ኢትዮጵያን እንቀኝ

ርዕዮት ሚድያ እሁድ January 28, 2018 የኢንተርኔት ስርጭቱን የጀመረበትን አንደኛ ዓመት ክብረ-በዓል “ኢትዮጵያን እንቀኝ” በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት እንደሚያከብር ሲገልጽ ደስታ ይሰማዋል፡፡ ዝግጅቱ በእለቱ ከ4 PM ጀምሮ 7701 16th Street, NW Washington, DC 20012 በሚገኘው Tifereth Israel አዳራሽ በርካታ ታዳሚዎችና የክብር እንግዶች በተገኙበት ይመደረካል፡፡

ርዕዮት ሚድያ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትን የመኖር ምክንያትና ዋና መርህ ያደረገ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቱ ማናቸውንም ጉዳዮች በልዩ ልዩ የአቀራረብ ስልቶች የሚዳስስ ሚድያ ነው፡፡ ግባችንም ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ መሻል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የዜና፣ የትንተናና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን አሰናድቶ በበርካታ መንገዶች ኢትዮጵያውያን ዘንድ በያሉበት መድረስና የኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ጉልህ ድምጽ መሆን ነው፡፡ በቀደመው አመት፣ አሰናድተን በምናቀርባቸውና በቀጥታ በምናሰራጫቸው ዝግጅቶች አማካይነት በአለም ዙርያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ጠንካራ ትስስርና ተደራሽነት ፈጥረናል፡፡ በእለቱም ከ500 በላይ ታዳሚዎች ይህንን ኢትዮጵያን እንቀኝ የተሰኘ ልዩ ዝግጅት ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓሉን ራስ ባንድና ድንቅ ድምጻውያን ሀገራችንን በሚያከብሩ ውብ
ስራዎቻቸው ያደምቁታል፡፡ ኢትዮጵያን የሚያወሱ በታላላቅ ብዕረኞች የተጻፉ ግጥሞች፣ ተረኮችና ተውኔት፣ ኢትዮጵያዊ ሀገራዊ ማንነትን የተመለከቱ የምሁራን ትንተናዎች፣ ምጥንና አጫጭር ውይይቶችና ሌሎች አይነተ ብዙ መሰናድኦዎች ይቀርባሉ፡፡

በመሆኑም፣ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በስፍራው በአካል በመገኘት በአሉን አብራችሁን እንድታከብሩ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል፡፡

ኑ ኢትዮጵያን እንቀኝ፡፡

ኢትዮጵያ ምንጊዜም በክብር ትኑር፡፡

ርዕዮት ሚድያ (reyotmedia@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።


For Immediate Release

Reyot Media is proud to announce it will be celebrating its first-year anniversary on Sunday January 28th, 2018, starting at 4:00 pm at the Tifereth Israel Synagogue located at 7701 16th Street, NW Washington, DC 20012.

Reyot Media is a vibrant community media enterprise that expounds on everything Ethiopian across multiple platforms and formats available to audiences around the world.

Our mission is to reach out to all Ethiopians wherever they are, with the news and entertainment content that resonates with them.

We have developed a strong footprint and reach across the Ethiopian community through the contents and programs we produce that are broadcast live on Saturdays and Sundays.

The event is scheduled to attract up to 500 to attend the festivities in person and will be livestreamed across multiple online platforms to reach several thousand people across the globe.

We invite you all to help us celebrate our first anniversary.  There will be distinguished guests, plays, poetry readings,testimonials, presentations, live music with Ras Band and celebrated singers.

Reyot Media, LLC, 8209 Fenton Street, STE 8, Silver Spring MD, 20910

reyotmedia@gmail.com

202.415.8418


Notice: Reports, rebuttals, analyses, press releases and/or recommendations offered by the author/s or organization/s do not necessarily reflect that of Goolgule: Amharic Internet Newspaper’s stand.

Speak Your Mind

*