የሂወት ውል /Hewett Treaty/

የሂወት ውል በ1876 ዓ.ም (1884) አጼ ዮሐንስ ከእንግሊዝና ግብጽ ጋር ውል የገቡበት ሲሆን ንጉሱ በሰሩት የፓለቲካ ቀመር ስህተት የኢትዮጵያን ጥቅምና ሙብት አሳልፈው ለወራሪዎች የሰጡበት፣ ከጎረቤት ደርቡሾች ጋር ጠላትነት በመፍጠር ለጎንደር መተማ መውደም (በደርቡሾች መቃጠልና መዘረፍ) እንዲሁም ለራሳቸው ለዮሐንስም ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነ፣ ኢትዮጵያን እርስ በርሱ ተያያዥነት ወዳለው ችግር ውስጥ የከተተ አስጠቂ ውል ነው። ይህንን ውል ተከትሎ እንግሊዝ ምጽዋን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ባለቤት ለሆነችው ለኢትዮጵያ ማስረከብ ሲገባት ለጣሊያን አሳልፋ ሰጠቻት። ጣሊያን ሳትለፋና ሳትደክም እንደ ገና ስጦታ ከእንግሊዝ ከተበረከተላት ከምጽዋ ወደብ በመነሳት ወደ ውስጥ ሃገር ቀስ በቀስ መስፋፋት ጀመረች።

ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ምጽዋ ላይ ስትደራጅ ብሎም ያለማቋረጥ ወደ ውስጥ ስትስፋፋ አንድ ነገር መደረግ አለበት እያሉ ራስ አሉላ በተደጋጋሚ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ ለነበሩት ለአጼ ዮሐንስ ቢያሳስቧቸውም ለቴዎድሮስ ሞትና ለዮሐንስ መንገስ ባለውለታ የሆኑትን እንግሊዞችን ላለማስቀየም እንዲሁም በፈረመት የሂወት ውል ምክንያት ሁለት እጃቸው የታሰረው አጼ ዮሐንስ ምንም ማድረግ አልቻሉም ነበር። በተለይም ራስ አሉላ አንተን አውርዶ መንገስ ይፈልጋል በማለት እንግሊዞች የሚያስወሩትን ወሬ በማመን አሉላን በማግለላቸው የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጣሊያን እየተጠናከረ መጣ፣ ኢትዮጵያም የበለጠ የችግር አረንቋ ውስጥ እየገባች ሄደች።

የጣሊያኖችን የማይቆም መስፋፋት እና የንጉሱን ቸልተኝነት መታገስ ያልቻሉት ራስ አሉላ አባ ነጋ ሰሃቲ እና ዶጋሊ በሚባሉ ቦታዎች ከጣሊያኖች ጋር ጦርነት በማድረግና ወራሪውን በማሸነፍ ለጊዜው የጣሊያንን መስፋፋት የገቱት ቢሆንም ንጉሱ የሃገር ጉዳይነቱን በመተውና አሉላ ለስልጣኔ ያሰጋኛል በሚል መሠረተ ቢስ ጥርጣሬ ያለኔ ፍቃድ ለምን ከጣሊያን ጋር ጦርነት ገጠምክ ወደሚል የግል ተራ ጥል ውስጥ ገቡ። በዚህም የተነሳ ንጉሱ መቀመጫቸውን አስመራ በማድረግ እስከ ምጽዋ ድረስ በመወርወር ጣሊያንን ሲያስጨንቁ የነበሩትን ጀግናውን ራስ አሉላን ከስልጣናቸው በማንሳታቸው የተነሳ በተፈጠረ ክፍተት በመጠቀም ጣሊያኖች ያለከልካይ አስመራ ከተማ ሰተት ብለው መግባት ቻሉ።

አጼ ዮሐንስ የሰሩት ስህተት ለአጼ ምኒልክ እዳ ሆነባቸው። ስለዚህ አጼ ዮሐንስ በሰሩት ስህተት ምኒልክ ምን ያድርጉ? የትግራይ ባላባቶች ከጣሊያን በሚያገኙት አልባሌ የካኪ ሱሪና ኮት የሃገራችንን ጥቅም ለጣሊያን አሳልፈው ሲሰጡና በጥቅማ ጥቅም ሲሞዳሞዱ ጀግናው ምኒሊክ ናቸው ከሸዋ ድረስ ሺ ኪሎ ሜትር ተጉዘው ሄደው አድዋ ላይ ጣሊያንን አሸንፈው ከነጭ ባርነት ትግራይን ነጻ ያወጡት። ለምን በጣሊያን አልተገዛንም ካልሆነ በስተቀርር የሚያመዛዝኑበት ህሊና ካለቸው አጼ ምኒሊክ ለትግራይ ባለውለታ ናቸው። (Dereje Tefera የጻፈውን Bahirdar Press ፌስቡክ ላይ ታትሞ የተገኝ)

Comments

  1. wei gud,men aynet asafari sewoch nachehu,derows ke mengistu zer men yemireba ywetal?

Speak Your Mind

*