ኢትዮጵያ በ2032

የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገር አቀፍ የውይይት መድረኩን በፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን እና ዴስትኒ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ ናቸው በጋራ ያዘጋጁት።

በመድረኩ ላይም የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የበርካታ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮችም በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።

መድረኩ የሀገሪቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማቀራረብ የወደፊት የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት በማለም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችም፤ በመድረኩ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ፤ አሁንም ለኢትዮጵያ በርትተው እንዲሰሩ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮቹ ከዚህ ቀደም በዚህ መድረክ ስር በጋራ በነበራቸው ቆይታ ስለ ሀገሪቱ ፖለቲካ በስፋት መምከራቸውን እና በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮች በውይይት ብቻ የሚፈቱ እንደሆኑ ከመግባባት መድረሳቸውን አስታውቅዋል።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ መድረኩ በሀገር ጉዳይ ሁሉም በንግግር የሚፈታ መሆኑን ልምድ የተገኘበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአብን ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፥ መድረኩ የተራራቀ አቋም ያላቸው የፖለቲካ ሀይሎችን ያቀራረበ መሆኑን ተናግረዋል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ምንም አይነት የተራራቀ የአቋም ልዩነት ቢኖርም፤ በመቀራረብ እና በመወያየት የማይፈታ ነገር እንደሌለ ያስተማረ መድረክ መሆኑን ተቅሰዋል።

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳም፥ “መድረኩ መጀመሪያ ሲጀመር ውጤቱ ላይ ጥርጣሬ ነበረኝ፤ ወደ ስራ ስገባ ግን ቀስ በቀስ በመነጋገር፣ በመወያየትና በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ መፈለግ እንደሚቻል ልምድ ያገኘሁበት ነው” ብለዋል።

የአዴፓ ተወካይ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፥ “በመድረኩ በጋራ በመሆን ሀገርን፣ የዴሞክራሲ ስርዓትን፣ መንግስትን እና ኢኮኖሚን መገንባት እንደሚቻል አረጋግጫለሁ” ብለዋል።

የሀገር ሽማግሌ ተወካዮችም በመድረኩ ላይ መድረኩ ለኢትዮጵያ መፃኢ እድል በር የሚከፍት መሆኑን በመግለጽ፤ ለኢትዮጵያ ስንል ሁላችንም ዝቅ ብለን እንስራ ሲሉ መናገራቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በመድረኩ ላይም ከ50 በላይ የተቋማት መሪዎች በኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉም ነው የተገለፀው። (ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ)

Comments

  1. በኔ ግምት ሰው ለውይይት ሲተጋ የመጀመሪያ ጥረቱ መሆን ያለበት ለውይይት መክንያት የሆነውን ችገር አንጥሮ በማውጣት፤ የውይይቱ ተሳታፊ በሙሉ ነጥሮ በወጣው ችግር ላይ መስማማት ያስፈልጋቸዋል። ችግሮች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ችግሮች ባንድ ጊዜ ባንድ መንገድ ይፈታሉ ማለትም አይደለም። ነገር ገን ከችግሮቹ ውስጥ መጀመሪአ መፈታት ያለበት የቱ ነው በማለት ችግሮቹን በቅደም ተከተል ዘርዝሮ ማስቀምት ያስፈልጋል። እስካሁን ባየሁዋቸው ውይይቶች ላይ ኡሉ እንዳቸውም በጋራ የትስማሙበትን ችግር አንጥረው አውጥተው ከፊታቸው በማስቀመጥ አይደለም በእውነት እንነጋግር ካልን ውይይት የሚያልቀው ላልታውቅ ችግር መፍትሄ በማፈላለግ ጊዜው የሚያልቀው። ምሳሌ ኮሌጆ ትማሪዎችን ጉዳይ በንውሰ ካማራ አገር የመጣው ተማር ለምን ኦርሞ አገር ይገደላል? ከአኦሮሞ ኧርስ የመጣው ተማሪ ለምን አማራ አገር ይገደላል ለሚለው ጥያቄ ተስብስበው የነብሩ ሊሂቃን ምክንያቱን አንትሮ አውጥቶ ከማውጣትና ለዚያ መፍትሄ ከምውፈለግ ይልቅ፤ ወላጆች ልጆቻችሁን ምከሩ፤ ተማሪዎችም ተምራችሁ ትልቅ ስው እንድትሁኑ ትምሕርታችሁን አጠናክሩ … ውዘት ንው። ጥያቄው ታድያ በርግጥ ተማሪዎቸ ትምህርታቸውን አለማጥናከራችው ነው የግድያው ክንያት? ዝውላጆቸ ልጆቻቸው አለመምከርም ምክንያት መሆኑ እንዴት ታወቀ?

Speak Your Mind

*