ትልቅ ሰው ትልቅን

ይባላል …

ድሮም ይነገራል

ትልቅ ሰው ትልቅን ያስከትላል ሲባል

በፊትም ሰምተናል

ይኸው ዕውነት ሆኖ ሲፈጸም አየን ቃሉ

በነጋሽ ገ/ማርያም፣ በተስፋዬ ሳህሉ

የሐምሌ ወርን የሰላሳ ቀናት እቅፍ

በነኀሴ ተክተን ሳናልፍ

ሁለቱን ታላላቅ የጥበብ ከዋክብት አከታትለን አጣን

የአዛውንቶች ክበብን ዘጋን

ፀጋዬ ገ/መድህን በጻፈው

አባተ መኩሪያ ባዘጋጀው

አውላቸው ደጀኔ፣ ወጋየሁ ንጋቱ በተጫወቱበት

ዓለሙና ሲራክ አብረው በሆኑበት

እነ አስናቀች ወርቁ፣ በላይነሽ አመዴ፣ እነ አባተ መኩሪያ

መላኩ አሻግሬና ዘነበች ታደሰ እነ ሠይፈ አርኣያ

ሙናዬ መንበሩ፣ ኃይማኖት ዓለሙ፣ እነ አስራት አንለይ

በኃይሉ መንገሻ፣ ሱራፌል በጋሻው፣ ያ ፍስሀ በላይ

በተካፈሉበት …

የላይ ቤት ትዕይንት

ተባብረው አብረው አንድ ላይ ሊሰሩት

ነጋሽ ገ/ማርያም፣ ተስፋዬ ሳህሉ፣ እንደ ልማዳቸው አብረው ተሰለፉ

እነሱ ያላዩት አበባ ታቀፉ

ዛሬ ግን ጭብጨባ አልነበረም ከቶ ሳቁንም አልሳቅን

ትልቅ ሰው ትልቅን ያስከትላል ብለን

በሐምሌ ላይ ቆመን

ከሐምሌ ተባብረን …

ጥሬ እንባ አፈሰስን

ለአባባ ተስፋዬና ለሌሎችም በዚህ ላልተካተቱ የጥበብ ሰዎች መታሰቢያ ይሁን!

ወለላዬ

Comments

  1. Guys!!! Abba Abba Tesfaye was a great man who had taught the “Fafa” generation so many things. We all respect his legacy!!!

  2. Yes, he was excellent Ethiopian.

    Unfortunately, we have also these ones:

    https://www.youtube.com/watch?v=ZlCeCmHYRsQ

Speak Your Mind

*