• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!

November 1, 2019 04:09 pm by Editor 3 Comments

የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡

የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ የጨፈጨፋቸው ሚኒስትሮች አጽም በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ በተመሳሳይ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች በግፍ ይገደሉ ነበር፤ የደረሱበት የማይታወቁት፤ አድራሻቸውና ማንነታቸው የተሰወረ እጅግ በርካታ ነበሩ።

የመረጃ ምንጮቹ እንደሚሉት የቤተመንግሥቱ መቆፈርና መታደስ በከፍተኛ ደረጃ የህወሓትንና ተባባሪ ጽንፈኞች ያስደነገጠው በዚህ በጅምላ መቃብር ይታወቃል የሚል ስጋት እንደሆነ ተናግረዋል። በቁፋሮው ከ300 በላይ የኦሮሞ ልጆች አጽም የተገኘ ሲሆን ጉዳይ በምሥጢር ተይዞ ለጊዜው በክብር እንዲቀመጥ ተደርጓል። “መለስ በ300 ኦሮሞዎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ” ያሉት መረጃ አቀባዮች፣ “በነዚህ ምስኪን ዜጎች አጽም ላይ “ታላቁ መሪ” በሚል የመለስ ምስል እንዲቆም ተደርጎ ነበር” ብለዋል። አያይዘውም ለማንኛውም በሚል ሁሉም ጉዳይ በፊልም ሰነድ መያዙንና በወግ በወጉ መቀመጡን ገልጸዋል።

ወደ ሥልጣን ከመጡ ማግስት በአገር ቤትና በውጭ አገር የተሰወሩና ደብዛቸው ጠፍቶ የቀሩ ዜጎች ጉዳይ በተደጋጋሚ ሲቀርብላቸው “እንፈልጋለን፣ መረጃ ያላችሁ ስጡን፤ ተባበሩን” በሚል ከመናገር በላይ እላፊ ሄደው ያልተነፈሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቤተመንግሥቱን ዕድሳት ለሚዲያ ባሳዩበትና ባብራሩበት ወቅት ስለዚህ ጉዳይ ያሉት ነገር የለም። ይህንን ጉዳይ የሚያውቁ ለጎልጉል ሲናገሩ “ጊዜው አሁን በመሆኑ ነው” የሚል እምነት ስላደረባቸው ነው።

መቼና እንዴት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ለጊዜው ሃሳብ ያልሰጡት የመረጃ ሰዎች፣ የህወሓትና የነጃዋር አዲሱ ፍቅር ይህንን ዘግናኝ ግፍና በደል እንዴት ከመላው ኢትዮጵያዊና ኦሮሞ ህዝብ አእምሮ ሊፍቀው እንደሚችል ወደፊት የሚታይ እንደሆነም አክለዋል። 

የህወሓት አባል የነበረው ስዬ አብርሃ በዘመነ ግፍና ፍዳ ህወሓት ምን ያህል ኦሮሞዎች ያለ ፍትሕ ይማቅቁ እንደነበር ሲናገር “የነበርንበት ክፍል ውስጥ ከሀያ አምስት እስረኞች ሀያ ሁለቱ ኦሮሞዎች ናቸው፤ … የእስር ቤቱ ቋንቋ ኦሮምኛ ነው” ማለቱ ይታወሳል። በመቀጠልም የለውጥ እንቅስቃሴ በተጀመረ ጊዜ ህወሓት በዋንኛነት የጨፈጨፈው የኦሮሞ ወጣቶችን እንደሆነ፤ ቁጥሩም ከ5,000 በላይ እንደሚሆን የብዙዎች ግምት ነው።

በዚህ መልኩ የኦሮሞን ደም ሲመጥ ከኖረው ህወሓት ጋር የስትራቴጂና የታክቲክ ልዩነት የለንም አብረን እንሠራለን በማለት ጃዋር መሐመድ ሰሞኑን የተናገረውን የኦሮሞ ልጆች እንዴት ተቀብለው በህወሓት የሤራ ፖለቲካ ውስጥ ሊገቡ ቻሉ? የፈሰሰውስ ደም? ይህስ በወጉ ያልተቀበረ አጽም አይወቅሳቸውም? በማለት የሚጠይቁ ጥቂቶች አይደሉም።

አጽሙ ሲወጣ ክፉ ሃዘንና የቁጭት ስሜት ይታይ እንደነበር የዜናው ሰዎች ተናግረዋል። ከተገኘው ሰነድ ጋር በማመሳከር ስማቸውን ለማግኘት ቢሞከር እንደማያዳግትም ገልጸዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት ወቅቱ ሲደርስ በወጉ ስለሚከውነው ለጊዜው ተጨማሪ ነገር ከመናገር ተቆጥበዋል። 

በዛሬው ቀን (አርብ) በአምቦ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ለማውገዝ ቀጠሮ የተያዘና ወረቀት የተበተነ ቢሆንም የታሰበው አለመሳካቱን የአምቦ ነዋሪዎች ለጎልጉል አስታውቀዋል።

ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ ለሁለተኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ለመሰናዶ ዶ/ር ዐቢይን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጆች ጥሪ አቅርበው ነበር። በአራቱም የአምቦ ቀበሌዎች የተደራጀው የአካባቢው ማኅበረሰብ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን/ልጃችንን መናገር አይቻልም፣ አሁን ገብቶናል” በማለት ነውጠኞች ሊያደርጉ የነበረውን ሠልፍና ጥሪውን አምክነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው እለት የአምቦን ሕዝብ ሰብሰበው በዝግ ካወያዩ በኋላ ከጠ/ሚ/ሩ በሰሙት ሁሉ ተሰብሳቢዎቹ መጸጸታቸው ተጠቁሟል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን እንዳሉ በግልጽ ባይናገሩም ስብሰባው በለቅሶ የተሞላ እንደነበር ታውቋል። ከዚህ ስብሰባ በኋላ አምቦና አካባቢው ላይ የታየው ለውጥ ተራ ሳይሆን በጸጸት የተሞላ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። እንደዚህ የአቅጣጫ ለውጥ ሊያመጣ ያስቻለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ምን እንደሆነ ለማወቅም ጉጉት ፈጥሯል።

ጎልጉል መረጃዎች ቢኖሩትም ለጊዜው መቆጠብን መርጧል። በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ለመቃወም በተለያዩ የክልሉ ከተሞችና ዩኒቨርሲቲዎች ወረቀት ቢበተንም፤ ጥሪ ቢተላለፍም የተቃውሞ ሰልፍ ስለመደረጉ የተሰማ ነገር የለም።

(ፎቶ፤ እውነተኛው ሳይሆን ለማሳያነት የቀረበ ነው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Uncategorized Tagged With: Full Width Top, jawar, jawar massacre, meles, meles zenawi, Middle Column, oromo, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Abebaw says

    November 2, 2019 08:11 am at 8:11 am

    yes genuine information,keep it up.Feeding real stories.

    Reply
  2. Shgootei says

    November 5, 2019 05:51 pm at 5:51 pm

    ጎልጉል ይህን ዓይነት የ300 ሰው ዕልቂት ወያኔዎች አይፈፅሙትም አይባልም ከዚህም በላይ ያደርጋሉ፤ ነገር ግን እነዚህን ጉዳዮች አስባችኋል?

    1) ምንጮጫችሁ በቀጣም ሆነ በተዘዋዋሪ ማረጋገጥ ወይም ሊያሳምን የሚችል ማስረጃ አልሰጧችሁም፤ አንባቢ እንዴት ይመን?
    2) አስክሬኖች ሲወጡና መላው ሁኔታ በፊል ተቀጿል ካሉ ስለምን ትንሽ ቁራጭ ፊልም ካልሆነም ፎቶዎች still images ማቅረብ አልተቻለም
    3) የሰጣችሁት ነገሩ የተደበቀበት ምክንያት አያሳምንም፤ ጉዳዩን መደበቅስ ወንጀል መደበቅ አይደለመ?
    4) እንዲያውም ይሄ ሕወሐትን እንደ ድርጅት መሪዎቹንም በየሥልጣን ሃላፊነታቸው መጠየቅና ተጨማሪ ውርደትና እሥራት ትዕዛዝ ማስውጫ አይሆንም?

    Reply
  3. whatsmyname says

    November 6, 2019 06:54 pm at 6:54 pm

    Dear editor,

    You deleting my comments because you didn’t like them? Or you judged them to be what you didn’t want to hear or, should I say, read? You want to inform or express your view to the public but you sit high and almighty admiring your ‘flawless’ work. If you were in a position of power you would do a hundred fold worse things than suppressing opinion. Ibab libun ayito eger nesaw

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am
  • የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ December 6, 2020 11:41 pm
  • “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ December 2, 2020 12:24 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule