መፍትሄው በብሄራዊ መግባባት የሽግግር ሂደትን እውን ማድረግ እንጂ ለ27 ዓመት የተደረገውን መድገም አይደለም

ህወሓት-መራሹ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 17 ቀናት የወሰደ ስብሰባውን እንዳጠናቀቀ በማመልከት መግለጫ አውጥቷል። ስብሰባው ከመጠናቀቁ በፊት ትልቅና አዲስ ነገር አመላካች የሆነ ውሳኔ እንደሚያሰተላልፍ በተለያየ መልክ ሲጠቁም ቢከርምም፣ የመጨረሻው መግለጫ እንደሚያመለክተው ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካለፉት ጊዜያት የተለየ ተስፋ ሰጭ ነገር ይዞ አልመጣም።

ይህ ደግሞ ሀገራችን ባለችበት ሁኔታና ሕዝባችን ለመብቱ መከበር እያሳየ ከሚገኘው ቆራጥነት አንፃር ሲታይ ገዥው ህወሓት-መራሹ ኢህአዴግ አሁንም ለሕዝባችን ብሶት፣ ለሀገር ደህንነትና ለአካባቢውም መረጋጋት ደንታ እንደሌለው፤ ከዚያም አልፎ ሥልጣኑን ይዞ ለመቆየት ደግሞ አፈናውን፣ ረገጣውን፣ ከፋፋይነቱን ባጠቃላይም ከፍተኛ ወንጀልን ከመፈጸም እንደማይመለስ አመላክቷል።

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Speak Your Mind

*