ሃቀኛው መላኩ ፈንታ

መልከ ቀና ነው፤ ፀጉሩ እንደ መኸር ጤፍ ተኝቷል። ሲራመድ ይፈጥናል። ወደ ምኒሊክ ቤተመንግሥት እየገባ ነው። ገባ።

“አቶ መለስ ሦስት ምርጫዎች አሉኝ!” ቀጠለ።

አንድ ህግ ተክትዬ መሥራት፣ ሁለት እያስመሰልኩ መኖር፣ ሶስተኛ ሳልሰራ በሪፖርት መኖር!

አቶ መለስ በምርጫው ተደንቀው “በህግ ስራ፤ ማንም ከህግ በታች ነው” አሉት።

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ንግግር ከራሱ እሳቤ ጋር ተጣጣመ።

የሚኒስቴር የቤተሰብ መኪና አልቀበልም ብሎ ቤተሰቡ በአዲስ አበባ የታክሲ ሰልፍ መያዝ ለመዱ። ቁርስ እና ምሳውን ከመስሪያ ቤቱ ካፍቴሪያ በ15 ብር እየተመገበ ሥራውን አጧጧፈ።

አንድ የክልል ቢሮ ኃላፊ ቢያንስ ሁለት መኪና እና መኖሪያ ቤት ይሰጠዋል። ለዚህ ሰው ግን የለውም ።በጭቃ ቤት ይኖራል። ሰውየው የገቢዎች እና ጉምሩክ ኃላፊ ነው። ሚኒስትር ነው። የሃገሪቱ ገንዘብ በመዳፉ ቢያልፍም ወደ ኪሱ አያስገባም። ሰውየው መላኩ ፈንታ ነው።

አንድ ቀን የአቶ በረከት ስምኦን ዘመድ በ3 ሚሊየን ብር ያለቀረጥ ካሜራ አስገባ። መላኩ ሆዬ አስወረሰው። አቶ በረከት ቢደውልም ወይ ፍንክች መላኩ ሆዬ።

መላኩ ሒልተን እና ሸራተን ሆቴልን አያውቋቸውም። አላሙዲ ስለ መላኩ ኩሩነት ሁሌም ይደነቃሉ። ለአላሙዲ ሚኒስትሮች ይሄዱላቸዋል እንጂ ራሳቸው ወደ ሚኒስትር ቢሮ አይሄዱም። አላሙዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ብቻ ይገባሉ። ሌላ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በገንዘባቸው እና በወኪላቸው ያስፈፅማሉ።ኩሩው አቶ መላኩ ግን ከአላሙዲ ጋር ሸራተን አልተገናኙም። ይልቁንም አቶ አላሙዲ በአቶ መላኩ ተደንቀው ወደ ቢሮአቸው አመሩ። አቶ መላኩ እና አላሙዲ እንደማንኛውም ደንበኛ ቢሮ ተገናኙ።ሲገናኙም መላኩ የተለየ መቅበጥበጥ አላሳየም። አቶ አላሙዲ በአቶ መላኩ ተደነቁ።

አቶ መላኩ ሲታሰር ከሚኖርበት የመንግሥት ቤት ቤተሰቦቹ እንዲወጡ መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። የአቶ መላኩ ቤተሰቦች ወደ ጎዳና ሊወድቁ ሲል በክብሩ የማይደራደር በመሆኑ ቀድሞም አድንቀውት ነበርና አቶ አላሙዲ ለአቶ መላኩ ቤተሰቦች ቤት ሰጧቸው። እስከዛሬም የሚኖሩት አቶ አላሙዲ በፈቀዱት ቤት ነው። አቶ አላሙዲ ጉዳይ ለማስፈፀም በብቸኝነት ሂደው የነበሩት ወደ አቶ መላኩ ቢሮ እንደሆነ ይነገራል።

2005 ዓም ከ3 ሺ በላይ አማራዎች ከቤሻንጉል ተፈናቅለው ፍኖተሰላም ላይ ከተሙ።

አቶ መላኩ “አማራው ሁነኛ ተወካይ የለውም። ሀገሪቱም አግላዋለች” ሲል በኢህአዴግ ጉባዔ ተናገረ። በብአዴን ውስጥ ትምክህት ቤቷን ገነባች ተብሎ ተወገዘ።

አቶ መላኩ በ 2000ዎቹ አካባቢ የአማራ ልማት ማኅበር ቴሌቶንን አቀናጅተው በቀን ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ አሰብስበዋል። አማራው በኢኮኖሚ እንዲራመድ አማራ ባንክ እንዲከፈት አድርጓል። ይህ ባንክ በወቅቱ አማራው አማራ ሲሉት ብዙ ላይሞቀው ይችላል ተብሎ አባይ ባንክ ተብሏል። የደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካ እና በደብረብርሃን ያሉ ውስን ፋብሪካዎች የአቶ መላኩ የጥረት ውጤቶች ናቸው።

ጎንደር ፒያሳ የዳግማዊ ቴዎድሮስን ሃውልት እንዲቆሞ አድርጓል። አቶ በረከት እና አቶ መላኩ ጎንደር ቀበሌ አንድ አብረው አድገዋል። የዳግማዊ ቴዎድሮስ ሃውልት ሲገነባ አቶ በረከት አሻራ ብዙ ባይኖራቸውም የኔ ስም ከአሰሪ ኮሚቴው ካልገባ ብለው ስማቸውን አሰፍረዋል።

የወገኑ ወደኋላ መቅረት የሚያንገበግበው አቶ መላኩ በ 2005 ዓም የብሄሮች በዓል በባህርዳር ሲከበር ከተማሪዎች ካፌ ሻይ በ50 ሳንቲም አብረን ተቋድሰናል። አቶ መላኩ ክብራቸው እውነት እንጂ ስልጣናቸው አልነበረም።

ግንቦት 5 ቀን 2005 ዓም ሙሰኛ ተብሎ ወደ ቃሊቲ ገባ። ከተከሰሰበት ገራሚ ነገር ውስጥ የወይዘሮ መቅደስ ለማ ጉዳይ ነው።

አቶ መላኩ ከወይዘሮ መቅደስ ሁለት ልጆችን ወልዷል። ቴዎድሮስ እና ፋሲል መላኩን። ነገር ግን የሰማንያ ሚስቱን በስልጣኑ ከሌላ ወንድ የነጠቃት ነው ተብሎ ተከሰሰ። የሁለት ልጆቹን እናት ባለቤትህ አይደለችም ተባለ።

ሌላው ሆቴል ሄደህ ሳሙና እና ሻወር ስልጣንህን ተጠቅመህ በነፃ ተጠቅመሃል የሚል ክስ ነበር።

እንዲሁም ባለቤትህን ደብረሊባኖስ ገዳም በመንግስት መኪና ወስደሃል ተብሎም ተከሶ ነበር።

መላኩ 5 ዓመት ሙሉ ያለ ብይን በእስር ቆየ። በአምስት ዓመቱ እስሩ ተቋረጠ። አቶ መላኩ እንደ እስክንድር ነጋ፣ እንደ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከውጭ ወደ ሃገራቸው ገብተው ለሃገራቸው ሲሉ ዋጋ ከከፈሉ ብሩሃን መካከል ናቸው።

አብዛኛዎቹ መረጃዎች ከአቶ መላኩ አንደበት እና ከባለቤታቸው ከወይዘሮ መቅደስ የተወሰዱ ናቸው።

(ምንጭ፤ የሺሀሳብ አበራ ገጽ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Comments

 1. ይገርማል! መልካም ሰው የማይከበርበት አገር፡፡

 2. Aytalnew Newzendro says:

  The truth should have been told in time so that we stand with him and shorten the suffering.

 3. I doubt this story – it is just what the author says. First of all what is Melaku doing with EPRDF? How do we know he is not corrupt? Yes, he might felt Amhara people are disadvantage later on but to start with why join eprdf or its government – if there is a differece between the two. Also you said he didn’t get a government assigned house and then you say his family was kicked out of one. So Ala-moudi did that out of the kindness of his heart? I will find that heard to believe. When do we Ethiopians stop this cult status building of individuals? The whole story about Melaku is fishy.

 4. This is a fake story. No one works with woyane if the do not have an impaired or opportunistic trait. Melak is no different. Stop covering up the truth. He was a woyane minister at the end of the day imprisoned or not. So what is all this trim a about? Was he as you said an honest man?

 5. ወይ አጋጣሚ ! ኮ/ል መንግስቱ ኃይለ ማርያም ሌ/ ኮ/ል አጥናፉ አባተን ካስገደሉ በኋላ ከነቤተሰባቼው የሚኖሩበትን የመንግስት ቤት በአስቼኳይ እንዲለቁ አስደርገው 8 ልጆቻቸዉን ሜዳ ላይ እንዲፈሱ ወይም እንዲበተኑ ማደረጋቸውን የያኔው ሕፃን ልጅ ዛሬ ግን የ5 ልጆች አባት የሆነው ሱራፌል አጥናፉ አባት (የሌ/ኮ/ አጥናፉ አባተ ልጅ ) አሳዛኝ ታርካቸዉን በቅርቡ ጽፎ አስነብቦናል። ይሄ ታሪክ የሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች የመጥፎ ታሪካችን ጠበሳ ነው። ግን ግን ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ እንደተባለው ሁሉ በየትኛዉም አፍሪካ ውስጥ ያሉ ዲክታተሮች በህዝባቸው ላይ ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። አይደንቅም? – የሁሉም አገር የፍሪካ ዲክታተሮች ባህሪ !

 6. ከቀደመው ታሪካችን የዛሬው የሚለየው ጥላቻውና ሽኩቻው በዘር ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያዊነትን ይጠላል፡፡ በቅርቡ የወያኔው ባለሥልጣን ዶ/ር ደ/ጽዮን በመቀሌ በሰጡት መግለጫ ዶ/ር አቢይ እንደዚህ ከቀጠለ የትግራይ ህዝብ አንድ ነገር ያደርጋል። ምን ማለት ነው? ማንን ለማስፈራራት ነው? ወያኔ የቀን ለውጥን የማያይ እውር ድርጅት ነው። ዛሬ የሃገራችን ህዝብ ወያኔን አክ-እንትፍ ብሎታል። መዝባሪና የዘር ሰልፈኛን ጭራሽ ጠልቷል። የአቶ ለማ መገርሳን ድርጅቶ በአራተኛ ደረጃ ላይ ፈርጆ ራሱን አንደኛ ብሎ የሰየመው ወያኔ ህፍረት የማያውቅ ድርጅት ነው።
  በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ የደረሰውም ግፍ ከወያኔ የክፋት ኮሮጆ እየተቆነጠረ የሚዘራ መርዝ ነው። ሰው ለእውነት በእውነት የማይኖርባት ሃገር! አቶ በረከት ሻቢያ እንጂ ወያኔም አይደለም። ልቡ አስመራ ቂጡ አዲስ አበባ ነው። ደግሞስ በቃኝ ካለ በህዋላ ዛሬ ተመልሶ በወያኔ ሥር በመሆን ህዝባችንን የሚያምሰው ለምን ይሆን? ወያኔ ሙሉ ታህድሶ በማድረግ ህዝብ ለመረጠው ሥልጣን ያስረክባል ብለው ለሚያምኑ የፓለቲካ ጅሎች የምለው አንድ ነገር ነው። የቅርቡን የጄ/ል ሳሞራንና(ወይን ጋዜጣ) ና በመቀለ የዶ/ር ደ/ጽዮንን ቃለ መጠየቅ መጣጣም በቂ ይሆናል። አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድህረ ገጾች የሚለፉትን ማየት ተገቢ ነው። በሃገር ውስጥ ታዋቂ የነበረው “በረከት መንግሥተአብ” ስለትግራይ ዘፈን አወጣ ይለናል አንድ ሾተላ የወያኔ ድህረ ገጽ ጡሩምበኛ። ይመስለኛል ወያኔ በጎን ከኤርትራ ጋር ድርድር ጀምሯል። ይመቻቹሁ።

 7. እስክዛሬ በሌሎች ስናይ የነበረው ዘረኝነት በአማራውም ማየት ጀምረናል። አማራ በመሆኑ ብቻ መላኩ እንዲፈታ ከተፈታ በሁዋልም መኪና እንዲሸልም ሁኖዋል። ይገርማል!
  እኔ እንደማየው ይህንን የሚያደርጉት እንዳውም በመላኩ ሙሰኝነት ተጠቃሚ የሆኑ አይቀሩም እላለሁ።

 8. አቶ ሰውነት – እንደ ሰው በሰው ከሥር መፈታት ደስ ሊልህ/ሽ ይገባ ነበር። ያው ግን ወያኔና የተለጣፊዎች በሽታ ተስቦ ነው፡፡ ዞሮ ተመልሶ ሰውን በዘር ማሰለፍ። በወያኔ ያለ ቅጥ ሃበሳ የቆጠረው ወገን የአማራው ህዝብ መሆኑ ቢታወቅም ሌሎች የሃገራችን ህዝቦችና በየአደባባዮ ወያኔ ቆመንለታል የሚሉትና በስሙ የሚነግዱበትን የትግራይ ህዝብ ሳይቀር ለመከራ ዳርገዋል። እኔ ለሰው መኪና የምሸልምብት ሃብት የለኝም። ግን ቡና ወይም ሻሂ ለማለት እበቃለሁ። ያው እንኳን ተፈታህ ዳግም እንዳይጠልፉህ ተጠንቀቅ ለማለት። በወያኔ ዘመን ከእሥር መፈታት የመኖር ዋስትና አይደለምና። እንዲሁ ግን በቅርበትም ሆነ በርቀት ከእውነት ጋር ባልተገናኘ ነገር ሰውን መወንጅል ተገቢ አይደለም። ሙስና ስጪና ተቀባዮም ያው እኩል ወንጀለኞች ናቸው። ይህ መቆም ያለበት ነገር እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ከአቶ መላኩ የመኪና ሽልማት ጋር ግን የሚያገናኘው ነገር ያለ አይመስልም።

Speak Your Mind

*