የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!

ዜናው የውሸት ነው

ለሥራ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን ጠቅሶ ፋኑኤል ክንፉ ፈንታሌ በሚባለው የግል የዩቲዩብ ገጹ በድምጽ ያሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ መሆኑ ተጠቆመ። 

“የፈንታሌ ሚዲያ ምንጮች” እንደነገሩት ያስታወቀው ፋኑኤል ክንፉ ዜናው እውነት እንደሆነ አድርጎ ለማሳየት የተጠቀመው አቶ ለማ ለቪኦኤ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ነው። 

ለአቶ ለማም ሆነ በኦሮሚያ ጉዳይ እጅግ ቅርብ የሆኑ የሚዲያ ውጤቶች ለጊዜው ምንም ያላሉበትን ጉዳይ ፋኑኤል ምንጮቹን ጠቅሶ ይህንን አነጋጋሪ ዜና ትናትን ሌሊት (በአዲስ አበባ አቆጣጠር) ላይ መለጠፉ አነጋጋሪ ሆኗል። 

ዛሬ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የመከላከያ ሚኒስትርን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ የአቶ ለማ የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ የሚታወቅ አይደለም። የኤፒው ኤሊያስ መሠረትም የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አነጋግሮ በተመሳሳይ አቶ ለማ መልቀቂያ ስለማቅረባቸው የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አረጋግጦ ዜናውን “ፌክ” በማለት በፌስቡክ ገጹ አሰራጭቷል። ዜናው ሃሰተኛ ቢሆንም ይህ እስከታተመበት ድረስ ፋኑኤል ማስተባበያ አላቀረበም።

በሻኪሶ የወርቅ ማዕድን ማውጪያ አካባቢ ሚድሮክ ላደረሰው የጤና ችግር ተቃውሞ በገጠመው ወቅት በአንድ አፍታ ሚዲያ ላይ “ጃዋር እንዴት ሼኽ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ይታሰራሉ ይላል” በሚል በኦሮሞ አክቲቪስቶችና ልሂቃን ክፉኛ የተተቸው ፋኑኤል ዜናውን ከኦሮሚያ ጉዳይ ውስጥ አዋቂ ሊያገኘው እንደማይችል፣ ይልቁኑም አካሄዱ የዲጂታል ወያኔ ስራ አስፈጻሚ ዓይነት መሆኑንን የሚያመላክት እንደሆነ ነው አቶ ሙክታር ሰይድ ለጎልጉል የገለጹት።  

በኦሮሚያ ጉዳይ የቅርብ መረጃ ያላቸው አቶ ሙክታር ከዚህ ያለፈ ማንነታቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀው ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ እንዳሉት “ፋኑኤል ዜናውን በፍጹም ከኦሮሚያ ምንጮች ሊያገኝ አይችልም፣ ከሆነም በጣም ከራቀና ተባራሪ ወሬ ብቻ ሊሆን ነው የሚችለው፤ የዲጂታል ወያኔ ሥራ መሆኑን የሚያመላክቱ ብዙ ቅመሞች አሉበት፤ የሚገርመው ግን ህወሓቶች የብሔርብሔረሰቦች ጉዳይ ይመለከተናል እያሉ ለኦሮሞ ሕዝብ አዛኝ መስለው ሰሞኑን በመቀሌ እንደታየው ስንት እያወሩ ከአንዳንድ የኦሮሞ ኃይሎች ጋር እንሠራለን እያሉ በሌላ ወገን ደግሞ እንዲህ ዓይነቱን የመብት ረገጣ ይክዳሉ” ብለዋል።  

በመደመር ሃሳብ እንደማይስማሙ ያስታወቁት አቶ ለማ “ተሰሚነት ካጣሁ ቆይቻለሁ” ሲሉ በቪኦኤ በኩል ምሬት ማሰማታቸው ይታወሳል። የኦዲፒ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ በበኩላቸው አማራጭ ሃሳብ ካላቸው ሁሌም በሩ ክፍት መሆኑንን አመልክተው “ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጻቸው የአዲሱ አስተሳሰብ ውጤት በመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል” ማለታቸው የሚታወስ ነው።

አቶ ለማ ይህ ዜና እስከታተመበት ድረስ መልቀቂያ ያላስገቡ ሲሆን እሳቸው የሚመሩት ጥላ የተሰኘው የኦሮሞ ድርጅቶች ጥምረት ከሌሎች የብሄረሰብ ነጻ አውጪ ግንባሮች ጋር በዛሬው ዕለት ግንባር ለመመሥረት መስማማቱ የአቶ ለማ መጨረሻ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውን ሃሳብ አጠንክሮታል።

ፋኑኤል ክንፉ ከዚህ በፊት በረከት ስምዖን በመሰረተውና በሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን በጀት ይተዳደር በነበረው ሰንደቅ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ በመሆን ጋዜጣው በበጀት ችግር እስከተዘጋበት ቀን ድረስ ሲሠራ እንደነበር ይታወቃል።

በሌላ ዜና ኢሌሌ ሆቴል በተደረገ ስብሰባ አስር ፓርቲዎች መቀላቀላቸውን ፋና ዘግቧል። ከኦሮሚያ አቶ ዳውድ የሚመሩት ኦነግ ሸኔ ብቻ ነው ያለበት። ከአስሩ ፓርቲዎች ውስጥ አራቱ ቀደም ሲል አጋር ክልል ውስጥ የሚገኙ የ“ነጻነት ታጋዮች” ሲሆኑ ሲዳማ ነጻነት ንቅናቄን ጨምሮ ሶስቱ ከደቡብ ክልል ናቸው። ከአማራ ክልል ቅማንትና አገው በሸንጎና በፓርቲ ስም የተደራጁ ይገኙበታል። አቶ ዳውድ ውህደቱን አስመልክቶ ንግግር ሲያደርጉ በፈቃደኛነት የተከናወነ ሲሉ አሞግሰዋል።

ድርጅቶቹም

1) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)

2) የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)

3) የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርቲ ፣

4) የሲዳማ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ፣

5) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ

6) የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ

7) የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

8) የአገው ሀገር አቀፍ ሸንጎ

9) የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና

10) የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ናቸው።

አቶ ለማ የሚመሩት ጥላ የተሰኘው የኦሮሞ ድርጅቶች ኅብረት አሁን በተፈጸመው ግንባር ዙሪያ ያለው አቋም አልታወቀም። የግንባሩ የመጨረሻ ራእይም ይፋ አልሆነም። አዲስ ተመሠረተ በተባለው ግንባሩ ውስጥ አቶ ዳውድ የሚመሩት ኦነግ መገኘቱ ቀጣዩ ጨዋታ ምን ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

ከዐሥሩ ድርጅቶች በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው በጣም ጥቂቶቹ ሲሆኑ በአዲሱ የምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ምዝገባ ሥነሥርዓት መሠረት ተገቢውን የአባላት ፊርማ አሰባስበው ዕውቅና ለማግኘት የሚበቁት ምን ያህሉ እንደሆነ ሌላው አጠያያቂ ጉዳይ ሆኗል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

 1. We know know TPLF is the source behind the fabrication that Obo Lema ,submitted a letter of resignation.The main strategy for TPLf for disseminating this rubish, according Ethio-codes and Tolosa Ibsa is that. After the official statment of Obo Lema,TPLF sensed there is a frictaion between Lema and Abiy,and is in the process of planning a serious of sabotages aimed at assassinating Ethiopian officials,including Obo Lema.

  TPLF ,in collaboration with Ezekiel Gebisa,Daud Ibsa,Jwar Mohamed,Tesgaye Ararasa, has reached a deal in Mekele conference.One of the agreement of that conference is that plan an assassination aginst Obo Lema. Then,blame this on the regime and use it as a means to agitate the Oromo people for uprising against P.M Abiy.

  In other words, precipitate such a crisis within the reform team,mobilize the Oromos for anti Abiay protest,and use this occasion to usurp illegitimate power in collaboration with its junior partner the OLF. OLF is apolitical jackass that will not hesitate to bargain on the life of one of the beloved citizen. This dreamers will never leave the Ethiopian people alone so long they are given ample room to continue their dirty politics of stabilizing he nation.

 2. Tesfa!
  Your analysis or opinion is illogical, incoherent and out of this world. To hate TPLF is one thing but to conclude to ridiculous conclusion entirely different. Lemma and abiy are two sides of the same coin, they may disagree on somethings and that is natural. Also the other personalities you mentioned are within their rights to associate with whomever they wish and prefer. This is what is called personal freedom. The fear and doubts we endured under TPLF rule is gone. One thing you should understand is OLF is an organization and an idea as well . Oromos love the idea of freedom that OLF the organization enunciated many years ago.

  • Actually my opinion far from being illogical ,i sense, it generates surprise response from you. Lema’s interview with VOA,while he was conducting an official business was out of protocol than your assertion, “the differences between the two is minor”. Beside, the Mekele gathering which reportedly spent $14 million in expense for the entertainment of TPLF’s friends,mainly for drink, hotel and other luxury items while the people of Tegrie are in dire straight.

   And you said those who traveled to Mekele were ,”Exercising their personal freedom”.The Mekele conference is a discussion on how to conduct political subversion , with the participants involved against the reform team.As far as I know the decadent OLF was out of fortune since iat has nothing going for her after it spent decades immured in Asmara.Until the day team Lema traveled to Asmara and offered them a face saving means to enter Ethiopia.Ever since it entered through Bole Airport,it has been desperate for power. And this desperation, has led it to employ multiple means.

   One of it is to launch OLF Shane to be armed and financed through bank robbery,forced tax levy from merchants who work in Oromo and material support gained from TPLF. while the notorious Abatorbe is terrorizing the Oromos in to submission,by eliminating ODP members and police officers within Oromo.

   Two,use the OMN propagandists J.M,Ezekiel Gebisa,,Tesgaye Ararasa in cooperation with TPLF to spin revisionist ideas, to promote a forum favorable for TPLF come back.I am just calling the OLF a spade. And there is no such a thing of freedom of assembly,when OLF sympathizers assemble with TPLF to devise a means, how to remove a legitimate government.

   Not to mention the fact there is no such a thing as two centers of power in Ethiopia. TPLF can not continue to play two cards.She has to make up her mind between cessation or to stick around.That means,before any thing else, she has to settle this issue for once and for all with the people of Tegria. And the Ezkiel group if they have issue against the governme,nt they must address it in Ethiopia, thn to go to Tegrie to join a subversive movement.I can only say this the time has come any one that travels to Mekele be it the OMN propagandists or any paid cadre to choose either Mekele as his /her center or Addis. They can not have it both ways.If they insist both means we want them to be locked up.

Speak Your Mind

*