“ባለፉት 50 ዓመታት የተከሰቱት ጦርነቶች የተጀመሩት ሚዲያው ባስተጋባው ውሸት መሆኑን ደርሼበታለሁ” ጁሊያን አሳንዥ፤ የዊኪሊክስ መሥራች። የአገራችን ሚዲያ አውታሮች በተለይም የግሉ ሚዲያ የሚባሉትና በ1997 ምርጫ ወቅት የነበሩት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲቀጭጭ፣ የሃሳብ ልዩነት እንዳያድግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ጉያ ሥር ገብተው የፈጸሙት ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው። ለቀጣዩ ትውልድ መማሪያ ይሆን ዘንድ በወጉ ተጠንቶና ተሰንዶ ሊቀመጥ ይገባል። ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲከሰት ያየነው ፖለቲካው ወይም ፓርቲዎች ሚዲያውን አጀንዳ እያስያዙ ሲመሩት ይቆዩና በኋላ ፖለቲከኞቹ እርስበርስ ሽኩቻ ውስጥ ሲወድቁ የሚፈልጉትን ለማጥቃት ወይም በሐሰት ለመወንጀልና ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ሲሉ ለሚዲያ ባለቤቶቹ ባሪያና ተገዢ በመሆን እነርሱ ሚዲያውን መምራት ሲገባቸው … [Read more...] about ቀጣዩ የዳያስፖራ ፖለቲካና የሚዲያው አሰላለፍ
Politics
የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ማረጋገጫ ሰጠ
* በ“ጋዜጠኛነት” ስም የሚፈጸመው የሚዲያ ሸፍጥ በትግራይ ክልል "ከ200 በላይ ኢንዱስትሪዎች ሥራ ጀምረዋል" በሚል ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ሪፖርት "ከእውነት የራቀ ነው" ሲሉ የከሰሱት የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ 212 ኢንዱስትሪዎች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ሥራ እንዲጀመሩ ክስ ባቀረቡበት ዜና ጎን ለጎን አስታወቁ። ዜናው የክስ ሳይሆን አሃዱና ቲክቫህ በቅብብሎሽ አንዱ ሌላውን ዋቢ አድርገው ባሰራጩት ዜና መግቢያና ርዕስ ቀዳሚ ያደረጉት "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፓርላማ ያቀረቡት ሪፖርት ከዕውነት የራቀ ነው" በሚል ነው። ዜናው በመሪ ርዕሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የቀረበውን ክስ አላብራራም፣ እርሳቸው ካሉት ጋርም አላነጻጸረም። የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መሐሪ ገብረሚካኤል "በአሁኑ ወቅት በክልሉ ሥራ የጀመሩት ለትላልቅ … [Read more...] about የትግራይ ኢንዱስትሪ ቢሮ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ማረጋገጫ ሰጠ
ትህነግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂደውን ሽብር እንደሚቀጥል አስታወቀ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትሕነግ) በማለት ራሱን የሚጠራው ቡድን በዓለምአቀፉ የአሸባሪ ቋት ተመዝግቦ የሚገኘው የወንበዴዎች ስብስብ ነው። ከስድሳ ቀናት በላይ ስብሰባ ተቀምጦ የነበረው ትህነግ የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሚገባው አልተተገበረም በሚል በመንግሥት ላይ የተቃውሞ መግለጫ አውጥቶ ነበር። በቀጣይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በጥር 23 ቀን 2016 ዓም ለትሕነግ መግለጫ አጸፋ ምላሽ የሰጠ ሲሆን በዋነኝነት ስምምነቱን ለመተግበር መንግሥት እንዴት ከሚገባው በላይ ርቀት እንደሄደ የጠቆመ ነበር። እንደ ማሳያም ከስምምነቱ ወዲህ መንግሥት ለትግራይ ክልል ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገልጾዋል። ለዚህ የመንግሥት ምላሽ ትሕነግ የአጸፋ ምላሽ ሰኞ የሰጠ ሲሆን ለክልሉ የተደረገውን 37 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ምንም ዓይነት ዕውቅና ሳይሰጥ የፕሪቶሪያው … [Read more...] about ትህነግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያካሂደውን ሽብር እንደሚቀጥል አስታወቀ
የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ለማምከን በሶማሊያ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ
ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲ እና በሌሎችም ዘመቻዎች የምትከተለውን ስትራቴጂ የተመለከተው ሰነድ ሚስጥራዊ ማስታወሻ ለ፡ ሐሰን ሼክ ሞሃሙ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት A confidential Memorandum To: HE. Hassan Sheikh Mohamoud President of the Somali Federal Republic ከ፡ ሙክታር አይናሼ፣ የሶማሊያ መንግሰት የፀጥታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝና አማካሪ፣ የሶማሊያ ዜጋ --ግልባጭ፡ -ሃምዛ ባሬ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር -አብዲ ሃሺ አብዱላሂ፣ የላዕላይ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ -አደም መሀመድ ኑር ማዶቤ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፤ እና -ለሁሉም የፌዴራል አባል ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ቀን፡ … [Read more...] about የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ለማምከን በሶማሊያ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ
የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ
በ116ኛው የሠራዊት ቀን ሲከበር ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበትን ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እንዲከበር ተደርጓል” በማለት ቀኑ ለምን እንደተመረጠ ይፋ አደረጉ። ከዚህ ሌላ ፊልድ ማርሻሉ በንግግራቸው፤ ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ከጀግኖች የተረከብናትን ኢትዮጵያ እንደተከበረች እና ማንነቷ እንደተጠበቀ ለማስቀጠል ወታደራዊ ዝግጁነታችንን አሳድገንና ቁመናችንን አዘምነን ማንኛውንም ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመፈጸም ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አሣውቀዋል። የሠራዊቱ አባላት የተሠጣቸውን ታላቅ አደራ በድል ለመወጣት የመፈጸም ብቃታቸውን በማሣደግ በዓላማ ጽናታቸው እንዲቀጥሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳስበዋል፡፡ ሠራዊቱ ሀገሩን እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን … [Read more...] about የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ
ጥቅምት 15 ለምን?
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአዲስ መልክ ጥቅምት 15 ቀን ላይ መከበሩ ለምን እንደሆነ ከዚህ በታች ለመረዳት እንዲቻል በቀላሉ የተሠራውን መግለጫ ይመልከቱ። ስለ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የማዕረግ ምልክቶች ምን ያህል ያውቃሉ? ከ"ፊልድ ማርሻል ጄነራል" ጀምሮ እስከ "ምክትል አስር ዓለቃ" ድረስ በአጠቃላይ 18 ማዕረጎች ይገኛሉ። የማዕረጎቹን ዝርዝር ከነምልክቱ እነሆ፦ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ጥቅምት 15 ለምን?
“በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”
"በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት " በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮ ለ116ኛው የሠራዊት ቀን እንኳን በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ የረዥም ዓመታት ሀገርን ከጠላት የመከላከል የተጋድሎ ታሪክ ካላቸው ሀገራት መካከል በጀግኖች ልጆቿ የአይበገሬነት ፊት የምትሠለፍ ታሪካዊት ሀገር ናት። ከቀደመው ዘመን ጀምረን አሁን ላይ ያለውን እውነታ እንኳ ብንቃኝ ኢትዮጵያ በርካታ የውጪ ወራሪ ሀገራት ያሠፈሠፉባት ጥቂት የማይባሉ የውስጥ እርስ በርስ ግጭቶች የተከሰቱባት በባንዳዎች የተፈተነችበትና በየትኛውም ዘመን ያልተንበረከከች የወራሪዎችን ፈተና አልፋ ዛሬ ላይ የደረሠች ሥለመሆኗ የታሪክ ድርሳናት መዝግቧል። በሀገራችን የጀግንነት የታሪክ መዝገብ ያልሠፈሩ ግን ደግሞ አለም ያወቃቸው ቱባ ባህሎችና ድንቅ ታሪኮች ያላት ኢትዮጵያ በታሪክ … [Read more...] about “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት”
ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው
በጦር መሣሪያ ንግድ፣ በኮንትሮባንድ፣ በዝርፊያ፣ ጦር በማደራጀትና በከፍተኛ ዕዳ የተዘፈቁት አቶ ወርቁ አይተነው ከአምስት ወር በፊት አገር ለቀው የወጡት የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደሆነ የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ገለጹ። “ሚዲያ ጋላቢው” የሚባሉት አቶ ወርቁ አይተነው የኅልውናውን ጦርነት “ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል ነበር” የሚሉ ይኸው “ሠርግና ምላሽ ወደ ሐዘን ተቀይሮባቸው እንዲሰወሩ አድርጓቸዋል" ሲሉ ይገልጻሉ። እነዚህ ለአቶ ወርቁ ቅርብ የሆኑ ወገኖች እንደሚሉት ሪፖርተርን ጨምሮ ዘመኑ ያፈላቸው ሚዲያዎች ሕዝብን ሲያደናግሩና የማይጨበጥ መረጃ ሲረጩ መቆየታቸው ሳያንስ “አቶ ወርቁ አገር ውስጥ መኖር ባለመቻላቸው ተሰደዱ" ሲሉ የከፋይ ጋላቢያቸው አፍ ሆነዋል። “ሲፈልግ አራክሶና አፍንጫ ይዞ የሚሞግተው የዋልታው ስሜነህ ባይፈርስ ከወርቁ አይተነውን ጋር ባደረገው … [Read more...] about ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው
“ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
ዛሬ የትግራይ ክልልን እንዲያስተዳድሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቀመጡት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚታወቁባቸው የሽፍትነት ዘመን ንግግራቸው መካከል “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” የሚለው ነው። ዛሬ ደግሞ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ሆነው አራተኛውን ሙሌት ቦታው ድረስ በመሄድ አክብረዋል። ያኔ ተሸጧል ሲባል አብረው ያመኑና ዜናውን ያራገቡ መልስ ሊሰጡበት የሚገባው ጥያቄ፤ 1ኛ. ግድቡ አልተሸጠም ነበር ወይም 2ኛ. የተሸጠው ተመልሷል ወይም 3ኛ ይህ አሁን ሞልቶ የሚታየው ግድብ ከተሸጠ በኋላ በአዲስ መልክ የተሠራ ነው። መልሱን ለአቶ ጌታቸውና ደጋፊዎቻቸው እንተውና ኢትዮ12 ስለ አራተኛው ሙሌት በተመለከተ የዘገበውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግሥት የመፈረም ፍላጎት … [Read more...] about “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ
የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት
“ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል ድረስ እሄዳለሁ” በሚለው ሕዝብን የናቀና አገርን ያዋረደ ንግግር የሚታወቁት የአሁኑ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአስተዳዳሪነት የተሾሙባት ትግራይ እየፈረሰች መሆኑን በራሳቸው አንደበት አረጋገጡ። ቀደም ባሉት ዓመታት የትህነግ ሰዎችና አብረዋቸው የሚሠሩ ምሥጢረኞች፣ እንዲሁም የሚታወቁ ባለ ብሮች ብቻ የሚያውቋቸው የግል እስር ቤቶች በአዲስ አበባና በአንዳንድ ክልልሎች እንደነበሩ ይታወሳል። በነዚህ እስር ቤቶች የሚታሰሩ በድርድር ጠቀም ያለ ብር ከፍለው የሚለቀቁ ሲሆን እንደ አሁኑ ሚዲያ ባለመፍላቱ ይፋ አይሆንም ነበር። ይሁን እንጂ በሾርኔ በሚታወቁ ዓምዶች ፍንጭ ይሰጥ ነበር። በወቅቱ ደኅንነቱ የራሱ ልዩ እስር ቤቶች እንዳሉት ቢታወቅም የግል እስር ቤቶቹ ግን በመንግሥት መዋቅር ሥራ ባሉ ወይም በነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች የሚተዳደር ኃላፊነቱ … [Read more...] about የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት