ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ

ከውጪ ሀገር የመጡ ሰዎች ለአፄ ምኒልክ ስለ ፎቶግራፍ እንዲህ ብለው አስረዷቸው “በአውሮጳ አንድ ትንሽ ሳጥን አለች ሰውን፣ ፈረሱን፣ ቤተመንግስቱን ሁሉ ወደ ሳጥኗ ታስገባና ሁሉን ትንሽ አርጋ ታሳያለች” አሏቸው

ምኒልክም በሰሙት ነገር ተገርመው እንዴት ይሆናል ይሄን ነገር ማየት አለብኝ ብለው የፎቶ ማንሻ እንዲመጣ አዘዙ።

ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓም አጼ ምኒልክ የመጀመሪያውን ፎቶ ሲነሱ

የፎቶ ማንሻውም (ካሜራ) ከእነ አንሺው በ1875 ዓም ወደ ሀገራችን ገባ። ሆኖም ግን አጼ ምኒልክ ፎቶውን ሊነሱ ሲሉ ቀሳውስቱ መኳንንቱ ከለከሏቸው፣ ርኩስ ነገር ነውና አጥፉልን አሏቸው።

ምኒልክም “እግዚአብሔር የፈጠረውን ነገር አታርጉ፣ አትንኩ፣ ነውር ነው ማለት አምላክን መቃውም ነው እንዲህ ያለ ሀሳብ አታስቡ ዞር በሉ ከፊቴ” ብለው ግንቦት 13 ቀን 1875 ዓ/ም አጼ ምኒልክ የምትመለከቱትን የመጀመሪያ ፎቶ ተነሱ።

መልካቸውንም በማየታቸው ወደዱት ከዚህም በኋላ ራሳቸው አጼ ምኒልክ ፎቶግራፍ ማንሳትን ፊልሙን አጥቦ እስከማሳተሙ ተማሩ፡፡

የኢትዮጵያ ባለውለታ እምዬ ምኒልክ!

ምንጭ-፡ የኢትዮጵያ ስልጣኔ መጽሐፍ (ሔለን ምኒልክ ቴዎድሮስ)

Comments

  1. The other side of tigrayonline.

  2. Getachew Selassie says:

    ዋው!በጣም፡ደስ፡የሚል፡ታሪክ፡ነው። በእውነት፡እኝህ፡ንጉሥ፡በአሁኑ፡ጊዜ፡ቢኖሩ፡አገራችን፡የት፡በደረሰች፡
    ነበር። ምግባር፡ከጥበብ፡ጋር፡እግዚአብሔር፡ሰጥቷቸዋል።

  3. ቄስና ደብተራ ድሮም (ጋሊሊዮ ለመጀመሪያ ጊዜ «መሬት ጠፍጣፋ ናት» በማለቱ በካቶሊክ ቀሳውስት የደረሰበትን ያስታውስዋል»፡፡

  4. Hey!!! Golgul!!! Where is my comments???? Did you swallow it??? It was supposed to be fixed at the screen. Do you have any reason for that!!???

Speak Your Mind

*