ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ ይባላሉ፤ በቦረና ዞን የዲሎ ወረዳ ቃዲም ኦላ ጫጩ ገልገሎ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ወ/ሮ ጂሎ ጃተኒ የዱር እንስሳት የሆነውን ነብርን በማላመድ አብራቸው እየኖረ ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ ጂሎ በዞኑ ድርቅ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ለከብቶች ሳር ለመፈለግ ወደ ዱር ባቀኑበት ጊዜ የነብር ግልገል ማግኘታቸውን ይናገራል። ወይዘሮዋ ግልገሏን እነርሱ የሚመገቡትን ምግብ በመመገብ እንዳሰደጉትና አሁን ላይ ተላምዶ ከፍየሎችና ህፃናት ጋር እያደገ ነው ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ነብርን ያላመዱ እናት
Social
ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የሠራ ወጣት
በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ሥራዎች የሚታወቅ ወጣት ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰራ። በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ስራዎች የሚታወቅ ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያ 360° ዞር መምታት የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰርቶ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ እና የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በተገኙበት ለእይታ አቅርቧል። ሮኬቱ ከስድስት እስከ 10 ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል መሆኑን ወጣት ዘካሪያ በመገለጽ በአንዴ አራት ቀላዮችን የሚይዝና መወንጨፍ የሚችል ሮኬት መሰራቱን ገልጸዋል። ያለሰው ንክኪ በራሱ ማዘዣ 360° ዲግሪ በመዞር በአየር ክልል የሚንቀሳቀስና ጥሶ የሚገባ የጠላት ዒላማን መምታት የሚችል ሮኬት መሆኑንም አስታውቆ ቦታው ከተመቻቸ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የተሳካ … [Read more...] about ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የሠራ ወጣት
በኢትዮጵያ ካሉ 47 ሺህ ት/ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራት ብቻ ናቸው
በኢትዮጵያ ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “ከፍተኛ” የሚባለውን ደረጃ ያሟሉ፤ አራት ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ካሉ 47 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራቱ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ወላጆች፣ የቀድሞ ተማሪዎች እና መምህራንን የሚያሳትፍ፤ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ሀገር አቀፍ የትምህርት ዘመቻ በአንድ ወር ተኩል ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 15፤ 2015 በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው። ሪፖርቱን ለፓርላማ አባላት ያቀረቡት … [Read more...] about በኢትዮጵያ ካሉ 47 ሺህ ት/ቤቶች ውስጥ ተፈላጊውን “ከፍተኛ ደረጃ” የሚያሟሉት አራት ብቻ ናቸው
በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
ጦርነት ባሕላችን ነው፣ ተራራ ያንቀጠቀጠ ትውልድ፣ ወዘተ በሚሉ ባዶ ዲስኩሮችና ከንቱ ልፈፋዎች ትውልድን በስሁት ትርክት ሲነዳ የኖረው ትህነግ የሚፈራው ጥያቄ እየቀረበለት ነው። "ልጆቻችን የት ናቸው?" "ልጆቻችንን መልሰን ማግኘት እንፈልጋለን" ወዘተ የሚሉ የወላጆች ጥያቄ በትግራይ እየተሰማ ነው። አቶ ገብረመስቀል አበበ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ “ከአንድ ቤት አንድ ሰው ወደ ጦርነት መግባት አለበት፣ ካልሆነ እርዳታ አይሰጠውሙ” በተባለ ጊዜ አንዱ ልጃቸው በግዳጅ ወደ ውጊያ ማምራቱን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነግረውናል። አሁን በተደረሰው ስምምነት መሰረት “ልጄ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ በሀዘንና በተስፋ እገኛለሁ” የሚሉት አቶ ገብረመስቀል ልብ በሚሰብር ሁኔታ እያለቀሱ ልጄ ካለ መንግስት ምላሽ ይስጠኝ ሲሉ … [Read more...] about በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው
“የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮችን በመቀበሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ። በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ዓመት በላይ በመጠለያ ጣብያ የቆዩ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን እስከአሁን ድረስ የደብረብርሃን ከተማ ህዝብና ከአንዳንድ ድርጅቶች ውጭ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው ባለመሆኑ ለችግር በመጋለጣቸውን ተፈናቅዮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል። በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሄር በተለይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰዎች ተጠግተውና ቤት ተከራይተው የሚኖሩትን ሳይጨምር ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በ6 መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች … [Read more...] about “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል
አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ … [Read more...] about አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ
ሕጉ ምን ይዟል ? ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው (LGBTQ+) ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ የረጅም ጊዜ እስር ይጠብቀዋል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ፣ በቤተሰብ ደረጃ ያስጠለለ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል። በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል። "በተመሳሳይ ጸታ መብት" ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት … [Read more...] about የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ
በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም
ከቀናት በኋላ በሚካሄደው ሮም ማራቶን ኢትዮጵያዊው ሯጭ በባዶ እግሩ በመሮጥ ታሪክ ሊደግም ነው። የፊታችን እሁድ የ2023 በሚካሄደው የሮም ማራቶን ኢትዮጵያዊው የባዶ እግር ሯጭ እንዲሁም ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ቁልፍ ሰው (ዳይሬክተር) በመሆን የሰራው የ45 ዓመቱ ኤርሚያስ አየለ ሙሉ ማራቶን በባዶ እግሩ በመሮጥ የታላቁን አትሌት አበበ ቢቂላን ታሪክ ሊደግም ይችላል እየተባለ ነው። ኤርሚያስ ከዚህ ቀደም የታላቁ ሩጫንና የሀዋሳ ግማሽ ማራቶንን በባዶ እግሩ የሮጠ ሲሆን ይህንን የሚያደርገውም ለኢትዮጵያው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ክብር እንዲሁም ለሀገር ገፅታ ግንባታ ሲል መሆኑን ተናግሯል። የሮም ውድድሩ ቀላል እንደማይሆንና ስሜታዊም የሚያደርግ እንደሆነ የገለፀው ኤርሚያስ "ይህን ትልቅ ትርጉም ያለውና ታሪካዊ ውድድር ለማድረግ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ" … [Read more...] about በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም
“አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ
በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጣችው የኒጀር ዜግነት ያላት የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኪታ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም በማድረግ አፍሪካዊያንም እንዲያውቁት ማድረግ ይገባል ብላለች። ባለሙያዋ የፍራንኮ አፍሪካን ፊልም አዋርድን አሸንፋለች። በሥራዎቿ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥታለች። የፊልም ጸሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ራህማቶ ኪታ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲኾን በአደባባይ ጥረት የጀመረችው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በማነጋገር መኾኑን አብራርታለች። በቅርቡም ይፋዊ ደብዳቤዋን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት መሥጠቷን አብራርታለች። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የታየላት "የጋብቻ ቀለበቱ" የተሰኘው ፊልሟ በፊልሙ ዕይታ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳታፊዎችን … [Read more...] about “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ
አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ
የኢትዮጵያን ፊደል አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ አሃጉር ፊደል ይደረግ ዘመቻ መጀመሪያ በግሪጎሪያን 1989, በየሐረርወርቅ (የኢትዮጵያወርቅ) ጋሻው መስራችነት ተጀመረ። ይህንን ትልቅ ዓላማዋን በጽናት ይዛ ግቧን ለመምታት እነሆ በይፋ በ1990 (ግጎ) ለአፍሪካ መሪዎች በነብስ ወከፍ በማስተዋወቅ ብሎም ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት አሁን የአፍሪካ ኅብረት ጭምር ካስተዋወቀችበት ጊዜ ጀምሮ አንድቀን ሳታቋርጥ ቀጥላበት እነሆ በጉዳዩ ጸንታ እስከዛሬ በመታገል ላይ ትገኛለች። ከተነሳችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ እንቅፋቶች በትሕነግ መሪ በመለስ ዜናዊና በግብረ አበሮቹ ጅምሯን ለማኮላሸት የተፈጸሙ ችግሮች ቢያጋጥሟትም፣ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ወደኋላ ሳትል ሌሎች አፍሪካውያንን ጭምር በማስተባበር እየታገለች ትገኛለች። ለዚህም አንዱ ይሄ የስም ፊርማ ዘመቻን ጀምራ ለዚህ ዓላማ ይጠቅማሉ … [Read more...] about አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ