የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች

(ቀጭኑ ዘ-ቄራ )

“በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም።

እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው ከተንበሪውን የሚያስከፍቱ ደንበኞች ብቻ ናቸው። “ደንበኞች” ስል እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።

ሮዚና ወገቧ ሸንቃጣ፣ አንጀት የሚባል ነገር ያልሰራባት፣ ዳሌዋ ሰፊና ክብ፣ ሽክ ያለች፣ አንገቷ ውድ ነገሮች የሚቀመጡበት፣ ሽታዋ የሚያውድ፣ ዓይነ ርግቧ በቀለም እንደ ስዕል የሚዋብ፣ ሳሳ ያለ ልብስ የምትለብስ፣ እንግዳዎቿን በምትዘጋባቸው ቤት እየተዘዋወረች የምትቀበል አራዳ ነች። አስተናጋጆቿ በጣም ትንንሽ ልጆች ሲሆኑ ጸሃይ አይነካቸውም። ስራቸው ለሮዚና እንግዶች መስተንግዶ ሳይስተጓጎል መስጠት ነው – የሚጠጣ  ያቀርባሉ፤ ፍም እሳት አዘጋጅተው ቡና ያፈላሉ፤ ለማሟሟቂያ የቡናው ስነ ስርዓት በየክፍሎቹ ከተከናወነ በኋላ የጫቱ ሙቀት እየጨመረ ሲሄድ ሺሻ ይለኮሳል። ህጻናቱ ሺሻ እያሞቁ ደንበኞቹን ለማስተናገድ ከቡና ማፍያው በርጩማ ተነስተው ፍራሹ ላይ ሲወርዱ ከአባታቸው ጋር በሰንበት የሚጫወቱ እንጂ የስራ ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ጫት እየቀነጠሱ፣ ሺሻ እያሞቁ ደንበኛቸውን ባፍ ባፉ መከደም ዋና ስራቸው ስለሆነ ተክነውበታል።

ተጋብዤ የተመለከትኩት ክፍል የነበረችው ልጅ ሪታ ትባላለች። ንግግሯ የቀምጣላ ልጆች አይነት ነው። ስትስቅ አማርኛ አይመስልም። ጠይም ቀለሟ የጸዳ፣ ለጋ ነች። እንደ ጋባዤ አገላለጽ “ጥፍሯ ይበላል”፤ ዕድሜዋ ከአስራ አምስት አይበልጥም። ቡና እንደጨረሰች ስስ ነገር ለብሳ ደንበኛዬ ጎን ቁብ አለች። መቃም ትችልበታለች። ጫት ላኪዎች በትዕዛዝ የሚልኩትን ጫት ትጠጣዋለች። ያለ ምንም ማጋነን የቅጠል አበላሏን ፍየል ብታየው በቅናት ምላሷን ትቆርጠዋለች። ምን አደከማችሁ ቅማ ታቃቅማለች። አልፎ አልፎ ሮዚና ለጉብኝት ብቅ ብላ ስትመለስ ቤቱን ታውደዋለች።

ምርቃናው ሲጨምር ወዳጄ ቀስ በቀስ ከልጅቷ ጋር ተጣበቀ። እጆቹም ሁለመናውም እሷ ላይ ሆነ። በቃ ደረቱ ላይ ጣላት። ደረቱ ላይ አንጋሏት ሺሻውን ይምጋል። ብቸኝነቱ ሊውጠኝ ሲደርስ መሄድ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ። ፒኮክ እንደምጠብቀው ነገርኩትና ተለየሁት። ህጻኗን ልጅ ደረቱ ላይ አንጋሏት ስመለከት ልጄን አቅፌ ሳስገሳው ትዝ አለኝ። የሚያስገሳት እንጂ የሚዳራት አይመስልም። እንዲህ ያሉትን ትውልድ አምካኝ ቤቶች ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪና ህግ አወጪዎቹ በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደማሉ። ዝግ ቤቶች…

ፒኮክ አፕሬቲቩ ይጥማል። በጫት የጦዙ ማገዶ ላለመጨረስ አፕሬቲቭ ይወጋሉ። መኪና ውስጥ ሆነው የተጣመዱም ይወጋሉ። “ያራዳ ልጅ” በማለት ሳንቲም የሚለምኑ፣ ሎተሪ የሚያዞሩ የጎጃም ጉብሎች፣ የመንገድ ላይ ነዋሪዎች፣ ቀበሌና አድራሻ የሌላቸው ወንድምና እህቶች፣ ኑሮ ያዞራቸው የኑሮ ሰለባዎች ይታያሉ። አዲስ አበባ ሁሉን ተሸክማ  እየመሸላት ይነጋል።

አፕሬቲቬን እየቀነደብኩ ስለ ሮዚ ቤት እያሰብኩ ቆዘምኩ። ቤቱ ውስጥ ያሉት ህጻናት የተመረጡ ናቸው። መልምሎ የሚያመጣቸውና ስልጠና የሚሰጣቸው አለ። በህጻንነታቸው ተከትበው ሺሻ ስር ሲርመጠመጡ  በዛው ሱስ ይዟቸው ገደል የከተታቸው፣ ኖረውም ተስፋ ያጡ፣ ታመው የፈረደባት እናት እጅ የወደቁ አሉ። አገሩ እንዲህ ሆኗል። የኢትዮጵያ ህዳሴና የኢኮኖሚ እድገት ያተረፈው እንዲህ ያሉትን ዜጎች ነው። በርግጥ አገሪቱ ኢኮኖሚዋ አድጓል። ያደገው ግን ለዝግ ቤት ተጠቃሚዎች እንጂ ለሌሎች አይመስልም። እድገቱ የሚታያቸው በዝግ ቤትና ቤታቸውን ለሌሎች ዘግተው አገሪቱን እያለቡ ላሉት ይመስላል።

በሃሳብ እየቀባጠርኩ፣ አፕሬቲቬን እየሳብኩ ቆየሁ። ወዳጄ ተመችቶታል መሰል አልመለስ አለኝ። ፒኮክ ስለሰለቸኝ ደወልኩለትና እንስራ እንገናኝ አለኝ። ወደ እንስራ አመራሁ። እንስራ ደግሞ ሌላ ትዕይንት አለ።

እንደምን ከረማችሁ… ። አሁን እንስራ ነኝ። እንስራ ለማታውቁ ላስተዋውቃችሁ። እንስራ ቦሌ ቴሌ አካባቢ የሚገኝ የምሽት ንዳድ ቤት ነው። በመለስ ሞት ምክንያት ተፋዞ ከርሞ ነበር። እንስራ ሲገቡ በጡንቸኞች ይዳብሳሉ። ፍተሻ መሆኑ ነው። እንስራ በር ላይ ተዳብሰው ሲዘልቁ ቀለሙ አይን ይወጋል። የደም ጢስ የሚጨስበት ይመስላል። እንስራ ውስጡ በዲጄ ይናጋል፤ ይነዳል። በምድር ቤት ውስጥ የሚደለቀው ሙዚቃ ከተለያዩ አቅጣጫ ከሚፈሰው የተደበላለቀ ቀለም ጋር አንድ ላይ ተዳምሮ የሲኦል ቤተ ሙከራ ይመስላል። መድረኩ ላይ እየተገመዱ የሚላቀቁት ተዋንያኖች እንግዳ ያስደነግጣሉ። ቁመታቸው ረጃጅም የሆኑ እንስቶች የተጠና ዳንስ ይተውናሉ።

እርቃናቸውን ያለ ልብስ የሚናጡት እንስቶች ሃፍረታቸው ላይ የቻይና ማራገቢያ የምትመስል አነፍናፊት ከመለጠፋቸው ውጪ ሁሉም ነገር እንደ አዳምና ሄዋን እንደ ድሮው፣ እንደ ጥንቱ ነው። እርቃን!! ዳንሱ “ብልግና ተኮር” ይባላል። ወገብና መቀመጫን በማላመጥ ሲወዘውዙት ማየት ይመስጣል። “ኮረኮንች” የሚባለው ምንነቱ የማይታወቀውን አልኮል በሉት ዊስኪ እየተጋቱ አብረው የሚያውካኩትን ለተመለከተ አገራችን ውስጥ ችግር በቃል ደረጃም የሚታወቅ አይመስልም።
ከየአቅጣጫው የሚወርደው ባለቀለም ጨረር የሰውነታቸውን ቀለም እንደ እስስት ይቀያይረዋል። እየነደደ ወርዶ የሚቀንሰው ብርሃን ውስጥ ኮሮኮንች ያሳበዳቸው ይዘላሉ። አንዳንዶች መድረኩ ላይ ሳያስቡት ደርሰውበት ዓይናቸውን ከእምብርት በታች ቸክለው ይቅበዘበዛሉ። አንዳንዶች ጥንድ ሆነው መጥተው ብቻቸውን ያሉ ይመስል በሜዳ ላይ ወሲብ መሰል ዳንስ ተማርከው ዓይናቸው ሲቅበዘበዝ አለመስማማት የሚፈጠርበት አጋጣሚ አለ።

ስድስት የሚሆኑት ዳንሰኞች አጎንብሰው መቀመጫቸውን ሲወዘውዙት፣ ተሸብርከው “እንካ፣ አምጣ” ሲሉ፣ ሙዚቃው ሲያቃጥር “የኮረኮንቹ” ኮታ ሳይታወቅ ይበረታል። ከቦሌ አካባቢና ከዩኒቨርሲቲ መንደር የሚዝናኑ መስለው የሚነግዱ በተመሳሳይ ራቁታቸውን ከጊዜያዊ ጓደኞቻቸው ጋር ያስነኩታል። የዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ካነሳሁ አንዴ ወደ አንጋፋው የዝሙት ገበያ ናዝሬት ፔንሲዮን ላምራችሁ።

ናዝሬት ፔኒስዮን እንደ ዛሬው ሳይሆን “ሻሞ” የሚባልበት ለሞት መጣደፊያ አልኮል መቸርቸሪያ ባር ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን አካባቢው የጫት መቃሚያና የድለላ ስራ እምብርት በመሆኑ ሰው ስፍሩ ነው። ናዝሬት ፔንሲዮን በብዛት የንግድ ስራ ኮሌጅ ተማሪዎች እንደሚታደሙበት አንድ ወቅት መረጃዎች በይፋ ተሰራጭተው ነበር።

በተለይ ከክፍለሃገር የሚመጡ ተማሪዎች ከመንግስት የሚሰጣቸው ወርሃዊ ድጎማ ለቀለብና ለማደሪያ ስለማይበቃቸው ናዝሬት ፔንሲዮን ለስራ መሰማራታቸው ያደባባይ ወሬ ነበር። “ይሞታል ወይ?” ያለች ተማሪም ነበረች። ውዱ መሪያችን፣ ነብሳቸውን ይማረውና፣ ስጋቸውን እየሸጡ የሚማሩ ተማሪዎችን አስተዋውቀውናል። እኚህ መሪያችን ናቸው “ልማታዊ ሴቶችን አፈሩ፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት አዘነቡ” የሚባሉት፣ እየተባሉ ያሉት። የኮሜርስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ ሀዋሳና አርባ ምንጭ ችግሩ ያስከተለው ቀውስ ቤተሰብን አንገት ማስደፋት የደረሰበት ደረጃ ደርሷል።

ቤተሰብ ልጄ ተምራ ተመረቀች ብለው ሲጠብቁ አጅሬው የቀሰፋቸው ጥቂት አይደሉም። ሃዋሳ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የቡና ቤት ኮማሪቶች በ”ገበያዬን” ወሰድሽብኝ ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሲገቡ ማየት የተለመደ እንደሆነ ሀዋሳ በነበርኩበት ወቅት ያስተዋልኩትና ያረጋገጥኩት ጉዳይ ነው። አንዴ እኔው ራሴ አብራኝ እንድትጠጣ ለጋበዝኳት ልጅ ይህንን ጥያቄ አቅርቤላት “ገበያችንን ዘጉት” በማለት የስድብ ናዳ እያወረደች ነበር ሁሉንም ያጫወተችኝ – ተማሪዎቹን ማለቷ ነበር። የሴቶች ተሳታፊነት አደገ ይሏል እንዲህ ነው። ነብስ ይማር።

ወደ እንስራ ልመልሳችሁ። እንስራ ጥቂት እንደቆየሁ ወዳጄ ያችኑ ልጅ አንጠልጥሎ መጣ። መጨለጥ ቀጠለ። አስቀድሞም ሲጠጣ ስለቆየ ለመስማት ጊዜ አልወሰደም። እንደውም እንደ አዲስ ጀበና መንተክተክ ጀመረ። ህጻኗን ከፊትለፊቱ ወትፏት በቁሙ እንደውሻ ይቀነዝራል። መብራቱ ስለሚመች ስጋት የለም። በቁሟ በዳንስ እያስመሰለ ፈትጎ ሊገላት ምንም አልቀረም። ይህ ሰው ያለውን ኃላፊነት እዚህ ከሚያደርገው ተግባሩ ጋር በማገናዘብ ሳስበው አመመኝ። እንዲህ ያሉ ብዙ “ትልልቅ ሰዎች” ይመሩናል። በችጋር ይጠብሱናል። ሲሞቱ በደቦ ያስለቀሱናል። በጀት ከልክለው በረሃብ ያቃጥሉናል። ሲሞቱ ደግሞ በጀት መድበው ደረት ያስመቱናል። “ያገራችሁን ህዳሴ ከእኛ ጠብቁ” እያሉ ያለ ሃፍረት ይሰብኩናል። አጽማቸውን እናመልክ ዘንድ ይመኛሉ። ከወዳጄ ጋር የትና እንዴት እንደተገናኘን አስታውቃለሁና ተረጋጉ። አሁን በፈጣሪ እጅ ላይ ሆኖ እየኖረ እንደሆነ፣ ከቤቱም እንደማይወጣ ሰምቻለሁ። ሮዚ አራዳዋ አለች እንዳማረባት። ህጻናቱ ግን … ። ሰላም እንሰንብትና ሳምንት እንገናኝ!!

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. ውድ ጎልጉል እነዚህ አስተያየቶች የኔ አይደሉም። በከረንት አፌር ዌብሳይት ላይ ለተለጠፈው የናንተ ጽሁፍ የተሰጡ አስተያየቶች ናቸው። ከዛ ላይ ቀድቼ በትክክለኛ የጽሁፉ ባለቤቶች ገጽ ላይ ለመለጠፍ ተገደድኩ;
  Askale DamaReply

  September 21, 2012 at 4:00 am

  Golgul,
  I know what I am thinking requires resources on your part. Ethiopia truly appreciates the critical service your are undertaking – the documentation of Woyane crimes. We pray you that sustain the resoutces to systematically catalogue undisclosed woyane crimes in the areas of –
  1. Military killings & genocide
  2. Police & security killings & beating & violations
  3. Security & Intelligence violations and abuses
  4. Political crimes & corruptions
  5. Economic crimes & corruptions
  I say this because there is going to be a turn of events for criminals to be accountable. Ethiopia will need the facts you are so fruitfully uncovering.

  AnonymousReply

  September 20, 2012 at 11:33 pm

  በርግጥም ሁኔታው አሳዛኝ ነው:: ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ ያቀደውና ያለመው ደርሶለታል:: ይኽውም ህዝቡ በሃገሩ እንዳይኮራ ሃገርንና ሰንደቅ አላማን ማንቋሸሽ: በሞራሉ ውድቅ የሆነ ወጣት ማፍራትን: ወጣቱ በተለያየ ሱስ ተይዞ እነርሱን የማያስቸግርበትን መንገድ መፍጠር ; የትምህርት ጥራትን ማውረድ; በዚህም የተነሳ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣቶች ውጭ ሃገር ሄደው እንኳን ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ማሽመድመድ: የጥራት ደረጃውን ያልጠበቀ ሕንጻ በየቦታው በመገንባት ሃገሪቱ በርግጥም እያደገች ናት ማስባል:: እውነታው ግን ከጥቂት ከተሞች በስተቀር አብዛኞቹ የክፍላተ ሃገር ከተሞች በአሉበት እየረገጡ መሆናቸውን ዜጋውን አለማሳወቅ: ሽርሙጥና ሲበዛና ቀሳፊው በሽታ አምራች የሆነውን ወጣት ሲያጠቃ ከሚዲያ ያላለፈ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጥሩንባ መንፋት:: እህቶቻችን በየአረቡ አገር እየተሰቃዩ የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ጆሮ ዳባ ማለት: ብቻ ወያኔ ያፈራረሰውን መልሶ ወደቀድሞ ቦታው ለመመለስ ብዙ አመታት እንደሚፈጅብን ጥርጥር የለውም:: ለወያኔ ምስጋና ይግባውና ወደ18ኛው ክ/ዘመን ተመልሰን የሰውን ስም ጠይቀን የየትኛው ጎሳ አባል እንደሆን የምናሰላበት ጊዜ ደርሰናል:: ይህን ጠላት ታግሎ ለመጣል የሁላችንም ግዴታ ነው:: የ 21 አመታት ጭቆናን በቃ ማለት ያለብን ጊዜው አሁን ነው::

  ZienamarqosReply

  September 20, 2012 at 3:03 pm

  <>:-ይኸን:የመሳሰለውን:መርዶ:እየሰማን:የትግሬ:ወያኔ:በሥልጣን:ላይ:መቀመጡ:እጅግ:በጣም: አሳፍፋሪ:ነው::እንደነዚህ:ያልሉትን:ባላሥልጣኖች:አግኝቶ:ለማነጋገር:ዕድል:ያገኙት:ጸሐፊ:እንዴት:እንዳስቻለዎት: አናውቅም:እንጂ:እኛ:የመቅረብ:አጋጣሚው:ቢገጥመን:የውሻ:መርዝ:እንደ:ምንም:ለመጨመር:አንመለስም:ነበረ:: በተለይ:በዝሙት፣በጫት፡ምርቃናና፡በመጠጥ፡ኃይል፡ለተዳከመ፡አረመኔ።ሆነና!፣ይኸን፡አሳዛኝ፡ድርጊት፡ሰምተን፡ ሀገራችንና፡ሕዝባችንን፡ከዚህ፡አዘቅት፡ለማውጣት፡በኅብረት፡ቆርጠን፡መነሣት፡ይኖርብናል።ለማናቸውም፡ልቦና፡ ሰጥቶ፡እግዚአብሔር፡ያነሣሣን።አሜን።

  mamoReply

  September 20, 2012 at 2:23 pm

  yeadisu amet (2005) mert weyem quter 1 metetef. maxim gorky ena dostoyovisky tez alugn besent ametachew .go go go

  Teddy MenbereReply

  September 20, 2012 at 11:35 am

  በእዉነቱ በጣም በጣም ያሳዝናል .ግን እስከመቸ ድረስ እንዲህ ትዉልድ እና አገር ይጠፋል እኛ ኢትዮጵያኖች ትግላችንና እናቅስቃሲአችንን ከመቸዉም በበለጠ ማፋጠን አለብን.ይህ ጉዳይ ግዜ የምንሰጠዉ ነገር አየደለም.ዎያኔወች እኮ አሁን የመጡብን ባገራችን፣በህየወታችን፣በሃይማኖታችን ፣በማንነታችን …የመሳሰሉት ነዉ .ስለዚህ ክ እስካሁኑ ይበልጥ መደራጀት አለብን.ምንም እነኩአን ስለ ዘረኛዉ እና ሰየጣናዊዉ መንግስት ማንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁልጭ ብሎ እየመጣ ቢሆንም፣አሁንም ቢሆን ግን መሰሪነቱን ያልተረዱ በዉጭአገር ለሚኖሩት ወንድሞቻችን የወያኔን ማንነት ማሳየትና ማስተማር ከሁላችን የሚጠበቅ ነዉ.
  ለምሳሌ እኔ በምኖርብት በጀርመን አገር 6 የሚሆኑ በሰፈሬ የሚኖሩ ወንድሞች ከ አሁን በፊት ከ ተለመደዉ የንሮ እንቅስቃሴ ዉጭ ስለ ሀገራቸዉ ብዙም ትኩረት ሳይሰጡ የነበሩ ወገኖች ነበሩ ነገርግን ምክንያት እየፈጠርኩ በየግዜዉ እንገናኝ እና ስለ አገራችን ጉዳይ እንድንወያይና እንዲሁም በ አሁኑ ሰአት ህዝባችን ላይ ምን በደል እየተፈፀመባት እነደሆንና ወዴትስ እያመራች እነደሆን ማስረጃወችን፣ፅሁፎችን፣ቪዲወችንን እነድናይ እና እንድናመዛዝን እገፋፋቸዉ ነበር. አሁን በሚገርም ሁኔታ ስለ አገራቸዉ ወቅታዊ ሁኔታ በየግዜዉ በመከታተል፣እነደ ESAT ያሉትን የህዝብ አይንና ጀሮ በመደገፍ ፣የወያኔን ስርአት ከስሩ ለመንቀል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አባል በመሆን፣አገርቤት ካሉ ወጣቶች ጋር ሳየቀር ግንኙነት በመፍጠርና information በመለዋወጥ፣ከትግሉ ጋር ተቀላቅለዋል፣፣ እግዚአብሄር ይመስገን !!!

  • be wana ketemachen eyetederegu yalut negeroch asasabi eyehonu memtatachew tekekel new enantem eyakerebachehu yalachehut ewenet new , yehunena ye botawochen sem metkesu yemaytaweku botawochen enditaweku madreg yemeslal , bekerb ke wechi yemeta zemed neger be meta bemagestu ezih bota wesedegn silegne , denegetku keyet semah selew wechi eyalehu semeche new ale yehunena negeroch andaysfafu ketefelege yederejetochen sem batgeltsu dehna neber,

 2. TELL THEM TO HOPE ON GOD YOU SAVE THE LIFE OF NOT ONLY YOUR SISTER ++ OTHERES GO ON SOME TIME YOU NOW YOU ARE FREE YOU LOSE YOUR FREDOM FOR OTHERES UNTILE THE DAY COME BERELEM YEFYEL TEBSE BET TETKAMNEBREKU ENDESZHAYENTE SERA ENDEMISERA ALAWUKEM NEBREGEB

 3. kemerdom merdo egzabher frdun yst!

Speak Your Mind

*