዓት ያሰፈነ ቡድን የሚመራው መንግስት ጥፋታዊ እንጂ ልማታዊ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም።

የሕዝቡን መብት ገፎ፣ የአገሩን ሃብትና ንብረት፣ ለም መሬት ጭምር ለባእዳን አሳልፎ እየሰጠ፣ እየሸጠና ተባብሮ እየመዘበረ በውጭ አገር ባንክ የሚያካብት ቡድን ስልጣን ላይ ባለበት አገር ውስጥ ልማታዊ መንግስት ኣለ ብሎ ማመን ቀርቶ መናገሩ የስህተት ስህተት ነው። (ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Speak Your Mind

*