በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ንብረታቸዉ ወድሟል የተባሉ የትግራይ ሰዎች ካሳ ሊከፈላቸዉ ነዉ

በ2008ዓ.ም. መገባደጃ ወራት ላይ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የኮሚቴ አባላትን የህወሃት/ኢህአዴግ ኃይሎች በጎንደር ከተማ ለማፈን ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ የህይወትና የንብረት ዉድመት መድረሱ ይታወሳል። በወቅቱ “ንብረታቸው ወድሟል” የተባለላቸው የትግራይ ተወላጆች የካሣ ክፍ ሊፈጸምላቸው መሆኑ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ “የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ንብረት እየተለየ ጥቃት ደርሶበታል” በሚል በህወሃት/ኢህአዴግ (“የፌዴራል መንግሥት”) የበላይ አደራጅነት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ጎንደር ከተማ ለሚኖሩ ትግራዋያን ነጋዴዎች “የጠፋባቸዉንና የወደመባቸዉን ንብረት” ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማስመዝገብ የካሳ ክፍያና እንደ አስፈላጊነቱ የረዥም ጊዜ የብድር አገልግሎት ሊመቻችላቸዉ እንደሆነ የጎልጉል ታማኝ የመረጃ ምንጮች ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተወክለዉ የተላኩ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የንብረት ገማች ባለሙያዎች ጎንደር ከተማ ተገኝተዉ “ተአረፉና ወደሙ” የተባሉ የትግራዋያንን የንግድ ደርጅቶች ወርቅ ቤቶችን፣ ሱቆችን፣ ሆቴሎችንና መኖሪያ ቤቶችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል። እንደ ጎልጉል የመረጃ ምንጮች  በጎንደር ከተማ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ትግራዋያኖች ከፍተኛ ግነት ባለዉ መልኩ ያልጠፋቸዉን ንብረቶች (በስቶክ ያልተመዘገቡ) አስመዝግበዋል።በተለይም የሁመራ፣ የተክሌ፣ የመሀሪ ወርቅ ቤት ባለቤቶች በህዛባዊ ተቃዉሞ ጊዜ ወርቅ ቤቶቻቸዉ ተዘግተዉ የነበረ በመሆኑ በርና መስኮታቸዉ ላይ በድንጋይ ድብደባ ጉዳት ከመድረሱ ዉጪ ይህ ነዉ የሚባል ንብረት ባልተዘረፈበት ሁኔታ ከፍተኛ የንብረት ዉድመት መድረሱንና በሚሊዮኖች ብር የሚያወጣ ወርቅ መዘረፋቸዉን አስመዝግበዋል።

ቅዳሜ ገበያ በተቃጠለበት ጊዜ

በተመሳሳይ መልኩ የሁመራ ፔንሲዮን፣ ጣና ሆቴል፣ ሮማን ሆቴልና ቋራ ሆቴል ባለቤት የሆኑ ትግራዋያን ወደመብን የሚሉትን ንብረት በሚሊዮኖች ደረጃ አስመዝግበዋል። በአንጻሩ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ አማሮች በህዝባዊ ተቃዉሞዉ ጊዜ የወደመባቸዉ ንብረት በከተማ አስተዳደሩ እንዲመዘገብላቸዉ በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም “ከክልል ትዕዛዝ አልተሰጠንም” የሚል ምላሽ ሲሰጣቸዉ ቆይቷል። በተለይም ከትግራይ ክልል በመጡ ሰርጎ ገቦች እንደተፈጸመ የሚጠረጠረዉ የከተማዋ ዋና የገበያ ማዕከል የሆነዉ “ቅዳሜ ገበያ” 446 የባህልና የዘመናዊ አልባሳት መሸጫ ሱቆች፣የጫማና ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችና መደብሮች “በድንገተኛ” የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደመባቸዉ ነጋዴዎች ዛሬም ድረስ አስታዋሽ አጥተዉ ባሉበት ሠዓት ለትግራዋያን ተወላጆች ብቻ ለይቶ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸዉ የከተማዋን ተወላጆችና ተጎጅዎችን እንዳሳዘናቸዉ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች ከወደ ጎንደር ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።

“በርግጥ ኢትዮጵያ ዛሬም ያልተሟላች ሀገር ነች። ለአንዱ ማርና ወተት የምታዘንብ ለሌላዉ ደግሞ መዐትና መከራ የምታወርድ ጉራማይሌ ሀገር ሆናለች። ተስማማንበትም አልተስማማንበትም በአንድ ሀገር እየኖርን በዚህን ያህል መጠን መለያየታችን እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነዉ። በአደባባይ አይን ያወጣ የብሄር መድሎ መፈጸም ሀገሪቱን ፍጹም ወደ አልተፈለገ መስመር ይመራታል እንጅ መፍትሄ አይሆንም። ትግራዋያንም ቢሆን በዚህን ያህል መጠን እንደ ብሄር ሊባል በሚችል መልኩ የሀገር ሀብት ቅርምት ተሳታፊ መሆናቸዉ ለነገ ዉርስ ዕዳ እያስቀመጡ መሆኑን ሊያዉቁት ይገባል። የሀገራችን ሰዉ “ግርግር ለሌባ ይመቻል!” እንደሚል የጎንደሩን ህዛባዊ ቁጣ ያስታከኩ ትግራዋያን ባለሀብቶች ጎንደር ላይ ያልታሰበ የትርፍ ሲሳይ ዘንቦላቸዋል” በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪ ለጎልጉል ተናግረዋል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. There is no more peaceful news,ledanm lemut,wede geta metegat yeshalegnal,tragic.

 2. “በርግጥ ኢትዮጵያ ዛሬም ያልተሟላች ሀገር ነች። ለአንዱ ማርና ወተት የምታዘንብ ለሌላዉ ደግሞ መዐትና መከራ የምታወርድ ጉራማይሌ ሀገር ሆናለች።
  >> የሁመራ፣ የተክሌ፣ የመሀሪ ወርቅ ቤት ባለቤቶች በህዛባዊ ተቃዉሞ ጊዜ ወርቅ ቤቶቻቸዉ ተዘግተዉ የነበረ በመሆኑ በርና መስኮታቸዉ ላይ በድንጋይ ድብደባ ጉዳት ከመድረሱ ዉጪ ይህ ነዉ የሚባል ንብረት ባልተዘረፈበት ሁኔታ ከፍተኛ የንብረት ዉድመት መድረሱንና በሚሊዮኖች ብር የሚያወጣ ወርቅ መዘረፋቸዉን አስመዝግበዋል።
  >> የሁመራ ፔንሲዮን፣ ጣና ሆቴል፣ ሮማን ሆቴልና ቋራ ሆቴል ባለቤት የሆኑ ትግራዋያን ወደመብን የሚሉትን ንብረት በሚሊዮኖች ደረጃ አስመዝግበዋል።
  **************!
  >>> በጎንደር ከተማ የሚኖሩ አማሮች በህዝባዊ ተቃዉሞዉ ጊዜ የወደመባቸዉ ንብረት በከተማ አስተዳደሩ እንዲመዘገብላቸዉ በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም “ከክልል ትዕዛዝ አልተሰጠንም” የሚል ምላሽ ሲሰጣቸዉ ቆይቷል።…
  >>> ከትግራይ ክልል በመጡ ሰርጎ ገቦች እንደተፈጸመ የሚጠረጠረዉ የከተማዋ ዋና የገበያ ማዕከል የሆነዉ “ቅዳሜ ገበያ” ፬፲፻፵፮ የባህልና የዘመናዊ አልባሳት መሸጫ ሱቆች፣የጫማና ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችና መደብሮች “በድንገተኛ” የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደመባቸዉ ነጋዴዎች ዛሬም ድረስ አስታዋሽ አጥተዉ ባሉበት ሠዓት…

  __” ተስማማንበትም አልተስማማንበትም በአንድ ሀገር እየኖርን በዚህን ያህል መጠን መለያየታችን እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነዉ። በአደባባይ አይን ያወጣ (ዘርና ጎሳ) መድሎ መፈጸም ሀገሪቱን ፍጹም ወደ አልተፈለገ መስመር ይመራታል እንጅ መፍትሄ አይሆንም። ትግራዋያንም ቢሆን በዚህን ያህል መጠን እንደ በነገድና ፖለቲካ ተጠቃሚነት ሊባል በሚችል መልኩ የሀገር ሀብት ቅርምት ተሳታፊ መሆናቸዉ ለነገ ዉርስ ዕዳ እያስቀመጡ መሆኑን ሊያዉቁት ይገባል።”

  » በጣም አሳፋሪና ዘግናኝ ነገር ቢኖር እራሱን መመገብ ካልቻለው የሱማሌ ከልላዊ ሕዝብና መንግስት ፲ ሚሊየን፡ ከአፋር ከልላዊ ሻንጣ ተሸካሚ ቡድንና ጥቅማጥቀምኞች ፰ሚሊየን ዕርዳታ፡ በአውስትራሊያ በሚገኙ ዲያስፐሮች በነጻ አውጪያቸው ኤምባሲ በኩል ለቁራሽ መሬትና ለህወአት አጋርነታቸን እጅ መንሻ ፲ሺህ ዶላር መቀፈላቸው የፖለቲካ ሽርሙጥናና በትግራይ ሰዎች ላይ ማላጋጥ በአማራ ህዝብ ላይ ለማሽቃበጥ የተሠራ መዳራት ነው እውነታው ከልሌ፡ ህዝቤ የሚሉት ድሃ ሕዝብ በምግብና ውሃ እጦት እየተሰቃየ ዛሬም የልመና አቁማዳቸን ይዘው መጽዋች ሀገሮች ላይ አሰፍስፈዋል።
  ****************!
  ***ለዚህ ሁሉ ጥፋት ዋናው የብሔርና ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም ሕዝብ እንደከብት ጋጣ በክልል የተጠረነፈበት..የህወአት፡ኦነግና ኦብነግ፡ የጫካው ማኒፌስቶ የከተማው ሕግ በቅንድቡ ላይ ጭረት፡ በአለባበሱና አነጋገር ዘይቤው፡ በዘፈንና ጭፈራው፡ በግንባሩ ላይ ብጥ፡ ዘርዝሮና መትሮ በሰጠው ክልል ለዩነትታችን ውብታችን በሚሉ ቱማታ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲንሳ፡ ሞፈር ዘለል..ትራክተር በቀል እያለ ‘በመፈራራትና በመጣራጠር’ ላይ የተመሠረተው ጽንፈኛ ብሔርተኝነት…በጸና አንድነት ላይ የቆመውን ኢትዮጵያዊነት እንዲክድ ያልተደረገበት ሸርና ደባ የለም።
  … ይህም ሕዝብን በቋፍ እያኖሩ ከማብላት ማባላት ባሕልና አዋጭ ቡልጠቃ ሆኗል። “ሰዶ ማሳደድ ሲያምረህ ሀገርህን በክልል ለውጥ” ሕዝብን ዋስተና የሚሰጠው መለመኛ በማደረግ፡ በገንዘብ እርጥባንና በሥልጣን ትቢት፤በመሳሪያ ብዛት መያዝ ሳይሆን፡ የሕግ ከለላ በመስጠት ሕገመንግስቱን… ‘መንግስትን መቆጠጣሪያ’ እንጂ፡ ‘የሕዝብ መጨቆኛ’ ባለማደርግ ተዘዋወሮ መሥራትና ንብረት ማፍራት፡ በችሮታ ሳይሆን በዜግነት መብት ለሁሉም ዜጋ እኩል መሆን ከሚታዩ አላግባብ ጥፋቶችም ይጠብቃል። የአብሮነት እሴት እንዲፈርስ ሲታለምና በዕቅድ፡ በዘመቻ ሲሰራበት ምን ይመጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር!?
  ** አድሎዓዊ ጥቅማጥቅመኞችም ተከልለውና በህወአት/ኢህአዴግ ጥላ ሥር ሆነው ትውልድ ባያመክኑና ባያባክኑ ሕዝብና ሀገር ባያጠፉ ይመከራል ዝም ያለ ሕዝብ የሞተ አደለምና በለው!።አራት ነጥብ።

 3. የትግሬ ወያኔን የማንነት ቀውስና የዝቅተኝነት ስሜት የተፈለገ ሓብት (ያዉም ተዘርፎ) ፣ የጠነባ ሥልጣን፣ የፈረንጅ ከረባት፣ የዐረብ የአንገት ፎጣ ሆነ ምንም ነገር ሊሸፍነው ሆነ አንገቱን ቀና አድርጎ ሊያስኬደው አይችልም። የዝቅተኝነት ስሜት መነሻውና መገንቢያው ደግሞ የታወቀ ነው። ( ሁሉ ሰው እኔን ዝቅ አድርጎ ይመልከተኛል ከሚል የሚነሳና የሚገንባ ማነነት ስለሆነ ) በቂጥ ቁሰል ይመሰላል። ስለሆነም ሃበት፣ ሥልጣን ወዘተ…. የሥነ ልቡና ዝቅተነኝነትን አይመልስም፣ አይሸፍንም ፤ አይገነባም፤ ኣያብልፅግም ፤ አያድነዉምም። ለዚህ ጥሩ ማሳያው ደግሞ የትገሬ ወያኔ ራሱ ነው። የትገሬ ወያኔ አጠገቡ ያለዉን የጎንድር ገበሬ ሆነ የጎንደር ህዝብ ሲጀመር ጀምሮ ይንቀኛል ብሎ ስለሚገምት፣ በ25 ዓመቱ የትገሬ ወያኔ አገዛዝ ዘመን የጎንደር ህዝብ በሙሉ በትገሬ ወያኔ ጥርስ ዉስጥ የገባ ጠላት ነው። የትገሬ ወያኔ ማፊያ ቡድን ይህ ጎረቤቱ የሆነውን ወንድሙን እንዲህ እንደ ጠላት አይቶ ሊያራቁተው፣ ሊያደኽየው ብዙ ቢጥርም ያ ህዝብ ግን እንደ እዉነቱ ከሆነ በሚደንቅ ሁኔታ በማንነቱ እጅግ የሚኮራና በዚያው ልክ ደግሞ ሠውን የሚወድና የሚያክበር ገራገር ህዝብ ነው። እኔ ለሥራ ጉዳይ በ2003 ዓ.ም ከናዝሬት ወደ ጎንደር ተጉዥ ነበር። ለ 2 ወርም በጎንደር ዩኑቭርስቲ በቆየሁበት ወቅት፤ የህዝቡ መስተንግዶ የሚደንቅ ነው። ሰው በልቶ የሚጠገብ የማይመሰለው ትንሹ ትልቁ እጥፍ ዘረጋ ብሎ ሰውን የሚያስተናግድ ህዝብ መሆኑን ተመልክቻለሁ። ድሮ ድሮ በአድኩባት ናዝሬት አብሬቸው የተማርኳቸው የጎንደር ልጆች ጓደኞች ነበሩኝና ስንቀላለድ ” ቀብራራው ጎንደሬ” የምንባባለዉን አስታውሸ፣ እኔም ወደ እነርሱ የትዉልድ ቦታ በአጋጣሚ ለሥራ ጉዳይ ሄጀ በካአል ሳዬው በእርግጥም ጎንደር ይገባዋል ብያለሁ። የትገሬው ወያኔ ይሄንን ህዝብ በጣም የሚፈራዉና የሚያበቀብቀውም በጣም ኩሩ ህዝብ ስለሆነ ነው። ቢፈራዉም አልፈርድበትም። ይህ ህዝብ በማንነቱ የሚኮራ፣ ባህሉን የሚወድ፣ ሰው አክባሪና ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይመሰለው ደግሶ ለማብላት የማይደክመው መሆኑን ስላየሁት እድለኛ ነኝ። ታዲያ ይሄን ህዝብ የትግሬ ወያኔ ቢጠላው ምን ይገርማል።…እነርሱ እኮ በማንነት ቀውስ ተስቃይተው ያደጉና የኖሩ፣ የዝቅተኝነት ስሜትም ስለሚሰማቸው፣ በደንብም በቅርበት ስለሚተዋቁ ይመስለኛል። ትዝ ይላችኋል የትግሬ ወያኔ ኢትዮጵጵያን ለመዉርር ወደ አዲስ አበባ ሲገስግስ እኮ 4ቀን ገትሮ የያዘው ይሄ ህዝብ ነበር። እኔ ያኔ አዋሳ ነበርኩ። ሌላው ደግሞ የተጋተረው የመረራ ጉዲና ትዉልድ ቦታ የአምቦ ህዝብ ነበር። የዝቅተኝነት በሽታ አያድረስ ነው ከ እንዲህ ዓይነት የዝቀተኝነት ሰሜት ይሠዉረን አሜን።

Speak Your Mind

*