የተቃውሞ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። ከ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ጋ ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰልፉ ወደ 80,000 የሚጠጉ ሰዎች መሳተፋቸውን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚገምቱ ጠቅሷል። የዜና አውታሩ አያይዞም የመንግሥት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን በሰልፉ የተገኙት በጥቂት መቶ የሚቆጠሩ እንደሆኑ መግለፃቸውንም ገልጿል።

ሰልፈኞቹ የጸረ-ሽብር ሕጉ ይሰረዝ፣ የታሰሩ የኅሊና እስረኞች ይፈቱ፣ የኢሕአዴግ መገለጫው ሙስና ነው፣ የሕዝቡ የመሬት ባለቤትነት ይረጋገጥ፣ መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም፣ ፍትኅ እንፈልጋለን፣ ዲሞክራሲ እንሻለን የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮችንም በከፍተኛ ድምፅ ማሰማታቸው ታውቋል።

በሰልፉ ላይ ከቃሊቲ እስር ቤት የተላከው የአንዱዓለም አራጌን ጨምሮ ዝዋይ ከሚገኙ እስረኞች የተላከ መዕልክት በንባብ ቀርቧል። ሠልፉ በአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ንግግር በፓርቲው ጽ/ቤት መጠናቀቁ ታውቋል። (ፎቶና ዜና: DW)

Comments

 1. **ጥንታዊቷ ቀበና ቅንብቢት ዛሬም ህዝባዊ ሆነች በለው!
  **ወያኔ ሙሉ በሙሉ የሀገር ባለቤትነቱን አረጋገጠ!ሠራዊቱ ማንበብና መጻፍ የመረዳት ችሎታው ሕገመንግስቱን ባለማስከበሩ ሕዝብን የመንቀሳቀስ መብት መንፈጉ ዕውቀት እንደሌለው አረጋገጠ!ሕገመንግስቱ ህወአት/ወያኔ ያስታጠቃቸው የተጨቆኑና የተረሱ ግን በህገመንግስት ወታቦ የተፈለፈላችሁ የሚባሉ ሀገርና ህዝብን በመከፋፋል ትውልድን ለማምከን ከመንቀሳቀስም አብሮ መኖርንም ገድበዋል።
  >>>ኢህአዴጎች በሕገመንግስቱ ጽሑፍ ፩ገፅ ተኩል ሥልጣን ጠቅልሎ አላስነካ ያላቸውን ለመንጠቅና ለ፯ለመካፈል መለስ ዜናዊን አስገድለው ፈጣሪን ሲከሱ “ተተኪ መኖሩን ባወቀ ሞት እንዲህ ባልተጨነቀ!? ..አሉ።ሲጨቆኑና ሲረገጡ ከነበሩ ብሄሮች አሁን የፊተኛው ወንበር ላይ ተቀምጠው ከኋላ ቂጣቸውን በህወአት እየተገረፉ ከሚቀባጥሩት ከኅይለማርያም ጎን አቶ ሬድዋን፤ሼምየለሽ ካሚላ፣ዲና ሙፍቲ፣ ሽፈራሁ ተ/ማርያም፤ ትምህርትን ለመበከል ከወሎዬው ሙስሊም ደመቀ መኮንን ሁሴን ሥልጣን ተነጥቆ ሃይማኖት አልባው ሽፈራሁ ሽጉጤ ሥልጣኑ ሲሰጠው ብሔር ብሔረሰብ ጥሩ የህወአት/ወያኔ የሙስና ሻንጣ ተሸካሚ ሆነው ሲያገለግሉ ኢህአዴግ በሀገሪቱ ምግብ ብቻ ሳይሆን የጭንቅላትም ድህነትን አጎናፅፎ ሊሞት ነው።

  **የአዲስአባባ የክለል ፖሊስና የፌዴራሉ ህወአት ፖሊሶች በጋራ ሰላማዊ ሠልፍል አደረጉ።ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ሲያጅቧቸው ውለዋል፡፤ ይህም ማንም የመንቀሳቀስና የመዘዋወር ፣የመሮጥና የመራመድን ሕገመንግስት ካልተፈቀደለት ቦታ የሚሰበሰብ ዜጋ ሁሉ ወንጀለኛ ነው የሚለውን ሕገመንግስት በተግባር ለማሳየት በሀገሪቱ ያለውን የ፩የብሔር ፪የብሐረሰቦች እና ፫ የህዝቦችን ልዩ መሆን የህገመንግስቱን ዜጎች ምንም ቦታ እንደሌላቸው በግልጽ አሳይቷል።
  ** ይህ ሕገመንግስት ከመፅደቁም ሆነ ኢህአዴግ አዲስአባባ ከመግባቱ በፊት ሰው አልነበረም የሚለው ፅሑፍ ሕዝቦችን የመኖር የመንቀሳቀስ ሥራ መክፈት እነዲሁም የሚሞቱበትንና የሚቀበሩበትን ሁኔታ ሁሉ በዜግነት መሥፈርቱ መሠረት ይሰጣል ይነፍጋል፡ ይህንኑ ሕግ ወያኔ አስፈፅሜአለሁ ሲል ተፎካካሪውም አበሮ ይከበር ይላል። እንዲሁም “ተገንጣይ የሜንጫ አብዮተኞችን” ጨምሮ ፌደራሊዝሙ መሬትና ሥልጣን ሰጥቶናልና አይነካም! አይደፈርም! አንደራደርም! አማራ መጥቶ ሥልጣን ከሚይዝ እንሞታለን ኢህአዴግ ድል አጎናጽፎናል ይላሉ። ምክንያቱም እየተጠቀሙ የቁራ ድምጽ አላቸው !የአዞ እንባ የሚያነቡ በህወአት/ወያኔ ሥም የቋንቋ፣ ታሪክን የሀገር ባህልና ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ንብረት ለማውደም ፣ዜጋን ለመምከን፤ ሙሉ ፍቃድና ከለላን ሰጥቷቸዋል። ጥቂት በጣም ጥቂት ግን” የማይከበር ሕግ ይቀበር!” ሲሉ ይደመጣሉ።አሳዛኙ ግን ቀበሮና በግ አብረው ተሰማርተው መጮሃቸው ነው።

  **ሌላው ፎጋሪ የሕግ በላሙያ መሳይ ገና ለሀጩንም አልሰበሰበብ ሼምየለሽ ካሜል አሉ ።
  ፩) “ክልከላን በአደባባይ ረግጠው ወጥተዋል ! **(አደባባይ ለምን እረገጡ ነው ጥያቄው?) ሀገሩ የማን ነው?
  ፪)ሽብርተኝነትን የሚያወድስና የሚያሞካሽ ቅስቀሳና ማነሳሳት (እስረኞቹ ቃሊቲ ተኝተው ነው የተረበሹትና የተቀሰቀሱት?)
  ፫) “ቀጥተኛ ሕጋዊ መዘዝ ያስከትልባቸዋል ? ሕግ ፍትሃዊ እንጂ “መዘዘዊ!” ከሆነማ ፍርድ ቤት የሄደ ሁሉ ወንጀለኛ ነው ማለት ነው!? በለው!
  ፬) በአደባአበይ መውጣት የተከለከለ ነው!!። መንቀሳቀስና መዘዋወር ማለት ጣራ ላይ መውጣት ይሆን? እስፖርት መሥራት ይሆን?
  ፭)”ከተፈቀደላቸውም ክልል ውጭ ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግም ያስከስሳቸዋል፡” ቀበና ብቻ ኢትዮጵያውያን ሆነች!ፈቃድ የሚሰጠው አካል ቅኝ ገዢ ነውን?
  ፮) ‘የፖለቲካ ምሕዳር’ ሲያምርህ “ጃንሜዳ” ትታጎራለህ አለዚያም በክልልህ ‘እስታዲያም’ ይሰራልሃል።

  **ድንቄም የህግ በለሙያ ፦ አይ የፈረደበት ሕገመንግስት አለ እንዴ? እግሩ ከካናዳ አይኑ ከህንድ እጁ ከደደቢት ጥርሱ ተሞክሮ ካላቸሁ በበበሀገሮች ተገጣጥሞ ተሠርቷል:: እዚህ ድሃና የዋህ መሃይም ህዝብ ላይ ተሞከረበት ሕገመንግስቱ ትክክል ቢሆን ይፈፀም ነበር!። የህገመንግስቱን መጣመምና ማደናበር ለተፈጠሩት ብሄሮች ኢህአዴግን ተለጣፊ ዜጋ አድረጎአቸው እንደ ጥሩ ማስፈራሪያ ይጠቀምበታል። ከሌለን ታልቃላችሁ!የሀገር መሪዎች አሳቢዎች ፣የኢኮኖሚም ጥቅምም ሃሳቢ እኛ ብቻ ነን።ከእኛ ውጪ ማንም የለም ብለዋል። አዎን ካልተከበረ ይቀበር!
  ድሮም ሕዝቡን በሶስት ዜግነት የከፈለ ነው። ብሔር፩ ብሔረሰብ፪ ህዝቦች፫ ኢህአዴግ ብቻ የሰልፍ ነፃነት አለው። ፩ኛ ዜጋ ነውና “ሁሉም ፓርቲ ለአንድ ዓላማ በህወአት የፖለቲካ ጥላ ሥር ብቻ ይሰባሰባሉ ይለዋል። መድብለ ፓርቲ አማራጭ ልሳን የለም የሰጠንህ ክልል የግልህ ሳይሆን የእኛ ነው ‘የኮንትራት መኖሪያ ቦታህ ብቻ ናት ይለዋል።!!!
  ይህንንም ብሔረተኞች በላኳቸው ተወካዮች አንብበው፣ ተስማምተው፣ ፈርመው፣ አፅድቀዋል ይላል፡፤ ይህ ማለት እዚህ ላይ ከፈረሙት ውጭ ማንም ፓርቲ መመሥረትም ይሁን መብት መጠየቅ መብት አይኖረውም።
  *** በአጭሩ አንድ ኦሮሞ ነው በኢህዴግ ተካቷል። ያለው አንድአማራ ነው በትውልድ ኤርትራውያን ተወክሏል። ያለው የደቡብ ህዝብና ህዝቦች በኅይለማርያም ካቢኔ ተወክሏል ስለዚህ እኛ ከፈጠርናቸው ውጭ መዘወዘወር፣ ፓርቲ መመሥረት፤መንቀሳቀስ፣ መሰለፍ፣ መጮህ፣ ሁሉ እንደውጭ ዜጋ ሊያስቆጥር የሚችል ነው።ህገመንግስቱን መግቢያ በደንብ ያንብቡ ምድረ ደንቆሮ አንቀጽ ፴፱ ላይ አፍጥጦ ከሕገመንግስቱ በፊት በሀገሪቱ ሰው አልነበረም የሚለው ኤአት ቅድመ አያት ያልነበረው በህወአት ወታቦ ተፈለፈለ እነደሆነ ፳፪ዓመት አልገባውም !!?ሼም ነው በለው!!ግን ንቃ ! እንቢኝ በለው! ሜዳና ሸንተረር ውሃ የሞላበት
  ሜዳውን ጨምሮ ሀገሬ ጋራ ናት!
  በቸር ይግጠመን !

Speak Your Mind

*