በባንዲራና አርማ ዙርያ ያሉ ውዝግቦች ባይሳ ዋቅ-ወያ

ባንዲራ የአንድ አገር ሕዝብ ማንነት መገለጫ ነው። የሰው ልጆች በታሪካቸው ውስጥ የየራሳቸውን ቡድን ወይም ወገን ከሌሎች ለመለየት ጨርቅን በተለያዩ ቀለሞች በመቀባት፣ እንጨት ላይ ሰክተው በእጃቸው ይዘው በመዞር፣ አንገታቸው ላይ በማሰር ወይም ጎልቶ እንዲታይ ከማሰብ አንጻር ረዘም ባሉ እንጨቶች ላይ እየሰቀሉ ከማንነት መገለጫም ባሻገር ይዞታን ወይም ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ይጠቀሙበት እንደነበር የሕብረተሰብ ታሪኮች መዝግበዋል። ባገራችን ባንዲራ እንደ ኢትዮጵያ መገለጫ ሆኖ መቼ እንደቀረበ በትክክል ባይታወቅም፣ ባንዲራን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ያስተዋወቁት አጼ ምኒልክ መሆናቸው በሰፊው ይነገራል። ያኔ ትክክለኛ ስሙ “ሰንደቅ ዓላማ” በመባል ቢታወቅም፣ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ከወረሩ በኋላ ግን “ባንዲራ” በሚለው የጣሊያንኛ ቃል ተተክቶ ዛሬ በስፋት እየተጠቀምንበት ነው። (በዚህ ጹፌም ይህንን ሳንወድ በግድ ተጭኖብን ዛሬ የአማርኛ ቋንቋችን አካል የሆነውን “ባንዲራ” የሚለውን አባባል በተደጋጋሚ እጠቀማለሁ)። ይህ ጽሁፌ የሚያተኩረው፣ ከአገርና ከማንነት ጋር ስለ ተያያዘው ባንዲራ ላይ ብቻ ነው።

(ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Speak Your Mind

*