በቅርቡ በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ይኖራሉ – የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የሥራ ኃላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር 102.1 እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል።

የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል ነው ተብሏል።

ዘርፉ እየተለየ ምርመራ የማድረግና ተጠያቂዎችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የ100 ቀን እቅድ አውጥቶ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እየሰራ መሆኑን ተሰምቷል።

በዚህ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፌስቡክ ገጽ ላይ በተሰጠው የባለአንድ ገጽ ዕቅድ በአገራችን የተጀመረውን ለውጥ ዳር ለማድረስ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በፈፀሙ ሰዎች የሕግ ተጠያቂነት የማረጋገጥ፣ የታራሚዎችን መብት አያያዝ ማሻሻል፣ የይቅርታና ምህረት አሰጣጥ ሥርዓቱን በተሟላ መልኩ ለመተግበር፣ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ የሚታዩ የጥላቻ ንግግር ወንጀል ሕግ ማውጣትና መተግበር እንዲሁም ሕገ ወጥነት፣ ስርዓት አልበኝነትና የመንጋ ፍትህን ለመቆጣጠር ከአሁን በፊት ታይተው የማይታወቁ ህጎችን የማርቀቅና የማሻሻል ሥራዎችን አቅዶ ውጤታማ ለመሆን የሕግና የፍትህ አማካሪ ምክር ቤት በማጠናከርና የሰው ሀይል በማደራጀት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙሃን ኅዳር 14፤ 2011ዓም መግለጫ የሰጡት አቶ ዝናቡ አስታውቀዋል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Comments

  1. እጅግ በጣም አስደሳች የለውጥ ጅማሮ ነውና ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።በተጨማሪ ወደ ክሊሎች፡ዞኖች እና ወራዳም ድረስ በተዋረድ መውረድ አለበት ምክንያቱም በየዩንቨርሲቲዎች ደህንነት በመሆን የመብት ጥያቄን የጠየቁ ተማሪዎች ደብዛቸውን ያጠፉ ማኒነታቸውን ደብቀው ዞኖች ወርደው ህዝብ ለህዝብ ሲያጋጩ የነበሩ ለምሳሌ የቀድሞው የሀላባ ዞን አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ኑር ሳሊያ በመቀሌ ዩንቨር በተመደበ ወቅት ብዙዎችን አሰውሩዋል ።በሚመረበት ዞን ትንሽዬ ከተማ ፌክ ISIS ፈጥሮ ሚስኪን ስረ አጥ ወጣቶችን ደካማ ወላጆቻቸውን ለመርዳት ከሚታትሩበት የቀን ሥራ ከሚሠሩበት ቦታ ISIS ነቸው በሚል አሳስሮ ቶርች አስደሪጉዋ ይህን በደል በመሸሽ የተሰደዱት ቁጥር ስፍር የላቸውም።የሀላባ ህዝብ ይህችን እስከፃፍኳት ደቂቃ ድራስ በፀራ ለውጥ ሀይሎች በመመራት ላይ ያለች ከተማ ናት።ከዝህ ቀደም የዶ/ር አብይ ን ምስል የያዛ ቲ ሸርት የለበሱትና ኮኮብ አልባ ባንድራ ያዛችሁ በሚል በወጣቱ ላይ የበቀል ዱላ በዘበት የፍትህ ያለህ!!!!’

Speak Your Mind

*