ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር የአገር ስጋት ሆኗል ተባለ

ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአገር ደረጃ ስጋት ሆኗል ተባለ። ከተለያዩ አገራት በድንበር በኩል የሚገባውን ሕገወጥ የጦር መሳሪያ አስመልክቶ ጠንከር ያለ ሕጋዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በከተማዋ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ጠንካራ የቁጥጥር ህግ ያስፈልጋል ብለዋል።

412 ሽጉጦችን፣ ከ12 ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶችንና ከ9 ሺ በላይ የክላሽ ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 5 ተጠርጣሪዎችን ፍ/ቤት በዋስ መልቀቁ ጥብቅ የሆነ አሰራር ላለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በተጨማሪ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋና ቤት ሰብሮ ስርቆት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል።

እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጥናት የተደገፈ የክትትልና የምርመራ ቡድን ማዋቀሩን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚጥሉና የአገርን ኢኮኖሚ የሚጎዱ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተነግሯል።

ነዋሪውም የከተማውን ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ለፀጥታ አካላት ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል።

ከዚህ የሸገር 102.1 ዘገባ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደተናገረው በአዲስ አበባ ከተማ በሶስት ቡድን ተደራጅተው ከባድ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከነመሳሪያቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። (ፎቶው ኢትዮጵያ ሳይሆን ለማሳያነት ከኢንተርኔት የተወሰደ ነው)

(ጎልጉል)

Comments

  1. ይህ የ27 አመት የሕገወጥ የፓለቲካ ድርጅት መሪዎች ገና መንግሰት ተብለው ሰይሰየሙ በፊት የነበረው የሕገወጥ የገቢ መንጫቸው ነው መንግሥትም ውስጥ ሆነው ይሰሩበት የነበረ ሰለሆነ ኣለም አቀፍ የወንጀል ድርጅት ነው። አሁንም በአንዳንድ የጉምሩክ መግቢያ በሮች የሚሰሩ ግለሰቦችን በመመደብ በሕገወጥ መንገድ እንዲገባና እንዲወጠሠ ያደርጉ የነበሩት እነዚሀለ የተደራጁ ኃይሎች ናቸው። ሰራዊቱን አጥሩ የወታደሮችና የነጋዴዎች መኪና በአግባቡ ይፈተሽ። የጉምሩክ ሰራተኞች በየጊዜው መቀያየር አደጋውን ይቀንሳል ።በጉምሩክ የፍተሻ ቦታዎች ላይ የፍተሻ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀምም አስፈላጊ ነው። የሕዝብ ደህንነት የሚጠበቀው በሕዝቦችም ጭምር ነው እንጂ በደህንነት ሰዎች ብቻ አይደለም።

  2. ህወሓት በኦሮሞና በኦሮሞ መካከል፣ በአማራና በኦሮሞ መካከል ጠብ ለመዝራት እየጣረ ነው። እነ ለማ ህዝባቸውን እንዲወጉ ለማድረግ ነው።

Speak Your Mind

*