“እንጭኒ” ላይ የሜንጫው አብዮተኛቸው ጃዋር ያስቀመጠው ተጨማሪ የጥላቻ ሓውልት

ትውስታችሁን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ ካሁን በፊት እኔ የጻፍኳቸው፤ ጃዋር የተናገራቸውን ነጥቦች ላስታውሳችሁ። “ኦሮሞዎች ወደ ግንጣላ የሚመራቸው የመጀመሪያው ጉዞ አገባድደውታል” ጌታቸው ረዳ (3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ- 2015)

“በማሃይም አዝማሪዎች እና በደደብ ምሁራን ጭንቅላት እየተመራችሁ የምታሽቃብጡ ኢትዮጵያውያን ሁላ የኦነግ እና የሻዕቢያ ባንዴራ ይዛችሁ መዝለል እና ማሽቃበጣችሁን ተው” (ጌታቸው ረዳ “የግንቦት 7 ጀሌዎች የኦነግና የሻዕያ ባንዴራ ማውለብልብ ብርቅ ሆኖባቸዋል- 2015)

አሁን ደግሞ ጃዋርን ላስታውሳችሁ፡

“ኦሮሚያ በአፍሪካ ውስጥ እንደ ኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ብሔሮች የሚኖሩባት አካባቢ የለም። ምናልባት ጆሃንስ በርግ በስተቀር። ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ‘ብሔር’ ‘ብሄረሰብ’ የለም።ባሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያዊያን ውጪ፤ ቻይኖችና እና ሕንዶች መጥተው አሮሚያ ውስጥ ይኖራል።” ጃዋር መሐመድ ምንጭ Ethiopian seamy (3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ- 2015)

“ቤተክርስትያንና የኦሮሞ እድሮች መሰራት አለባቸው። ባለንብት ሐገር በተለይ፤ 5-10 ኦሮሞ ባለበት ቦታ፤ በሓበሻ ‘ቸርች’ (church) ሄደን የምናስቀድስበት፤ በሐበሻ ‘መስጊድ’ (Mosque) ሄደን የምንሰግድበት ምክንያት የለም። ሁሉም ቦታ ይሄ አስፈላጊ እንደሆነ በጣም እወቁ! አወቁ!” (ጃዋር መሓመድ ለኦሮሞ ሜኔሶታ ማሕበረሰብና ከሌሎች ቦታዎች የተሰበሰቡ አሮሞዎዎች ፋሺስታዊ የሆነ የጸሎት ሃይማኖት ስፍራዎች ሳይቀር በጎሳ እንዲለዩ የሰበከበት ንግግሩ) ምንጭ (“fugra news Published March 24, 2015 (ለጽንፈኞች ሲሰግዱ የነበሩ አንዳንድ ጸረ ወያኔ ሚዲያዎች ዛሬም በመስገድ ላይ ናቸው ጌታቸው ረዳ (editor Ethiopian Semay) publsihed Dec, 15, 2015)

ይህንን ስታስውሱ ጃዋር አዲስ አባባ ሄዶ እያደረጋቸው ያሉት እንቅስቃሴዎች በጉልህ መረዳት ትችላላችሁ።

ይኼውና ዛሬ አሜሪካ ውስጥ ሚኔሶታ ከተማ ሲኖር የነበረው ጃዋር መሓመድ የተባለው ኦነጎች ያሰለጠኑት ወጣቱ የኦሮሞዎቹ ቤኒቶ ሙሶሎኒ አዲስ አባባ በገባበት ወቅት ከቦሌ አየር ጣቢያ አቀባባል ጀምሮ በኦነግ ባንዴራ ተጥለቅልቆ በተሸበረቀበት አዳራሽ ያየነው ጉደኛ ትዕይንት የሚኔሶታውን የጥላቻ ስብሰባ እጅግ በከፋ መልኩ አዲስ አበባም ውስጥ እንድናይ መደረጉ በብሔራዊ የአገሪቱ ቴ/ቪዥን ጣቢያዎች እንደተላለፈ ታስታውሳላችሁ።

የሜኔሶታው ወጣቱ ሙሶሎኒ ጃዋር መሐመድ የወላጅ እናቱን ‘አማርኛ’ ቋንቋ መናገር ስለቀፈፈው አማርኛን እንደ የጠላት ቋንቋ አድርገው በሚመለከቱት የኢትዮጵያ ኦሮሞ ማሕበረሰብ (እዚህ እኛ ጋር ያሉት “መስፍን ፈይሳን እና ቶላስን” እንዲሁም ጥቂቶች ኢትዮጵያውያን ኦሮሞሞዎችን ሳንጨምር) የመግቢያ ንግግሩን ባጭሩ በአማርኛ እንዲናገር ተጋባዡ ጉባኤተኛው እንዲፈቅዱለት ጥያቄ ማቅረቡ ለ27 አመት የኦሮሞን ማሕበረሰብ ለምንከታተል ጥቂት ታዛቢዎች ባያስገርመንም የኦሮሞ ማሕበረሰብ አስተሳሰብ ያልተከታተለ ብዙውን የዋህ ዜጋ ያስገረመ ጥያቄ ነበር።

አስገራሚ የሆነብኝ ደግሞ አማራዎቹ ይዘውት የመጡ አሳፋሪ ‘ማማሰያ’ (ወንጪት)ነው። ትንሽ ልበል እና ወደ አማራዎቹ ልገባ ነው።በዛው ባዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የኢንተርሃሙዌው መሪ ጃዋር መሓመድ የሚመራው ጥላቻ እና ግንጠላ የሚሰራጭበት የኦሮሞ ኔት ወርክ ሚዲያ ቴ/ቪዥን እየተባለ የሚጠራው ጣቢያ ሲያስመርቅ  የአፍሪካችን መዲና የሆነቺው አዲስ አባባን ኦነግ የፈለሰፈውን “መሰረተ ቢስ” የቦታ ስም መጥሪያ እየተጠቀመ ፍንፍኔ እያለ በተደጋጋሚ ሲጠራት ከነ ኦሮሞ ብሔረተኞቹ ከእነ ለማ መገርሳ ጀምሮ እስከ ተራው የኦነግ ጀሌ ጭብጨባቸውን ሲያቀልጡት ነበር። የኦሮሞዎቹ ስካር እንደ የኔዎቹ ትግሬዎች የጎሳ ስካር ተመሳሳይ ስለሆነ በጎሳ ፋሺዝም የሰከረ ማሕበረሰብ ሊያንጸባርቀው የሚጠበቅበት “የኸርድ/ሞብ ሜንታሊቲ” (የመንጋ ባሕሪ) ስለሆነ ብዙም አላስገረመኝም። ይልቁኑ ያስገረመኝ ቄስ ይመስል ፕሮፓጋንዳቸውን እንዲያዳምቅላቸው የጠሩት ንጉሴ ጥላሁን የተባለው የብአዴን የብዙሓን መገናኛ ሓላፊ ለምርቃት ተገኝቶ ጃዋርን “የነፃነት ታጋይ” ሲል ያደረገው ረዢም የአሽቃባጭ ንግግሩን እኔኑን አስደንግጦኛል። ለመሆኑ ይህ አማራ የሚባል ማሕበረሰብ ያ ሑሉ ጭንቅና መከራ በኦሮሞዎች እና በትግሬዎች እየተፈጸመበት መሆኑን አዙሮ የሚያስብለት ጭንቅላት ያለው ምሁር ሰው አለው? እንዲህ ያለ የተደጋገመ ጅልነት ሳደምጥ “እኔኑን እየጨነቀኝ መጥቷል”። እውነት፤እውነት “እየጨነቀኝ መጥቷል”።

ንጉሴ ጥላሁን የተባለ ይህ የብአዴን አማራ ተወካይ እንደ ሙያተኛ እና ባለ ስልጣን በጃዋር መሓመድ ሲሰራጩ የነበሩት ኦሮሞ ወጣቶችን አስተሳሰብ የመረዘ አደገኛ የጥላቻ ቅስቀሳዎች አልሰማም ይሆናል እንዳልል ቢያንስ የጃዋር ማንነት በዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫው በአልጀዚራ ቀርቦ የተናገረው ንጉሴ አልሰማውም ማለት አልችልም። ሌላው ቀርቶ ግመል ተጭና የማትችለውን በብዙ ኩንታል ተጭኖ የማይቻለው የኢንተርሃሙዌ ጥላቻ ቅስቀሳ ማሕደሮቹን ትተን በትንሹ ማስረጃ አልጄዚራ ላይ የተናገረው እንኳ ንጉሴ ጥላሁን አልሰማም ማለት ይቻላል? እንዴት ተብሎ ነው ጃዋር አርሲ ውስጥ ያደገበት እስላም ማሕበረሰብ በብዛት በሚኖርበት ክልል ‘እስላሞቹ የሚያዙትን ካላደረገ ክርስትያን ማሕበረሰቡ አፉን ቢከፍት በሜንጫ ነው አንገቱን የምንለው’ እያለ ጸረ ክርስትያን የሆነ ይህ አክራሪ የሜንጫ አብዮተኛ ወጣት በምን ሂሳብ ነው በንጉሴ ምላስ እንዴት ፤ ከቶውኑ እንዴት ሲኮን “ጃዋር የነፃነት ታጋይ” ሆኖ ሊነግረን የቻለው? ያች አገር ምን ጉድ ነው 27 አመት እየፈለፈለችብን የኖረቺው?

 ምስጢረኞች እነ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ፈረስት ባንዴራቸውን እያውለበለቡ አማራ እወክላለሁ ብሎ የብአዴኑ ንጉሴ ጥላሁን ማሲንቆ ቢስ አዝማሪ ይመስል ማይክሮፈን ላይ ቀርቦ ሲወጠውጥ (በአማርኛ መወጥወጥ ምን እንደምትሉት አላውቅም ፤ምውጣይ ወይንም “ዋጣ” አዝማሪ ከሚል የትግርኛ ቃል የተገኘ  (አዝማሪ በማሲንቆ ሲዘፍን የሚደመጠው መልእክት ለማለት ነው )ከትግርኛ የተጠቀምኩበት የመግለጫ ቃል ነው) ስለ ጃዋር ታጋይነት ሲመስክር ማድመጥ ያሳምማል። አማራን እያስበሉት ያሉት እነማን ናቸው? ብላችሁ ብትጠይቁኝ የምሰጣችሁ መልስ ማንም ሳይሆን  እንደ ዘወትሩ መልሱ “እራሱ የአማራ ምሁር!” ነው። በዚህ ጉዳይ ለብረካታ አመታት ስለተነጋገርንበት እዚህ አሁን ብዙ አልገፋበትም።

ሌላ ቀርቶ አብይ አሕመድ ዋሺንግተን ዲሲ መጥቶ እያለ በሕዝባዊ ጉባአው ላይ አቶ ተክሌ የሻው ስለ አማራ እሮሮ ያቀረቡት ስሞታ ሲመልስላቸው አንዲህ ነበር ያለው “አቶ ተክሌ ስለ አማራ ማሕበረሰብ የዘር ጥፋት በላዩ ላይ እንደተፈጸመበት የተናገሩት ባሕር ዳር ላይ እንደተናገርኩት በአማራ ላይ ብቻ የዘር ማጥፋት አልተፈጸመም። ያልተበደለ የለም..” ሲል መልሶላቸዋል። ይህ ጉድ አላስገረማችሁም? የአብይ አጉል “መልስ” ባሕርዳር መጥቶ እያለ ለአማራ ተፈናቃዮች ጉዳይ ተነሰቶ የሰጠበት መልስ ያኔ እኔም ስለሰጠሁበት የመልስ መልስ ምት እዚህ አልደገምውም። ያንን ትችቴን ድረገጼ ላይ ፈልጋችሁ ተመልከቱት። በዚያ ሳያበቃ ሜኔሶታ ላይ ተገኝቶ ኦሮሞዎቹ ለአማራ ያላቸው ጥላቻ ማንጸባረቃቸው ሽፋን ሲሰጣቸው “ኦሮሞዎቹ የተበደሉበት በደላቸውን ተረዱላቸው፤እንንከባከባቸው፤ እናክማማቸው….’ ዓይነቱ ንግግር መልስ በመስጠት “አማራው እና ኢትዮጵያ” የበደላቸው ይመስል በኦሮሞች የተገደለውና የተባረረው የአማራን ብሔረሰብ ኦሮሞዎቹ እያንጸባረቁት ላሉበት ብልግና የተሞላበት ጥላቻቸው ሽፋን አብይ የሰጠው መልስ አማራዎች “እንዲረዳላቸው” ይጠይቃል። ላንጸባረቁት ጸረ አማራ ጥላቻ “ምንኑ ጥላቻቸው’ አማራዎችና ኢትዮጵያውያኖች እንዲረዱላቸው እንደፈለገ ለኔ ግራ ገብቶኛል።

የዘንደሮ ፖለቲካ ወዴት እየሄደ እንዳለ ግራ ገብቶኛል። አብይ ዲሲ መጥቶ እያለ ያደመጥኩት ውሸት በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሜ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ። አክሱም እስላሞች በሞት ሲለዩ የሚቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ርቀት 35 ኪ/ሜትር ርቀው ነው የሚቀበሩት ብሎ አንድ ዋሾ እስላም ሲዋሽ ዶ/ር አብይም ያለማወቅ እውነት መስሎት ያንን ውሸት ተቀብሎ ሲያስገባ ሰምቼዋለሁ። እኔ የአክሱም ሰው ነኝ፡ 35 ኪ.ሜትር ማለት እኮ  ዓድዋን አልፎ እንትጮን አልፎ ማለት እኮ ነው። ርቀቱ የት እና የት እኮ ነው እያወራን ያለነው። መቃብር ቦታው አክሱም ውስጥ ነው። ከከተማዋ ዳገት ትንሽ ተምዘዝ ብላ ያለችባት የከተማዋ ክልል ልዩ ዳገታማ ስፍራ ተጠምዝዘህ የምትገኝ መቃብር ስፍራ ነች። በቃ። እስላም ብቻ ሳይሆን መስጊድ ለመስራት የታገደው “የአክሱም ሴት ክርስትያን እናቶቻችንም” ጭምር በጥንቱ ቤ/ክ ውስጥም ገብተው ገብተው ሊያስቀድሱ አይፈቀድላቸውም። መቃብራቸውም አርባዕቱ አንሰሳ በተባለው የከተማዋ ጥንታዊ ቤተክርስትያን ውስጥ ነው። እናቴ የተቀበረችበት በዛው ቤተክርስትያን ውስጥ ነው። ቤታችን ከማርያም በስተጀርባ ትንሽ እርምጃ ተራምደህ ሆንም አርባእቱ እነሰሳ ቤተክረስትያን ግን ከቤታችን ይርቃል። ይህ ብቻ አይደለም። ሌሎች ቤተክረስትያኖች (መድሃኒአለም፤ ገብርኤል ሩፋኤሌ ሚካኤል፤ ስላሴ….የሚባሉ ቤተክርስትያናት በከተማዋ ውስጥ እንዲገነቡ አይፈቀድም) ማርያም ብቻ ነች ያለቺው። በቃ! ስለዚህ እስላም ብቻ እንደታገዱ አስመስላችሁ እየወሰዳችሁ ለፖለቲካ መጠቀሚያችሁ ለማድረግ የምትወሹ ሰዎች አቁሙ። 35 ኪ.ሜትር  የሚል አዲስ ውሸት ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ ሲነገር የሰማ ሰው እውነት ይመስለዋል። ያውም ጠ/ሚኒስትሩ እውነት መስሎት የዋሾው ሰውየ ተቀብሎ ሲደግመው። እንኳን መቀበሪያቸው መስጊድ እንዲሰሩበት የተሰጣቸው ከተማ ‘ውቅሮ” ርቀቱ ከከተማዋ ቢበዛ በ4 ማይል ርቀት ውስጥ ነው የምትገኘው።

ወደ ጃዋር ልመልሳችሁ እና ልደምድም።

ባለፈው የሜኔሶታ ትችቴ የ”ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ” (Ethiopia out of Oromia) መሪ ጃዋር መሓመድ ከነ አብይ እና ለማ መገርሳ በሚስጢር ሲሰራ እንደነበር እራሱ በ ኢ ቲ ቪ ነግሮናል ብየ መጻፌን አይዘነጋም። እንዲህም ብየ ነበር “ምድረ ተደማሪ እንግዲህ እንኳን ደስ አላችሁ!! የ1983 የሰላም እና የዕርቅ ጉባኤ ታሪክ የቆዳ ለውጥ አድርጎ በ2010 የሰላም እና የዕርቅ ጉባኤ ከተፍ ስለሚል ለመስማት የቀፈፋችሁ ካላችሁ ጆሮኣችሁን ካሁኑኑ አዘጋጁት።” ብየ መተቸቴም ታስታውሳላችሁ።

አዎ ጃዋር የነ ለማ ቲም መሆኑን ያስመሰከረበት እርግጠኛ “ማስረጃችን”- ጃዋር አዲስ አበባ በገባ ሳልሰት ሳይሞላው “እንጭኒ” ወደ ተባለ የኦሮሞ አካባቢ ሄዶ ስለተደረገው ጦርነት “ሃውልት እንዲቆም” የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጦ መመረቁን በዜናዎች ተዘግቧል።

ለዛ ሁሉ “የኢንትርሃሙየ ኢትዮጵያውያኖችን ከኦሮሞ ክልል ለማባረር የቀሰቀሳባቸው ቅስቀሳዎቹ” ይቅርታ እንኳ ሳይጠይቅ፤ የአኖሌ ሃውልት እንዳይበቃ እንደገና በቁስላችን ላይ ሌላ ተጨማሪ ጨው እንዲነሰንስ እነ ለማ እና አብይ ፈቅደውለት ለማየት በቅተናል። ለዚህም ነው ባለፈው ጽሑፌ  “እንግዲህ ተደማሪም እልልታ አበሳሪም፥ አንጨብጫቢም ፥ ጨፋሪም፥ አዝማሪም፥ ጸሐፊም፥ አሞጋሽም፥ አሽቃባጫቢም ሁሉ በነ አብይ እና በእነ ለማ መገርሳ እና አብይ አሕመድ ጫማ ስር ወድቀህ እግር የተሳለምክ የዋህ ኢትዮጵያዊ  ሁሉ እርምህን አውጣ” ስል የተቸሁባችሁ። ባለፈው ሰሞን ካልተረዳችሁኝ ይኼው ዛሬ ሁለቴ እንድታስቡ እንደሚያደርጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።

 ይህ ሁሉ ኢሳያስ መጣ ተደመር፤ ጃውር መጣ ተደመር፤ ሌንጮ መጣ ተደመር፥ የኦነግ ባንዴራ ይዘህ ና ተደመር፤ የሻዕቢያ ባንዴራ ይዘህ ና ተደመር፤ “ሁሉንም ዓይነት አራዊት” ጋር አብረህ እንደመራለን ብለህ መሬት ቀውጢ ያደረግክ አዝማሪ እና ምሁር ሁሉ ይህ ጉድ ስትተሰማ ምን እንደሚሰማሕ ባላውቅም፤ ዛሬም ያንን መጣል የማትፈልጓትን ተስፋ የምትባል ከንቱ ማጃጃያ ልባችሁ ላይ ተሸክላ አልወጣ ስለምትል ዛሬም “እስኪ” ጊዜ እንስጠው የምትሉ ጅሎች በዛው ጅልነታችሁ እንደምትቀጥሉበት ሳልጠራጠር አልቀረሁም። በተለይ አማራ የምትባል ምን አባቴ እንደማደርግህ አላውቅም። ልቤን እያቃጠልከው እስከመቼ እንዲህ እየተጃጃልክ መዝለቅ እንደምትፈልግ አልገባኝም። በተለይ የአማራ ወጣቶች ከዚያ የመጃጃል ስካር ቶሎ ውጡ!!! ሻዕቢያ መጣ ወንድማችን፤ ኦነግ መጣ ወንድማችን…እንዲህ ያለ ጅልነት አቁሙ! አዝማሪው እማ በምን ገመድ መያዝ እንደሚቻል አላውቅም ከድሮ ዛሬ ብሶበት ከፍተኛ የሆነ ‘ደላላ’ እየሆነ እራሱን አጃጅሎ ሌለውን እያጃጃለ ማስጨፈሩ በምን እንደምናስቆመው ግራ ገብቶኛል።

በኦሮሞዎቹ ያላችሁ ተስፋ ዛሬ እቅጩን እንድታዩት ሆኗል። ጃዋር በነ ለማ እና አብይ ሴራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ እና ሜኔሶታ ላይ የሰራው የጥላቻ ሴራ አዲስ አባባ እንዲደግመው ሆን ተብሎ የተሸረበ ጸረ አንድነት ተንኮል መሆኑን ዛሬም በድጋሚ አንጭኔ ላይ አምቦ ላይ የኦነግ ባንዴራ እየተውለበለበ ሌላ የጥላቻ ሃውልት መሰረተ ድንጋይ እንዲጣል ማድረጋቸው ከዚህ ወዲያ ኢትዮጵያውያኖች በምን ቃል ቢብራራላችሁ ትፈልጋላችሁ? ሰሞኑን ሶማሌ ክልል ላይ 7 ቤተክርስትያን ተቃጥለዋል፡ ኢትዮጵያውያኖች ታርደዋል፤ የመቃዲሾ ሰንደቃላማ በግራኝ አሕመድ ፈረስ ሐውልት ላይ ተውለብልቧል። ምድረ ተደማሪ ከዚህ ወዲያ በምን ቃል ልንገራችሁ። ወያኔ እና የኦነግ ውጤቶች እኮ በለውጥ ስም አገር እያፈረሱ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ሳልገልጽ የማላልፈው ጉዳይ መስፍን ፈይሳ የተባለ ሜኔሶታ የሚኖረው አርበኛ እውነተኛ ኢትዮጵያው ኦሮሞ ከፍተኛ ምስጋናየ ይድረስህ። ቶሎሳ የተባልክ ወጣትም እንደዚሁ። የአንድነት ሃይሉ እና አማራ የተባለ ማሕበረሰብ እራሱን ካላዘጋጀ ገና ጉድ ታያላችሁ እያልኩ ነው። አሳዛኝ የሚሆነው ግን የሰለባው ተጠቂ ምስኪን ተራው ሕዝብ ነው እንጂ ቆስቋሾቹ እሳቱ አያገኛቸውም። እነሱ ሰው በሞተባቸው ስፍራዎች እየተገኙ ሃውልት ማቆም፤ ፕሮፓጋንዳ መንዛት ብቻ ነው ስራቸው።

እኛ ጥቂት ዜጎች ለበርካታ አመታት በኦሮሞ ምሁራን እና የጥላቻ ፖለቲከኞች እየመጣ ያለው አስፈሪ ሁኔታ አስቀድመን ነግረናል። በተለይ እኔን የምትከተሉ አንባቢዎች ስለ ኦሮሞ ምሁራንም ሆነ ማሕበረሰብ ለመግለጽ ያደረግኩዋቸው በርካታ ጽሑፎች የምታስታውሱት ነው። አሁን እወን እየሆነ 3/4ኘኛው የጎበጣ (የንጥቂያ) መሬት ያልነበረ ስም እየሰጡ  ግዛትን ማስፋፋት በነ ለማ መገርሳ እንክብካቤ እና መሪነት ዛሬም በስልት ኦነግ እና ኦሮሞዎች እየተጠራሩ ‘ኢትዮጵያን ሊበታትኗት” ኦሮሚያ የተባለ የፍጅት እና የመከራ አገር ለመመስረት እየጣሩ ነው። ኢትዮጵያ የምትልዩ ዜጎች በተቻለን ያህል መክረናል፤ አስጠንቅቀናል። በርካታ ወንድሞቻችን እና አህትቶቻችን በማሃይም አዝማሪዎች እና በደደብ ምሁራን ጭንቅላት እየተመራችሁ የምታሽቃብጡ ኢትዮጵያውያን ሁላ የኦነግ እና የሻዕቢያ ባንዴራ ይዛችሁ መዝለል እና ማሽቃበጣችሁን ተው፤ ማንጨብጨባችሁ መጠን ይኑረው ብለን ስንመክር መልሳችሁ ስድብ ነበር። ይኼው ያንጨበጨባችሁለት ፕሮፓጋንዳ ሳያፍር ዓይን አውጥቶ የኦነግ ባንዴራ አዲስ አባባ ተውለብሎባለችሗል። ጅግጅጋም የመቃዲሾ እስላማዊ ባንዴራ ተውለብልቧል; አብያተ ክርስትያናት እና ምእመናን ታርደዋል። የ1983 ዓ.ም ጅቦች በ2010 ዓ.ም በነ አብይ እና ለማ መገርሳ አበረታችነት መሪነት ወደ መድረክ ብቅ ብለዋል። ኦሮሚያ በተባለው ምድር እና ሶማሌ በተባሉት ባልካናይዝድ ክልሎች የምትኖሩ ዜጎቻችን አምላክ ከናንተው ጋር ይሁን እያልኩ ጸሎቴ ይድረሳችሁ እያልኩኝ በሚቀጥለው ጽሑፍ እስክንገኛኝ ሰላም!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ማሳሰቢያ – ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ ላይ “የጎሳ ፖለቲካ በማሕበረ ሰብ እና በምሁራን አስተሳሰብ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ” ምን እንደሚመስል በከፈትኛ ጥናት የተደገፈ የዶ/ር አሰፋ የምርምር ጽሑፍ  ስለተለጠፈ፤ ጸሑፉ ለተወሰ ጊዜ ማሕበረሰቡ እየተመላለሰ እንዲመለከተው ስለፈለግኩ፤ የኔ ጽሑፍ ለጊዜው አይስተናገዱም። የኔ አጫጭር ዜናዎችም ሆኑ ትችቶች ያላነበባችሁ ካላችሁ ከኤርትራ የትግርኛ ሚዲያዎች የተገኙ ወደ አማርኛ የተረጎምኳቸው በርካታ አጫጭር ዜናዎች እና የራሴንም ትችቶች ለማንበብ ስትፈልጉ ኢትዮጵያን ሰማይ ፌስቡክ እንደገና ስለጀመረ እዛው ጎብኙኝ። እንዴት እንደምትገቡም ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ ላይ ሊንኩን (ማስፈንጠሪያው) ለጥፌዋለሁ።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Comments

 1. የዛ መርዘኛ የመለስ ዘመድ አይደለህ ፤ ከመለስ ወገን መቼም ጥሩ አይታሰብ ፤ ዘረ መጥፎ
  አትድከም ማንም አምኖ አይቀበልህም ።
  ዘረኛ መርዝ

 2. ጨካኝ እና እፋኝ ፣ ገዳይ እና ጨፍጫፊ ከሆነው የደደቢት ደደብ ማሕበረ ሰይጣን መምጣትህን ግልጽ ኣድርገኸዋል።

  የደደቢት ደደብ ምን ጊዜም ደደብ።

 3. መጀመሪያ የመጡበትን ታሪካዊ ማንነት በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል ከዚያ በውኃላ በኮፊደንስ ማውራት ይችላል
  ዛሬ ሀገሪቱን ፖለቲካዊ ጅኦግራፊ ለመቀየር የሚሯሯጡ ፅንፍ የረገጡ ቤሄርተኞች በአቋራጭ የሀገሪቱን ሀብት ለመቀራመትና ፖለቲካዊ ትርፍ ለማትረፍ ሆን ተብሎ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ የርስ በርስ ጦርነት የማይቀር ጉዳይ ነው ለምን አዲስ አበባ የሁሉም ግብር ከፋይና የሀገሪቱ 70% ያለበት ከተማ ነች፡፡

Speak Your Mind

*