ፌዴሬሽኑ (ESFNA) የጠ/ሚ/ሩን ጥሪ ሊያጸድቅ ነው ውሳኔው “አደገኛ” ነው ተብሏል

የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) በዚህ ዓመት ሰኔ ወር መጨረሻ በዳላስ ከተማ በሚያደርገው 35ኛው የስፖርትና የባህል በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ንግግር እንዲያደርጉ የቀረበለትን ጥሪ ሊያጸድቅ ነው። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ፌዴሬሽኑ ለጠ/ሚ/ሩ ስምና የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ባዶ ቼክ ፈርሞ መስጠት የለበትም፤ ውሳኔው “አደገኛ ነው” ብለውታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ ሥልጣን መንበሩ ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ ለውጦች መኖራቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት እውነታ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በአገር ውስጥ እየተጀመረ ያለው የመግባባት መንፈስ ተደጋፊነት ያለውና መጎልበትም የሚገባውም ነው። በተመሳሳይ በዳያስፖራው ዘንድም እንዲሁ።

ሆኖም ጠቅላዩ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ በዴሞክራሲያዊ አሠራሮች ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አለመደረጉ፤ የፖሊሲ ሃሳብ አለመቅረቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም። በተለይም እስካሁን ያለው ሁኔታ ከቃላት ባለፈ መልኩ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ከማንሳት ጀምሮ በተጨባጭ አንኳር የፖሊሲ ለውጦች የተካሄዱበት ካለመሆኑ አንጻር ፌዴሬሽኑ መድረኩን በመክፈት ለህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፍጆታ እንዲሆን መፍቀድ ነው በማለት የሚሞግቱ ውሳኔውን “ታሪካዊ ስህተት የመፈጸም አደገኛ አካሄድ” ነው ይሉታል።

ከተለያዩ ወገኖች የሚነገረው መረጃ እንደሚጠቁመው ጠቅላዩ በፌዴሬሽኑ የስፖርት ዓመታዊ በዓል ላይ በተለይም “የኢትዮጵያውያን ቀን” በሚባለው ተገኝተው ንግግር እንዲደርጉ ጥያቄ ያቀረበው ህወሓት በ“አምባሳደርነት” ዋሽንግቶን ዲሲ ላይ ያስቀመጠው ካሣ ተክለብርሃን ነው። በመርህ ደረጃ ጥያቄው ስህተት ነው ባይባልም አፈጻጸሙና አወሳሰኑ ግን “አደገኛ ስህተት ነው” የሚሉበትን ምክንያት ያስረዳሉ።

ለ27ዓመታት እንደ ውዳቂ ጨርቅ የተጣለውን ኢትዮጵያዊነትን በመስበክ ሥልጣናቸውን የጀመሩት ዓቢይ አህመድ፤

 • አገሪቱን ወደተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት ሊወስዳት የሚችል ሕዝብ ሰብስቦ “ቃል እንገባለን” ከማለት ያለፈ የፖሊሲ መመሪያም ሆነ ፍኖተ ካርታ እስካሁን አላወጡም፤ የማውጣት ፍንጭም አላሣዩም፤
 • አቶ በቀለ ገርባ እንዳሉት እስረኞችን “በችርቻሮ እንጂ በጅምላ” አልፈቱም፤
  • አሁንም በእስር የሚማቅቁ ሺዎች አሉ
   • አቶ ለማ የሚያስተዳድሩት ኦሮሚያ እንኳን በቅርቡ 7611 እስረኞችን ነጻ ለቋል
  • አሁንም ኢትዮጵውያን በአገር ውስጥና በውጪ (ደቡብ አፍሪካ ነብሮ) በህወሃት ነፍጠኞች ይገደላሉ፤ የአገር ውስጥ እስር አልቆመም
 • የምርጫ ቦርድ ፈርሶ በአዲስ አልተዋቀረም፤ ገለልተኛ ኃላፊ አልመደቡም፤
 • ሚዲያው አሁንም ህወሓት እንደፈለገ የሚያሽከረክረው ነው፤
  • የሚዲያውን “እምቦጭ” ዘርዓይ አስገዶምን በሌላ የህወሃት አጎብዳጅና የዘርዓይ ምክትል ሰሎሞን ተስፋዬ ነው የተኩት
  • አፋኙ የፕሬስ ሕግ አሁንም በሥራ ላይ ነው
  • ነጻ ጋዜጦችና የሚዲያ ውጤቶች ፈቃድ የሚያገኙበት ምንም የተመቻቸ ሜዳ የለም፤ የፖሊሲ ሃሳብም እስካሁን አልቀረበም
 • ከሥልጣናቸው ተነሱ የተባሉት የህወሃት ወንጀለኞች አሁንም በሌሎች ሹመቶች “በነጻነት” እንዲሠሩ እየተደረገ ነው፤
  • ሕዝብን ሲያሸብርና ሲያስር የነበረው ጌታቸው አምባዬ ከጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የጠ/ሚ/ሩ የህግ አማካሪ ሆኖ ተሾሟል
  • የመለስ ሎሌ የነበረችው ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር የዴሞክራሲ ሥርዓት በኢትዮጵያ እንድታስተባብር በሚኒስትር ማዕረግ ተሾማለች፤
  • አስመላሽና አዜብ የሚቴክ ቦርድ አባላት እንዲሆኑ ተሰይመዋል፤
  • ፊት አልባው የደኅንነት ሹም ጌታቸው አሰፋ ቀኝ እጅ የሆነው ያሬድ ዘሪሁን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ተደርጓል፤
  • ዝርዝሩ አያቆምም
 • የኢትዮጵያውያንን የመናገር፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የማሰብ መብትን የሚነፍጉትን አፋኝ ሕጎች – የፀረ አሸባሪነት ሕግ፤ የመያዶች ሕግ፣ የፕሬስ ሕግ፣ ወዘተ እንዲሻሻሉ ወይም እንዲቀየሩ ምንም ያቀረቡት የፖሊሲ ሃሳብ የለም፤
 • በአጠቃላይ የአገሪቱ ክፍል የአማራ ተወላጆችን በተጠናከረ መልኩ የመግደል፣ የማፈናቀልና የማሳደድና ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ በንግግር ደረጃ እንኳን ምንም አልተናገሩበትም፤
 • የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ራፖርተር በኢትዮጵያ ህወሓት የፈጸማቸውን ግድያዎች እንዲጣራ ኃላፊውን ከማነጋገር ያለፈ ለተግባራዊነቱ የተደረገ አንዳችም እንቅስቃሴ የለም፤
 • እነ በረከትና ልደቱ እንደፈለጉ ከሚፈነጩነት መድረክ በስተቀር ሁሉንም ባለጉዳዮች ያሳተፈ የመግባባትና ወደ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ጉዞ የሚወስድ ፍኖተ ካርታ አልተሠራም፤
 • በሌሎች አገራት እንደተካሄደው የብሔራዊ ዕርቅና የእውነት አጣሪ ኮሚሽን መመሥረት አስመልክቶ የእርቅ ሞዴል አልቀረጹም፤
 • ህወሓት አሁንም ደኅንነቱንና መከላከያውን አልለቅም በማለት ነክሶ የራሱ አድርጓል፤ ለወደፊትም መከላከያውን የራሱ የማድረግ ስልት ነድፎ ጨርሷል
 • ከሁሉም በላይ ደግሞ ጠ/ሚ/ሩ ራሳቸውን ጭምር አላሠራ ብሎ አፍኖ የያዛቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ አላደረጉም።

ከዚህ ሌላ ሁለትና ሦስት ሆኖ መንቀሳቀስ ወንጀል በሆነባትና የህወሓት የበላይነት በሰፈነባት አገር ውስጥ ኢትዮጵያውያን ፊት ቀርቦ ንግግር ማድረግ ተገቢ ቢሆን እንኳን ፌዴሬሽኑ ቢያንስ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያቀርብ ይገባል የሚሉም ጥቂቶች አይደሉም። ከዚህ አኳያ አንኳር የሆኑ ሁለት ወይም ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች እስከ ሰኔ ወር መገባደጃ ድረስ የሚፈጸሙ ከሆነ በጊዜያዊነት የጠ/ሚ/ሩን ጥያቄ የመቀበል ውሳኔ ፌዴሬሽኑ ቢያስተላልፍ ሕዝባዊነቱንና አሁንም አይበገሬ ጠንካራነቱን ሊያሳይ ይችላል በማለት ሃሳብ የሚያቀርቡም አሉ።

በህይወት ዘመኑ ዳያስፖራውን ሲያንቋሽሽና “የሲኒ ማዕበል” በማለት እንቅስቃሴውን ሲያበሻቅጥ የኖረው መለስ ዜናዊ ዳያስፖራው ለአገዛዙ የውስጥ እግር እሣት ሆኖበት እንደቆየ ራሳቸው ህወሓቶች የሚመሰክሩት ነው። ከዚህ ዓይነቱ መለሳዊ አስተሳሰብ የራቀ አቋም የያዙት ዓቢይ አህመድ የዳያስፖራውን ጡንጫ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት በውል አስተውለዋል፤ አምነውም በገሃድ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽኑ ውሳኔ “አደገኛ ነው” የሚሉ ወገኖች ምክንያታቸውን ያስረዳሉ።

 • ዳያስፖራው በተጠናከረ ሁኔታ በአሜሪካ የሕግ አውጪ አካል ላይ ተጽዕኖ በማድረግ H.R. 128 በተወካዮች ምክርቤት እንዲያልፍ አድርጓል፤
 • በተለይም ከዚሁ H.R. 128 ረቂቅ ሕግ ጋር በተያያዘ አብሮ የሚደነገገውና የህወሓት ሙሰኞችን እጅግ ያስጨነቀው የማግኒትስኪ ሕግ በዳያስፖራው ጥረት የረቂቁ አንድ አካል እንዲሆን ተደርጓል፤
 • የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ በማፈን የህወሓትን ኮሮጆ አራቁቷል፤
 • ጠ/ሚ/ሩም ይህንን እውነታ አምነዋል፤ ለውጥ እያደረግን ነው በሚል በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገዶች ውጭ ምንዛሪው አፈና እንዲነሳላቸው ጠይቀዋል።

እነዚህን የመሳሰሉ ታላላቅ ተጽዕኖዎች በዳስፖራው እየተካሄዱ ባሉበት ወቅት ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውን በሚገኙበት ቀን ንግግር ማድረጋቸው ህወሓት ለራሱ የፖለቲካ ፍጆታ ይጠቀምበታል ሲሉ ውሳኔውን “አደገኛ ነው” የሚሉ ያስጠነቅቃሉ። ለ27 ዓመታት የህወሓትን አገዛዝ ያለማቋረጥ ሲቃወም የኖረውን ዳያስፖራ ዓቢይ ሲናገሩ የሚገኘውን ጭብጨባና ጩኸት ለአሜሪካና አውሮጳ ሕግ አውጪዎችና ፖለቲከኞች እንደ ግብዓት በማቅረብ “ዳስፖራውና መንግሥት በመቀራረብ እየሠሩ ነው፤ ልዩነቶቻችንን በውይይት ለመፍታት እየተነጋገርን ነው፤ H.R. 128 ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ሕጎች መወሰን አያስፈልጋቸውም፤ …” በማለት እስካሁን የተለፋባቸውን ታላላቅ ተግባራት ሁሉ በቀላሉ በማክሸፍ ህወሓትን ነጻ ማስወጣት የሚቻልበትን መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል ሲሉ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ “አደገኛነት” ያስረዳሉ። ስለዚህ የስፖርት ፌዴሬሽኑ በጠ/ሚ/ሩ ስም ለህወሓት የገንዘብ መጠን ያልተጻፈበት ባዶ ቼክ ፈርሞ መስጠት የለበትም ይላሉ።

የስፖርት ፌዴሬሽኑ ሰኞ ግንቦት 20፤ (ሜይ 28) ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ኢትዮጵያን ወደብ አልባ በማድረግ ሕዝቧን ለ27 ዓመታት በማያባራ ግፍና ውርደት ሲገዛ ለኖረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በመባል ለሚታወቀው የወንበዴዎችና የአሸባሪዎች ቡድን ሌላ ድል እንዳያጎናጽፍ በእጅጉ ተሰግቷል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

 1. ጠ/ሚ አብይ ተገኝተው ንግግር አደረጉና “አደገኛነቱ” ምኑ ላይ ነው?
  ሁሉን ነገር ማጨለም ለምን አስፈለገ?
  መቸ ይሆን የምናድገው?
  ዶ/ር ብርሃኑ ፓርላማውን ሁሉ ካላስረከቡኝ በስተቀር ባሸነፍነው አብላጫ ወንበር
  ብቻ አልሳተፍም አለ፤ ሁሉንም አጣው!
  ዶ/ር አብይ ስለ ኢትዮጵያ አገራችን ከዚህ ቀደም
  አረመኔው መለስ ሲቀልድብን የኖረውን ቀለበሰው።
  እንደ ቴዲ አፍሮ ማለት ነው፤ እንደ በቀለ ገርባ።
  የታሪክ አጋጣሚ ደጋግሞ ለምን ያመልጠናል?
  ጠ/ሚንስትሩን እንስማና ካልተስማማን መተው ነው!
  እኔ የሚመስለኝ የተቃዋሚው ጎራ ህዝቡን በጥላቻ ካልሆነ
  ማስተባበር አይችልምና ነው። ህወሓት/ወያኔን መጥላት ካልሆነ
  ህዝብ አይሰባሰብም። ዶ/ር አብይ የህዝቡን ቀልብ እንዳይስብና
  ያለ አጃቢ እንዳያስቀረን ፈርተን ነው። ምሥጢሩ ይኸው ነው!
  ዶ/ር ብርሃኑ ለምሳሌ፣ ጠ/ሚ አብይ ሰባት ነጥቦችን ካላሟላ አንተባበረውም ብሎናል።
  ባያሟላ ምን ማድረግ ይችላልና ነው የሚደነፋው? ያው ወደ ኢሳይያሱ ጋ መሄድ ካልሆነ።
  ነአምን ቢቢሲ “ሃርድቶክ”ላይ እንዲያውም ለኤርትራ ጥብቅና ቆሞ አላሳፈረውም።
  ባጭሩ፣ ዶ/ር አብይ መጥቶ ንግግር ቢያደርግ ምንም አደገኛነት የለውም።
  የኢትዮጵያ ህዝብ ክዳር ዳር ተገልብጦ መነሳቱ ህወሓትን አስደንግጦታል።
  ስዩም መስፍንን አድምጣችሁታል? ህዝብ ህወሓትን ማየትና መስማት አይፈልግም!!
  ትልቁ የፖለቲካ ድል የተገኘው አሁን ነው። ዶ/ር አብይ እና ገዱ እና ለማ
  ቁም ነገር እንዲሠሩ የህዝብ መነሳሳት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
  ህዝብ ተገልብጦ ቢሰማውና ልቡ ቢወሰድ አደገኛነቱ “መሪዎች” ነን የሚሉትን ሥራፈት ያደርጋቸዋልና ነው!
  ይልቅ ጉልበታችንን ለሌላ ዋነኛ ጉዳይ እናውል። ለምሳሌ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማ ስለ አሰብ ያነሳውን
  በዶ/ሩ አስተባባሪነት ኮሚቴ ተቋቋሞ በዓለም ፍርድ ቤት ፋይል መክፈት ይቻላል። ህወሓት የኢትዮጵያን ጥቅም
  አሳልፎ ሰጥቷል፤ ወንጀል ነው። ህወሓት በመሪዎቹ በኩል ያሸሸውን ንዋይ ለማስመለስ ዘመቻ ሌላኛው ሥራ ነው።
  በዐረብ ምድር ለብዙ እንግልትና በደል ለተጋለጡት ወገኖች፣ ያለ ወላጅ ፈቃድ ህጻናትን ለውጭ አገር የሸጡትን ጉዳይ። ወዘተ።
  ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት ለዘላለም ትኑር!

 2. Abiy is not elected he is selected by woyane
  We need a Prime minister by the people for the people.
  Inviting Dr.Abiy sends a message for the US government to turn around.
  Think about the thousands of youngsters perished by woyane
  Think about the thousands languishing in Tigray jail.
  Think the wealth looted by woyane
  Think about the people of wolkait and others.

 3. መጋበዝ: የለበትም: ባይ: ነኝ:
  ብዙ: ጥሩ ነገር: ሰርቷል: ግን: አስተዳደሩን: ጠልቶ: የወጣ: ህዝብ: መሀል: ምጣቱ: በአገር: ቤት: አሁንም: እየተገረፈ: እየተባረረ: እየተገደለ ያለዉን ኢትዮዽያዊ: መናቅ: ነዉ: የሚመስለኝ: ።ለነገ: የማይባሉ: ነገሮች: አሉ: ።
  እሱ: ታዋቂ መሆንና: ዶላር: የሚያገኝበትን: መንገድ: ነዉ: ያዘዉ: ” ኢሀድግ: ድርጅቴ ” እያለ: እየነገረን: ነዉ: የሚያወራዉ: ካልጠፋ: የክብር: እንግዳ: ኢሀድጉን: ብትጋብዙ: በጣም: አዝናለሁ ።የመናገር: ነፃነት ያለበት: ያለን: ኢትዮዽያዉያን: ይሄን ማድረግ: ከተሳነን: ,,,,,,,

 4. Dear Sir/Madam,
  Where is my comment?
  I put few days a go.
  Is this a social media for ideas?
  Kemakber selamla gar

  የኔ አስተያየት የት ገባ ቅርጫት ውስጥ እንዳማይገባ እርግጠኛ በምን ልሁን እዚህ ካልታየ።
  ከማክበር ሰላምታ ጋር።

  • Ayalew Shebeshi

   We have published what you sent us. We do not withhold comments unless they are derogatory, offensive, expletive, … Even Mulugeta Andargie (የህወሓት በረኸኛ) knows this very well.

   Regards,
   Editor

 5. Selam Editor,
  Thank you, still unable to see my comment for this particular ፌዴሬሽኑ (ESFNA) የጠ/ሚ/ሩን ጥሪ ሊያጸድቅ ነው.

  ከማክበር ሰላምታ ጋር።
  Ayalew

  • Selam Ayalew Shebeshi

   As we have to noted in our previous message, we have posted everything we received regarding this article. We hope that you can see other comments here also.

   If you still have your comment, send it again and we will post it. Again we DO NOT delete any comment just because it disagrees with us.

   Hope this shades some lights.

   Best
   Editor

  • If you are referring to this then you are talking about something different. You sent this comment to this article.

   Thanks
   Editor

 6. የአመታዊውን የአሜሪካ የስፓርት በአል በተለያዩ ግዜ ፈተና መጥቶበት ለመወጣት ችሏል።የአሁኑ ሁኔታ ትንሽም ለየት ቢልም በመሰረቱ አንድ አይነት ፈተና ነው።ከጠቅላይ ምኒስትራችን ጀርባ ብዙ አድሎ ሃይሎች ቢፈታተኗቸውም የአሁኑ ሂደት ተቀልባሽ ባልሆነ ሂደት ተጀምሯል ።ከርሳቸው ጋርም አብረን ወይም ከሌላ የሚመጣ ሐይል ጋር።
  በሌላ ሐገሮች እንዳየነው በስፓርት የተነሳ ኦሎምፒያድ ሆነ ሌላ ዝግጅቶችን እቀባ ይደረግ ሲባል ፓለቲካ እስፓርት ላይ የሚያደርገው ተፅንኦ መቅረት አለበት እየተባለ ብዙ ጊዜ አለምን ሲያወያይ ያለ አርእስት ነው።ስምምነቱም ሁለቱ ሁኔታዎችን መለያየትን አስፈላጊነቱ ታውቆ በዚሁ ረግቷል ።ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ጊዜ ቢሞከርም ።በተለይ ብዙዎቹ የአውሮፓ ሐገራት ፣አንድን የሌላ ሐገር መሪ መጥቶ በሃገራቸው በትልቅ መሰብሰቢያ (እንደ ስታድየም) ያሉ ቦታዎች የፓለቲካ ሂደት እንዲካሄድ በህጋቸው አይፈቅዱም ።ወናው ምክንያት የፀጥታና ሰላም የማስከበር ሁኔታ ነው።ማለትም ሰዎች የሃገራቸው ውጥንቅጥና ጠብ በሀገራቸው እንዲቀጥል አይፈልጉም ።ለዚህ ጀርመን በተቀዳሚ ሊጠቀስ ይችላል ።እኛም ኢትዮጵያን በውጭው አለም ይሄንን ውጥንቅጥ በ70 ና በ80 በአአ አቆጣጠር ጊዜያት በሰፊው ታይቶብናል።
  የአሁኑን ሁኔታ ለይቶ አለማየት ያለፈውን ያስደግማል።ባለፉት የአገዛዝ ዘመናት እንደ ኢሕአዴግ (ህወሓት) ዘመን ክፍፍሉ አልከፋም ነበር።
  ጠቅላይ ምኒስትራሽን ካሰቡበት ህዝባቸውን የትም ሐገር ሄደው ለማነጋገር አመቺ ሁኔታ ሊፈጥሩ ይችላሉ። አለበለዛ እንደ ተረቱ የላሊበላ ሰርግ በሰው ድግስ እንዳይሆን።

Speak Your Mind

*