“ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ድንበር የለም” – ህወሓት የትግራይን ሕዝብ የሚያስትበት ቅስት ሲሰበር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና አብረዋቸው የተጓዙ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን በኤርትራ የ27 ዓመታት ታሪክ የመጀመሪያ የተባለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ይህ ዓለም ከዳር እስከዳር ያዳረሰ ታላቅ ግንኙነት በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የህወሓትን ውስን አመራሮች ዕቅድና የትግራይን ህዝብ የሚያስቱበትን ቀስት ሰብሯል።

መሪዎቹ የሃገራቱን ሕዝብ የጋራ ፍላጎት፣ እኩልነትና ሉዓላዊነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት እያደረጉ መሆኑንን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው የገለጹት ንግግሩ በተጀመረ በቅጽበት ውስጥ ነው። አቶ የማነ እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች ፈጣንና አዎንታዊ ውጤት የሚያስመዘግብ ስምምነት ይፋ እንደሚያደርጉ ነበር ፍንጭ የሰጡት።

ይህንኑ ተከትሎ የጸብ፣ የጥላቻ ግንብ መናዱንና የ“ፍቅር ድልድይ” መዘርጋቱን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ተስማምተናል” ሲሉ በደማቅ ፈገግታ የተናገሩትና ያበሰሩትታላቅ ዜና “ድንበር የለም፣ ድንበር ፈርሷል” የሚለው ነው።

ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ዘመቻ የከፈተባቸው ህወሓት በትግራይ ክልላዊ መስተዳድር ስም፣ ከዚህ ታሪካዊ ጉዞና የዕርቅ ቀን አስቀድሞ ድርድሩ ግልጽነት የሌለው፣ የትግራይ ህዝብን ፍላጎት የማያስተናግድ በሚል ጥላሸት ቀብቶት መግለጫ አሰራጭቶ ነበር። ይህ ብቻ አይደለም በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ሕዝብ እንዲነሳ በምኞት ደረጃም ቢሆን ጥሪ አስተላልፎ ነበር። በተለይም የተሟላ መረጃ እንዳያገኝ የተዘጋበትን የትግራይን ህዝብ ለማነሳሳት ያልማሰው ጉድጓድና ያልቧጠጠው የክልል አጥር አልነበረም።

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ ሳይሆኑ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር “መሪዎቹ የሃገራቱን ሕዝብ የጋራ ፍላጎት፣ እኩልነትና ሉዓላዊነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት እየተደረገ ነው” ሲሉ ብዥታውን አከሰሙት።

ከሰዓታት ልዩነት በኋላ ራሳቸው ዐቢይ አሕመድ እንደ ፍም በሚያበራ ፈገግታ “ድንበር የለም” ሲሉ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ካሁን በኋላ የድንበር ውዝግብ እንደማይኖር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አረጋግጠውልኛል ሲል አስተጋቡ። ኢሳያስ ራሳቸው ቃላቸው የሳቸው ስለመሆኑ አሳይተውት በማያውቁት መፍለቅለቅ አረጋገጡ።

ይህ ብቻ አይደለም። ወደብ፣ ድንበር፣ ትራንስፖርት፣ ስልክ እና ነጻ የሕዝብ እንቅስቃሴ እንደሚኖር ከስምምነት መደረሱን ሲናገሩ ኢሳያስ አሁንም በጭብጨባ አረጋገጡ። ቅስቀሳው መና የቀረበት ህወሓት አድሮ ምን እንደሚል ባይታወቅም ለጊዜው የትግራይ አክቲቪስት የሚባሉትን ጨምሮ ቅርጹ ግራ የሚያጋባ ሆኗል። ህወሓት ፍላጎቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ እስከሚያስቸግር ድረስ ባዶ ቀርቷል።

የትግራይ ሕዝብና የአፋር ሕዝብ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ምንም ዓይነት ጸብ እንደሌለው፣ በፍቅር ጉርብትና አብሮ መኖር እንደሚፈልግ፣ ቂምና በቀል እንደሌላቸው “እመኑኝ” ሲሉ የተናገሩት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ “ልክ እኛን እንደተቀበላችሁት ሁሉ ልባችሁን ከፈታችሁ” ሲሉ ነበር የኤርትራ ሕዝብና መንግሥት የፍቅር እጃቸውን እንዲዘረጉ የተማጸኑት።

ከጅምሩ የአልጀርሱን ስምምነት ለመቀበልና ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ አምኖ እጁን በመስቀል የተስማማው ህወሓት አድሮ ሌላ ቅስቀሳ ለማድረግ የተነሳበት አካሄድና የፖለቲካ መዛነፍ ከምን ፍርሃቻ የተነሳ እንደሆነ በርካታ አስተያየቶችና መረጃዎች እየወጡ ሲሆን ወደፊት ሁሉም ነገር ይፋ እንደሚሆን የአብዛኞች እምነት ነው።

ሃያ አራት ዓመት ሙሉ አገር በዘር መርዝ ሲያምስና ሲያፋጅ ቆይቶ ድንገት እንደ ቡሽ የተስፈነጠረው መለስ ዜናዊ ያቦካውና “ያበከተውን” ፖለቲካ በ90 ቀናት ውስጥ መስመር እያስያዙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኤርትራ ዘልቀው በመግባት ኢሳያስን ሳይቀር ዛሬ ነጻ አውጥተዋቸዋል። በፍቅር ዝማሬ አስክረዋቸዋል። ፍቅርን ለተጠሙ እናትና አባቶች ፍቅርን አብስረዋል። ከጅምሩ ችግሩ በሕዝብ መካከል ሳይሆን በጎጥ በተደራጁ ከሃዲዎች ተጠንስሶ አስከፊ ውድመት ያስከተለ የጸብ ግንብ ዛሬ ፈርሶ የፍቅር ድልድይ ተመስርቷል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

 1. Good news to all Ethiopians

 2. ጠ/ሚ አብይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃል ያለውን ጠብ ወደ ሰላም አሸጋገሩ እየተባልን ነው። ሰላም የማይፈልግ ህወሓት ብቻ ይመስለኛል። ኢሳይያስ የምናውቀው ኢሳይያስ እንጂ አዲስ ግለሰብ አይደለም። እንኳን ለኢትዮጵያ ለራሱም ህዝብ አልበጀም። ከህወሓት/መለስ ጋር ሆነው አሰብን የተዋዋሉ፣ ደም ያፋሰሱ ናቸው። ኤርትራውያን ባገራችን ቡና ላኪ እስኪሆኑ ድረስ፣ በጠራራ ፀሐይ ዘረፋና ግድያ ሲያካሂዱ፤ ሥራ ቅድሚያ ሢሰጣቸው፣ አንድ ቢሊዮን ዶላር መለስ ቼክ ሲጽፍላቸው፣ ወዘተ። ሰማንያ ሺ ሰው ደም የፈሰሰው ለምን ነበር? ለመሆኑ ይኸ ሁሉ ግርግር ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም ያስገኛል? ማንነው ለኢትዮጵያ ጥቅም የቆመ? እነ ዶ/ር ብርሃኑ ሥልጣን ያግኙ እንጂ ስለ ኢትዮጵያ ጥቅም ደንታ የላቸውም። ባለፈው ቢቢሲ ሃርድቶክ ላይ የግንቦት 7 አቋም የኤርትራን መብት ማስከበር እንደ ሆነ ነኣምን ገልጾ ነበር። ሌንጮ ለታ ላፋሰሰው ደም ወደ ሄግ ሄዶ ለፍርድ መቅረብ ሲገባው አገር ቤት ገባ አሉን። ማንነው የኢትዮጵያን መብት የሚያስከብረው? ጠ/ሚ አብይ “ተፎካካሪ” እንጂ “ተቃዋሚ” አንበል ብለዋል። ለዶ/ር መረራ አዲስ ሹመት ሰጥተዋል። ለዶ/ር ብርሃኑም ይቀጥላሉ። እንደ 1983ቱ ለንደን ኰንፈረንስ ዛሬም የአገራችን ዕጣ በአሜሪካኖች፣ በኢሳይያስና በዶ/ር በረከት እጅ ወድቋል። ኢትዮጵያውያን የህወሓትን መርዝ ውጠው ገና አማራ፣ ኦሮሞ እያሉ ነው። በጎሳ ተደራጅተው አናሳ ሆነዋል፤ ለአገር የሚበቁ አንድ የሉባቸውም።

  ለምን ወቅታዊ ትንታኔ የሚሰጡ ጠፉ? አብይ ኤርትራ ድረስ ተጠርቶ እንደሄደ ያህል ተጉዞ ውል መፈራረሙ ተገቡ አይመስለኝም። በኢትዮጵያና በኤርትራ መሓል ድንበር የለም ማለት ውሎ አድሮ ችግር አለው። የወቅቱን ችግር ለመፍታት ሌላ ቆይቶ የሚከሰት ችግር መፍጠር ነው። ችግሩን የሚቀሰቅሱት ደግሞ ኤርትራውያን ይሆናሉ። አሁን እየተካሄደ ያለው የሰላም ግርግር ጥቅሙ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለኤርትራ ነው። ኤርትራውያን ሲያያዝላቸው መልሰው የሚናከሱ ናቸው። መረሳት የሌለበት፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት አገር እንጂ አንድ አይደሉም። አንድም አይሆንኑም። በተባበሩት መንግሥታት ዘንድ እንደ አገር ተመዝግበው ወንበር ይዘዋል። ዶ/ር በረከት ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች ብሎ ሲያታልል ከርሞ፥ አሁን ተመልሶ ከፌዴሬሽን፣ ከኮንፌዴሬሽን እንቁልልጭ እያለ ነው። ስለ ኤርትራ እንጂ ስለ ኢትዮጵያ ቅንጣት ገዶት አያውቅም። በሰላም አሳብበው ኤርትራውያን አገራችን እንዳይዘርፉ ምን ማገጃ ተደርጓል? በዩጋንዳ፣ በኮንጎ፣ በደቡብ ሱዳን የሚያካሄዱትን ማየት በቂ ማስጠንቀቂያ ይሁነን። በኦሮምያና በአማራ፣ በቤንሻንጉልና በጋምቤላ ያሉ ዜጐች ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም ለሰላም ዘብ ይቁም። ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን፤ ኤርትራ ለኤርትራውያን!!

  • The border war started, because of the weyane’s Tgray- Republic- agenda. The same problem the people of Welqait, Xegede and Afar encountered, we did. Just earlier, in 1998.

   Haile Selassie illegally abrogated the federation, hence triggering the 30 year war. What the weyane did, was to agree for our right to hold a referendum. We guided them all the way to AA after all, and helped them stabilize their rule in the first 2 years- as a quid pro quo.

   Which geographical entity did we hold a referendum for, you might ask? The same Eritrea, Menelik signed away, in his treaties with the italians 100 years earlier. And Assab happens to lie, within this geographical entity.

   Get over your racist hate, of Eritreans as people.

  • My brothers,
   I could be wrong , But I think you really sound like those ‘bitter’ ‘ye Ya tweled’ era politicians , who got no better solution other than drawing ‘red’ divisive line with attack & counter attack flares tooth and nail just to score a point. Your judgmental opinion on : Lencho Letta , your distasteful remarks for Dr. merera’s and Dr. Birhanu’s assumed posts… etc tells me how much you despise your fellow brothers for having a different route for the cause that they believed in , how much you are dis-crediting the sacrifice they have paid, and how much you don’t want to compromise on your red line just to stay honest to your self. 🙁 Try breathing the positive air my friend , its much lighter and feels good.
   I agree with you on on your passionate assessment of Ethiopia should look after her interest, and so does Eritrea , However your portraying of the Eritreans as someone to her take advantage of and the Ethiopians as candid benevolent is past thinking, don’t under estimate the youth today , and don’t underestimate their tactics either, look what they have done to the iron clad TPLF junta conglomerates.
   my two cents for you – stay positive my brother embrace future, and leave bitterness behind !

  • Tedros Bogale says:

   I smell EPRP

 3. ዛሬም በፊትም ሲገርመኝ የነበረ ነገር አሁንም እንደገና ያስገርመኛል። ሰው ሰላምን ሲሻ አሜን የማይል እብድ እንጂ ጤነኛ አይደለም። አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድህረ ገጾችና ጭፍን የወያኔ አምላኪዎች ዛሬም ያው የሚያላዝኑት ዜማ ከበረሃ የተማሩትን ብቻ ነው። ትግራይ ኦን ላየን የተባለ ድህረ ገጽ በገጽ ይህን አስፍሮአል። “You can create dramas with Amhara extremists and Derg left-overs,but there will no be peace with out Tigrai and TPLF, it is a fact”. ትላንትም አማራ ዛሬም አማራ የወያኔ የልሳን መክፈቻ። የዚህ ዓረፍተ ነገር ችግሩ የትግራይን ህዝብ ከወያኔ ጋር ደብሎ በማቅረብ ዛሬም በስሙ ሊነግድ መድፈሩ ነው። አይበቃም እስከዛሬ የነገዳቹህበት? ጊዜው እንደመሸባቸው የማያውቁ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አባላትና ፍርፋሪ ለቃሚዎች ዛሬም በ11ኛ ሰአት የሚያላዝኑት መከፋፈልን ነው።
  በወያኔ ደም ጠልቆ የገባው ጥላቻ በአማራው ህዝብ ላይ ለመሆኑ ህዝባችን ያውቀዋል። ከአንድ ቤት አራት ወንድሞችን አፍኖ ለ24 ዓመት ደብዛቸውን ያጠፋው ወያኔ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ፤በፍራቻ ዓእላፍ ሰዎችን ጉድጓድ ውስጥ የከተተ አጥፊ ድርጅት እንደሆነ አለም ያወቀው ነው። በዘር ፓለቲካ መነገድ አበቃ። የወያኔ የበላይነት አከተመ። የኤርትራን ነጻነት እወቁልኝ እያለ ወያኔ ለዓለም ሁሉ እንዳለፈፈ አሁን ሰላም እንፍጠር ሲባል ማኩረፋቸው የቱን ያህል የጠወለገ አስተሳሰብ ያለው ድርጅት እንደሆነ ያሳያል። አማራም ሆነ የደርግ ትራፊ ወይም ሌላ ለሃገራችን አንድነትና ለወገኖች እኩልነት የሚቆም ከሆነ ከጎኑ መቁማችን አይቀሬ ነው። አክ እንትፍ ያልነው የዘር ፓለቲካ ምንጭ ወያኔን ብቻ ነው። ዶ/ር አቢይና አቶ ኢሳይያስ በአስመራ ያሳዮት ወንድማዊ መከባበርና መረዳዳት የሚደገፍ ሃሳብ ነው። ወያኔ መዋጋት ከፈለገ ይግጠምና እንየው። እንዳለፈው ወራሪ መጣ በማለት ዳግም የኢትዮጵያ ህዝብ ማታለል እንደማይቻል ግልጽ ሊሆንለት ይገባል። መገዳደል፤ መጠላለፍ በቃ!!

 4. ዘላለማዊ ክብር ለወይን!!

 5. The border war started, because of the weyane’s Tgray- Republic- agenda. The same problem the people of Welqait, Xegede and Afar encountered, we did. Just earlier, in 1998.

  Haile Selassie illegally abrogated the federation, hence triggering the 30 year war. What the weyane did, was to agree for our right to hold a referendum. We guided them all the way to AA after all, and helped them stabilize their rule in the first 2 years- as a quid pro quo.

  Which geographical entity did we hold a referendum for, you might ask? The same Eritrea, Menelik signed away, in his treaties with the italians 100 years earlier. And Assab happens to lie, within this geographical entity.

  Get over your racist hate, of Eritreans as people.

 6. The Greater Tigray Republic (GTP) creation ideology is now DEAD, CREMATED & BURIED On the REALITY of PAN-AFRICANISM.

  When PAN-AFRICANISM fulfills it’s REALITY then Africa becomes borderless continent and Africans travel or move freely to any part of it. African people become Africans living in borderless continent and ONE AFRICA WILL BE CREATE.
  Eg 1. Look at African highways linkage, Ethiopian & Eritrean new Peace negotiation (https://www.youtube.com/watch?v=Ryk1cllzzlc and https://www.youtube.com/watch?v=5sCs6-hKuLE) and Somalia request economic integration ( https://www.youtube.com/watch?v=lQc2QKBcHZY) that leads to Somalia part of Ethiopia following IGAD integration: https://www.youtube.com/watch?v=9rsMF8ywBh0
  Eg 2. Ethiopia: ስለ ግንቦት 20 ጠ/ሚ አብይ አህመድ ያስተላለፉት አስገራሚ መልክት| Prime Minister Abiy’s Message about Ginbot 20: https://www.youtube.com/watch?v=FZY7jvcnaBc
  https://www.facebook.com/Global-African-Migrants-Professio…/
  Eg.3. Ethiopia:“ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አያስፈልጋቸውም” ኢሳያስ አፈወርቅ አስደናቂ ንግግር Dr. Abiy Siwoya Ahmed
  https://www.youtube.com/watch?v=kJRyaH9gjcY
  Eg.4 Ethiopia & ጅቡቲ Economic Integration
  https://www.youtube.com/watch?v=aohqwDRPBuQ

  https://www.facebook.com/ayu.asshi/videos/pcb.2028949613784332/2028946707117956/?type=3

Speak Your Mind

*