የበጋው መብረቅ (ሌፍተንት ጀነራል ጃጋማ ኬሎ)

. . . ጃጋማ በውጊያ ብቻ አልነበረም ብስለቱ በአስተዳደርም የተደነቀ ነበር።ለምሳሌ፤ከአምቦ መንገድ በላይ ያሉት ነዋሪዎች ጥራጥሬ እያዋጡ ቆሎ እየቆሉ ለአርበኛው ይረዳሉ፤ከአምቦ መንገድ በታች ያሉት ግን የጃገማ አርበኞች ሙጀሌ የወረሳቸው ሰለሆኑ ይህን የተሰነጣጠቀ እግራቸው ችሎ መራመድ አይችሉም፤ስለዚህ እንኳን እኛን ከኢጣሊያ ስራዊት ሊጠብቁን እና ሊከላከልሉን ቀርቶ ለራሳቸውም ሰለማይሆኑ በምንም ነገር አንረዳቸውም ማለታቸውን ጃጋማ ሰማ። ለሰራዊቱም ትእዛዝ ሰጥቶ ወደ ሃያ ሺህ ከብቶቻቸውን አስነዳባቸው፤ ህዝቡም በጣም ተደናግጦ ምነው ምላሳችንን በቆረጠው በሚል በጣም ተደናገጡ።ቀንበራቸውን ተሸክመው የጃጋማ ጦር የሰፈረበት ቦታ ድረስ በመሄድ እግዚኦ አሉ።

ወጣቱ መሪ ጃጋማ እንዲህ አላቸው (እኛ ከእናንተ የወጣን የእናንተ ልጆች ነን፤ጠላት የሚንቀን አንሶ ለሐገራችንና ለእናንተ በባዶ እግራችን ጠላትን ስለተዋጋን እንዲት ሙጀሊያም ትሉናላችሁ) እኛ የወገኖቻችንን ንብረት የምንዝርፍ ተራ ውንበዴዋች አይደልንም ሁለተኛ እንዲህ እንዳታደርጉ ብሎ መክሮና አስጠንቅቆ፤ከብቶቻቸው አንድም ሳይጎድል እንዲመለስላቸው አዘዘ።

ጣሊያን ከሚያደርገው ሕዝብን የመከፋፈል አላማው አንዱ ኦሮምኛ ተናጋሪውን በአማርኛ ተናጋሪ ላይ ማነሳሳት ነው።ይሀንን ጠንቅቆ የተረዳው ጃግሻ ካአድርገው ውስጥ ለመጥቀስ ያህል፤ዘውዴ ጥላሁን የተባለ ጀግና ማይጨው የክብር ዘበኛ አባል ሆኖ ከንጉስነገስቱ ጋር የዘመተ ከደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ ጋር ሆኖ በጀልዱ ታላቅ ጀብዱበተደጋጋሚ በመፈጸሙ።ጣልያንን መውጫ መግቢያ በማሳጣቱ የትናደዱት የጣሊያን ጦር አዛዦች በአይሮፕላን ወረቀት በመበትን ዘውዴ ጥላሁንን ያስጠጋ ወይም ቀለብ የሰጠ አካባቢው በአይሮፕላን እንደሚደበደብ ማስታወቁና በደጃዝማች ከበደ ጦር ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት በማድረሱ ደጃዝማች ገረሱ ለግዜው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄድ ስለጠየቁት፤አርበኛ ዘውዴ አስራ ሁለት ተከታዮቹን ይዞ ቀኛዝማች ወዳጆ ዘንድ ሄዶ ወደ አማራ ክልል አሳልፈኝ ብሎ እንዲረዱት ተጠግቶ ሰፈረ፤ቅኛዝማች ዘውዴም ነገ ዛሬ እያሉ በጎን ጀግና ወዳጅን ጃጋማን ቶሎ እንዲመጣ አስደረጉት። ዘውዴ ጃጋማን ሲያይ ትንሽ ተከፋ፤ ምክንያቱም የጃጋማ የአጎቱ ልጅ አባ ዶዮ ለጠላት አድሮል መባሉን በመስማቱ ጃጋማ አስልፎ እንዳይሰጠው ሰለፈራ ነበር።

ጃጋማ የዘውዴን ጀግንነትና ጥርጣሬ በመረዳቱ (አንተን አሳልፌ ብሰጥህ ነፍሴ አይማር፤እኔ ሳልሞት አንተ አትሞትም) ብሎ ዘውዴን ሰንጎታ ይዞት ሂዶ ስሙን አስቀይሮ ገብረማርያም አስኝቶ እስከመጨረሻው የነጻነት ቀን ድረስ በፍቅር አብረው እየዘመቱ ኖረዋል።ይህ የሚያሳየው የጃጋማን ፍጹም ኢትዮጵያዊነት ነው። . . . (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Speak Your Mind

*