የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የ EDF አቋም መግለጫ

የኢትዮጵያውያን የውይይትና ምክክር መድረክ (ኢውምመ) (EDF) በአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የተመሰረተ መድረክ ሲሆን በኢትዮጵያ መሰረታዊ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የፖለቲካዊ ችግሮች ዙሪያ ምርምሮችን እያካሄደ ለተፈላጊ ለውጦች የሚታገል ድርጅት ነው። የዚህ ድርጅት አመራር አባላት በቅርቡ በሚንስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም የሚተነትነውን ረቂቅ አዋጅ በጥልቀት ተወያይቶበታል።

ተወያይቶ የሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል በEDF እምነት በመጀመሪያ ደረጃ   በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መሰረታዊ ችግር ከብሄር ፖለቲካ የመነጩ አንዳንድ የህገ መንግስቱ አንቀጾች ናቸው። ለዚህ ለአሁኑ የሚንስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ መነሻውም ይሄው ህገ-መንግስቱ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ   5 ነው። ህገ-መንግስቱ ከብሄር ፖለቲካ አስተሳሰብ በመነጨ የተቀረጸ በመሆኑ መግቢያው ላይ ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች አገር መሆኑዋን ሲገልጽ ለዜግነት ቦታ አልሰጠም። በአንጻሩ የብዙ ዴሞክራት ሃገሮች ለምሳሌ የተባበረችውን አሜሪካንን፣ አውስትሬሊያን፣ ህንድን ብንመለከት “እኛ” በሚል ይጀምራል። የአንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ የተባበረ ማህበረሰብ እንደመሰረቱ በቃል ኪዳናቸው ላይ አስፍረዋል። ይህ መሰረታዊ እምነትና ቃል ኪዳን ለአንድ ሃገር ህልውና በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ፖሊሲዎችና ህጎች ሁሉ ከዚህ ከህገ መንግስቱ የህግ ምንጮች የሚቀዱ በመሆናቸው ህገ መንግስቱ የአንድን ሃገር ህዝብ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ወጥነት ማረጋገጡ ቁልፍ ነገር ነው።

ህገ መንግስቱ የያዛቸው አንዳንድ አንቀጾች በራሳቸው ችግር መሆናቸው ሳያንስ ከነዚህ አንቀጾች የሚቀዳው ህግ ሲመጣ ደግሞ እንዴት አንድነታችንን እኩልነታችንን እንደሚጎዳ የሚንስትሮች ምክር ቤት መግለጫውን ሲያወጣ ተምረናል። የሚንስትሮች ምክር ቤት መግለጫ የኢትዮጵያውያንን መሰረታዊ መብቶች እንደ ልዩ ጥቅም አይቶ አዋጅ ማውጣቱም ሌላ ችግር ሆኖ አይተነዋል። ከሁሉ በላይ ደግሞ አዲስ አበባ ብቻ ሳትሆን ቡድኖች ተሰባስበው የሚኖሩባቸውን የክልል ከተሞች ማለትም እንደነ አዋሳ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላና አንዳንድ ዞኖችም እንዲሁ የልዩ ጥቅም ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ ጉዳይ የሚያመጣው ዋና ችግር የልዩ ጥቅም አስተሳሰብ ሲስተማችንን እስከ ታች ሊያበላሸውና ከእኩልነት ይልቅ በተፈጥሮ ሃብትና ኢኮኖሚ ጉዳዮች የይገባኛል ጥያቄዎችን እየፈጠረ አንድነታችንንና የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄዎቻችንን ያበላሻል። ዛሬ በዚህ በወጣው አዋጅ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሚያዝኑት አዲስ አበባ ኣካባቢ ያለ ገበሬ አይጠቀም ከሚል ሳይሆን የአዋጁ ስሜት ብሄርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ፣ መሰረታዊ የዜጎችን  ጥያቄዎች ከመፍታት  ይልቅ ልዩነትን ለማጉላት  የተጨነቀ ሆኖ ስላዩት ነው።

ዛሬ ኢትዮጵያውያን የቸገራቸው ነገር እንዴት ከድህነት እንደሚወጡ፣ እንዴት ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንደሚያድጉ ነው እንጂ የቀበሌ ስሞች የመቀያየር ጉዳይ አይደለም። የሚንስትሮች ምክር ቤትን ያሳሰበው ጉዳይ በከተሞች መስፋፋት ጊዜ የሚመጣውን ችግር በተመለከ ቢሆን በመላ ሃገሪቱ ወጥነት ባለው ሁኔታ በከተሞች አካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎችን ህይወት በሚመለከት አንድ ወጥ አሰራር ሊፈጥር ይችል ነበር። ነገር ግን መንግስትን ያሳሰበው ጉዳይ ይህ ባለመሆኑ በብሄሮች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጉላት ሲጥር ይታያል። ወጥነት ያለው ኢትዮጵያውያንን በብሄር በሃይማኖት ሳይነጥል የሚንከባከብ ህግ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሞገስ ያገኛል። የመንግስት ስራ ከዚህ ፍጹም ተጻራሪ በመሆኑ መላው የሃገራችን ህዝብ ለተፈላጊ ለውጥ ትግሉን እንዲቀጥል ጥሪ እያደረግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የኢትዮጵያ ለጋሽ ሃገራት ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ ጥብቅ ርምጃ እንዲወስዱና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ እናደርጋለን።

የኢትዮጵያ የውይይትና መፍትሔ መድረክ
9900 GreenbeltRD.E#343 –  Lanham,MD 20706 (መግለጫውን በእንግሊዝኛ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Comments

 1. ተረፈ ታደሰ says:

  አንድ ነን እየተባለ እስከ መቸ እያለቀስን እንኖራለን፡፡ የድሮዎቹ እነምንይልክ እና አጤ ሀይለ ስላሴ መች ከዘረኝነት ፀድተዉ ያዉቃሉና ነዉ ጩሄቱ!! ዛሬ ግን ጊዜዉ ተቀይረዋል፡፡ መሰረታዊዉ ችግር ዛሬ ድረስ ያለዉ የተዛባ አመለካከት ነዉ፡፡ስልጣኔ ያልቀየረዉ፤ ትምህርት ያልቀየረዉ ፤ ባጠቃላይ ጊዜ ያልቄየረዉ አመለካከት!! ስለዚህ ይህን አመለካከታችሁን በማስተካከል ዉይይቱን ብትጀምሩ ትማሩበታላችሁ ባይ ነኝ፡፡

 2. ተረፈ ታደሰ says:

  For me citizen ship should come after realizing am free or under colony. I personally should not tolerate the concept of citizenship if i am still underneath of someones’ feet in the name of citizenship. I am Wolaitta and Wolaitta first. I don’t care about my citizen ship if I were already lost somewhere my identity. My personal identity should be respected first. Ethiopia (if there is, today) should be a country of tolerance and respect. No tolerance and respect mean no more peace, and security as well as development that prevails. I must respect the rights of minorities as well as diversities. The number or population size should not be a pride of any ethnic group in Ethiopia. A population size that supposed to be large as compared to others that you belongs to should not be your cause of pride. Your pride should be your own personality. You can be of a person of integrity, diligence, compassion, and vision. You can be a person of tolerance, hard working, friendliness, and so on. Paul Kaggame once said “no people compared to others weak, or so but your countries size be”. Thus, size has no significant effect on your personality or on your well being rather your good qualities like integrity, friendliness, communication, compassion, respect and tolerance to diversities. Diversity can’t and won’t be destroyed in any ways and any times. You should respect diversity but tolerate and further equality between you and others. No special person in this globe. No special clan or nationality or nation. All come from the same ancestors. Same family! Democratic and human rights should be judged with justices. Justice must be the center of all governmental functions. Political parties too should not be an exception. Our attitude toward diversity should be corrected soon otherwise no more improvement will be happen.

 3. Guys!!! As I understand, the ministers passed a big and historical bill in order to make the country united. The Parliament asked or gave a chance to be discussed and digested. In my part, the discussion should be given to Oromyia Government. The Oromyia Government has right and responsible to manage it. For instance, the Amhara and Tigrai regional Governments made their own state without anyone interference. In this case, this chance should be delivered and encouraged to a very beneficial way to Oromo people. Because, the city is in the middle of the regional Government.

 4. Tadesse says:

  When people lived in Addis Abeba,all you care was if you speak Amharic,I had friends of Oromo parents,they weren’t ashamed to say or tell this but they were also full of respect to what was going in the city.I am a tigrian who grew up in the 1950s and when I was to Mekelle in 1996,i was shocked how small the grain was/eshet in Amharic and shewit in Tigrigna,who care about the name of a land there while nature is deteriorating,I am an Ethiopian again and again.

 5. Tadesse says:

  I am sorry for my anger,some moslim Oromos,insult Ethiopia and all about Ethiopia,the amharans and every,the heroic amharans sent lemesmatu yemikef.

 6. Tadesse says:

  Like Gonder was built by foreigners.

 7. Tadesse says:

  Egziabher yefaredachew,lela men yebalal.Ye Ethiopia Egziabher.

 8. Tadesse says:

  Ye Egziabher lijoch slehonu ende teraw sew becha yefetenalu belo maseb yewahnet new/sle Israelawian yetebale.

 9. aradw says:

  የኦሮሞን ጉዳይ ለኦሮም ተወት ኣርጉት። ለቀቅ ኣርጉት ። የህ ጉዳይ ፊንፊኔን ወዳ ባለበቷ ኦሮሞ የመመለስ ጉዳይ ነው። የህ ደግሞ ማንንም ኣይጎዳም። ጥቅሙ ግን ለቡዙሃን ነዉ። መሁራኖችም አስተምሩ ተመራመሩ ዘፋኞችም ዘምሩ ዝፋኑ ብር ሰብሰቡ ።

 10. telala says:

  terei yalegizesh new yeteweledeshiw meweled yalebsh be 1800 wochu akabai neber. Gizena alem telosh hedual. neqa bey wolaitawochen atasedbi. wolaitanet yerasesh new betifelegim lalemehon aticheym. selezih wolaita first minamin yemityewen neger tewet argesh wedefit terameji. aemeroshenem kefet arigw gizew yeneged mehonu kertual. yegimel shint athugn.
  Mulei astesasebish lela new gen min yadergal chinqilatesh ayseram yezorebesh nesh beolf propaganda.
  Ardawm endezihu demo manew leoromo teqorqari yaderegeh. kemelekiaw rak bel metet nalahen nektotal

Speak Your Mind

*