በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ … [Read more...] about አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ
News
የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ
ሕጉ ምን ይዟል ? ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው (LGBTQ+) ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ የረጅም ጊዜ እስር ይጠብቀዋል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ፣ በቤተሰብ ደረጃ ያስጠለለ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል። በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል። "በተመሳሳይ ጸታ መብት" ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት … [Read more...] about የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ
አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን
* አሜሪካ ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል የ331 ሚሊዮን ዶላር ታደርጋለች * ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ትመለሳለች በመንግሥትና ሕወሓት መካከል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱን የተከታተሉት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም፤ በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያና በአሜሪካ … [Read more...] about አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን
ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያሰናከሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር ክስ እንዲመሰረት ጠየቀ። በመንግስት መስሪያ ቤቶች ስር የሚተዳደሩ ስብሰባ ቦታዎች እና አዳራሾች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ክፍት እንዲሆኑም ውሳኔ አሳልፏል። ቦርዱ ይህን ያስታወቀው፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ያጋጠሙ መስተጓጎሎችን በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 5፤ 2015 በአዲስ አበባው ሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው። በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሰረት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ቢያንስ በሶስት ዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ አለባቸው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ግዴታቸውን ለመፈጸም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወቅት መስተጓጎል እየገጠማቸው እንደሚገኝ … [Read more...] about ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ
በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ
ከፍጥነት ወሰን በላይ በመንዳት የሚደርሰውን የትራፊክ ጉዳት ለመቀነስ በተሽከርካሪዎች ላይ የፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ እንዲገጠም መወሰኑን ተከትሎ፣ በፌደራል መንግሥት ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው አቅራቢዎች ለኦሮሚያ ክልል እንዳያቀርቡ የገበያ ገደብ እንደተጣለባቸው ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። በዚሁ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የመሰረቱት “ኢትዮ መላ የተሸከርካሪዎች ፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ አስመጥቶ መግጠም ዘርፍ ማኅበር” ለአዲስ ማለዳ እንደገለጸው፣ በኦሮሚያ ክልል 17 ሺሕ ተሽከርካሪዎች የፍጥነት መገደቢያ እንዲገጠምላቸው ተወስኖ ከሕግ አግባብ ውጪ ለአንድ ግለብ ተስጥቶ ሌሎቹ በነጻ ገበያ እንዳይሳተፉ ተከልክለዋል ብሏል። የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ በክልሉ የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለንብረት ማኅበራት፣ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ ከአንድ ግለሰብ ጋር ውል ገብተው … [Read more...] about በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ
ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ
በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሰረት መንግሥት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ላገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች በየዓመቱ የበጀት ድጎማ ያደርጋል፡፡ በዚሁ መሠረት የ2015 በጀት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ለማከፋፈል በምርጫ ቦርድ ቀመር መሰረት የገንዘብ ክፍፍሉ መደልደሉን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ ቦርዱ ይህንኑ አስመልክቶ ቅዳሜ መጋቢት 2/2015 ከፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ውይይት በአገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፓርቲዎች 65 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ መደበኛ በጀት የበጀት ሲሆን፣ ፓርቲዎች ለሚያከናውኑት የሲቪል ትምህርት 41 ሚሊዮን ብር መመደቡን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ተናግረዋል፡፡ ፓርቲዎች የሚደርሳቸው ገንዘብ በዋና ዋና መስፈርቶች የሚመዘን ሲሆን፣ በሴት አባል ብዛት፣ በሴት አመራር ብዛት፣ በአካል ጉዳተኛ አባል ብዛትና በአካል ጉዳተኛ አመራር ብዛት ተሰልቶ የሚመደብ መሆኑ … [Read more...] about ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ
አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች
“መዓዛን ከሕግም፣ ከዕምነትም አንጻር የሽልማቱን መሥፈርት ጠይቁልኝ" በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ የዚህ ዓመቱ ደፋር ሴቶች ዓለምአቀፍ ሽልማት (2023 International Women of Courage Award) ለናዚ አባል መሰጠቱን በጥብቅ አወገዙ። አምባሳደሩ ያወገዙት ሽልማቱ ለዩክሬናዊቷ ዩሊያ ፓዬቭስካ በመሰጠቱ ነው። ከኢትዮጵያ ይኸው ሽልማት ለመዓዛ መሐመድ ተሰጥቷል። ዜናውን የተከታተሉ “ሽልማቱን ተከትሎ ወለል ብለው የሚታዩ ጉዳዮች አሉ” እያሉ ነው። ዓለምአቀፉ የሴቶች ቀን በተከበረበት ማርች 8 ቀን 2023ዓም “ደፋር ሴቶች” በመባል በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት መራጭና አቅራቢነት የተለየ ሥራ የሠሩ ሴቶች ሽልማታቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ተቀብለዋል። ይህ ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል ዩክሬይናዊቷ ዩሊያ ፓዬቭስካ … [Read more...] about አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች
ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይታሰባል ተብሎ ባልተገመተ ሁኔታ የዓድዋ በዓል በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በትግራይ የዓድዋ ከተማ ሶሎዳ ተራራ ሥር መከበሩን ኢፕድ ዘግቧል። በበዓሉ ላይ ህፃናት ስለ ዓድዋ ድል የሚተርክ ህብረ ዝማሬ አቅርበዋል። የከተማው ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዓሉን ለመታደም ማልደው በሥፍራው ተገኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡና በአማርኛ የተጻፉ አስደማሚ መፈክሮች በበዓሉ ሰልፍ ላይ ታይተዋል። ትህነግ በግፍ በሚገዛት ትግራይ ይህ ዓይነት አከባበር መከሰቱ ለክልሉ ሕዝብ የነጻነት ተስፋ የፈነጠቀ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ
በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ?
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን "በዓሉ በአዲስ አበባ ሶስቱም ቦታ በሰላም ተከብሯል፣ በዓሉን እንዳያከብር የተከለከለ ሰውም የለም" ብሏል 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ሚኒሊክ አደባባይ፣ አድዋ ድልድይ እና መስቀል አደባባይ በተለያዩ ስነስርአቶች ተከብሯል። የድል በዓሉን በሚኒሊክ አደባባይ ለማክበር የወጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች ግን” በዓሉን እንዳናከብር ተከልክለን ነበር፤ አስለቃሽ ጭስም ተተኩሶብናል” ብለዋል ከአል አይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ። እታገኘሁ በየዓመቱ የካቲት 23 የአድዋ ድል በዓልን ሚኒሊክ አደባባይና አድዋ ድልድይ ታከብራለች። ዘንድሮም በዓሉን ሁሌም እንደምታደርገው ጠዋት 3:00 መንገድ አቆራርጣ ሰሜን ሆቴል ከባለቤቷና ልጇ ጋር ደረሰች። ሆኖም ህዝባዊ በዓሉን ማክበር ከጀመረች ወዲህ ያልገጠማት ሁነት እንደተፈጠረ ገልጻለች። እታገኘሁ … [Read more...] about በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ?
አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት
ቢያንስ አንድ ቢሊዮን ብር ወይም ወደ ሃያ ሚሊዮን ዶላር አካባቢ የተዘረፈባቸው አውቶቡሶች የተገዙት ለዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ መሆኑ ታወቀ። ኤሊያስ ሳኒ ዑመር እና ያደታ ጁነዲን በክሪ (ብራይተን ትሬዲንግ) የመጨረሻ ተጫራች ሆነው በቀረቡበት ጨረታ ኤሊያስ ሳኒ ዑመር በኢትዮጵያ ውስጥ መኪና አስመጪነት ይቅርና በአጠቃላይ በአስመጪነት ያልተመዘገበ ድርጅት ነው። ሆኖም ለአንድ አውቶቡስ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር ዋጋ አስገብቷል። ባልተመዘገበ ድርጅት የተወዳደረው ኤሊያስ ሳኒ ዑመር ከፍተኛ ዋጋ አቀረበ ተብሎ 19 ሚሊዮን ብር ያቀረበው ያደታ ጁነዲን በክሪ (ብራይተን ትሬዲንግ) አሸነፈ ተብሎ ግዢውን ፈጽሟል። ከንቲባዋም የያደታ ጁነዲን በክሪ (ብራይተን ትሬዲንግን) ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል። ሆኖም ይህንን የመሰለ አደገኛ የሌብነት አሠራር ከመፈጸሙ በፊት የአውቶቡሶቹ … [Read more...] about አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት