ኤች.አይ.ቪ./ኤድስ በአዲስ አበባ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ደርሷል

በአዲስ አበባ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት 3 ነጥብ 4 በመቶ ደረሰ። በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ የስርጭት መጠን 3 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፅ/ቤት ከአስሩም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ከተውጣጡ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ጋር የ2011 እቅድ አፈፃፀምን እየገመገመ ይገኛል።

በግምገማው ላይም በከተማዋ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እና አሁን ላይም 3 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተመልክቷል።

ለዚህም በከተማዋ ያሉ አጋላጭ ቦታዎች መስፋፋት እና የስነ ምግባር ክፍተት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

በአለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት የኤች አይ ቪ ስርጭት ከ1 በመቶ በላይ ከሆነ ያ ሀገር በበሽታው ወረርሽኝ ውስጥ ነው።

ይህም በከተማዋ ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት መጠን በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የሚያመላክተው።

ምንጭ፤ አሃዱ ሬዲዮ

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Speak Your Mind

*