የኢትዮጵያ ወዳጅ ጆን ቤጀንት ዜና-ዕረፍት፣ የሃዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ወዳጅና የአፍሪካ ቀንድ አጋሮች [Partners in the Horn of Africa] የካናዳ ተራድኦ ድርጅት መስራች፤ በካናዳ የብሔራዊ መብቶችና ነፃነት ዋስትና ቻርተር በብሔራዊ ምክር ቤት እንዲፀድቅ አስተዋፅዖ ከተሳተፉት ጠበቃዎች አንዱ የነበረው ካናዳዊዩ ዮሐንስ ቤጄንት [John Baigent] ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ቤተሰባቸው፣ Partners in the Horn of Africaና በመላው ኢትዮጵያና ካናዳ የሚገኙ ወዳጆቻቸው ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቷቸዋል። ጠበቃ John Baigent ከአስራ ስድስት ዓመታት በፊት የመሰረቱት የግብረሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ በርካታ ሥራዎችን ሰርተዋል። የአፍሪካ ቀንድ አጋሮች ግብረሰናይ ድርጅትን ከሌሎች የዕርዳታ ድርጅቶች የተለየ የሚያደርገው ሁለት ዋና ዋና ቁም ነገሮች ይገኙበታል። እነርሱም:-

100% የሚሰበሰበው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ ለሚደረጉ  የእርዳታ ሥራዎች ይውላል። ይህ ማለት ድርጅቱ ለአስተዳደራዊ ስራዎች ከተገኘው እርዳታ ሳይቀነስ ኢትዮጵያ ለሚደረጉ ስራዎች ብቻ ይውላል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገነቡትን ፕሮጀክቶች የአካባቢው ማህበርሰብ ከ15%  ወይም 20% የሚደርስ አስተዋፅኦ የማድረግ ግዴታው የሚሰራውንም ማንኛውንም የግንባታ ሥራ የሚወስነው የአካባቢ ሕብረተሰብ ለአካባቢው የሚያስፈልገውና የሚጠቅመውን ቅድመ ሁኔታ በመስጠት ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Speak Your Mind

*