በ116ኛው የሠራዊት ቀን ሲከበር ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ “ዐጼ ምኒልክ የጦር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያቋቋሙበትን ቀን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ኾኖ እንዲከበር ተደርጓል” በማለት ቀኑ ለምን እንደተመረጠ ይፋ አደረጉ። ከዚህ ሌላ ፊልድ ማርሻሉ በንግግራቸው፤ ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ከጀግኖች የተረከብናትን ኢትዮጵያ እንደተከበረች እና ማንነቷ እንደተጠበቀ ለማስቀጠል ወታደራዊ ዝግጁነታችንን አሳድገንና ቁመናችንን አዘምነን ማንኛውንም ተልዕኮ በላቀ ብቃት ለመፈጸም ሠራዊቱ ዝግጁ መሆኑን አሣውቀዋል። የሠራዊቱ አባላት የተሠጣቸውን ታላቅ አደራ በድል ለመወጣት የመፈጸም ብቃታቸውን በማሣደግ በዓላማ ጽናታቸው እንዲቀጥሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳስበዋል፡፡ ሠራዊቱ ሀገሩን እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን … [Read more...] about የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ
News
መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው
አየር ኃይል የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አስተማማኝና ዘመናዊ አየር ኃይል የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ አየር ኃይሉ በሁሉም ረገድ በመዘመንና ስኬታማ በመሆን ሀገር የምትኮራበት ታላቅ ተቋም መሆኑንም ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ላይ በውጊያ መሠረተ-ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና አጠቃቀም በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን በተቋሙ የተለያዩ ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስተማማኝ የሀገር መከታ በመሆን ለየትኛውም ግዳጅ አፈጻጸም ብቁና ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን ዘመናዊ ተቋም የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በአየር ኃይል … [Read more...] about መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው
“ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል። "በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም" ሲሉ ተናግረዋል። "እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል" ያሉት ሚኒስትሩ "አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው" ብለዋል። "የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው" ሲሉ አስገንዝበዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ "ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር … [Read more...] about “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ
42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ
የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታምሩ ገምበታን ጨምሮ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰሞኑን መሆኑንና አቶ ታምሩ ገምበታ ግን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል። የምክትል ዳይሬክተሩ ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መበርበሩንና ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡ የመንግሥት አስተዳደር ለውጥ ከተደረገ ጀምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ተቋም ውስጥ የተለያዩ ለውጦች (ሪፎርም) የተደረገ ቢሆንም፣ አንዳንድ የተቋሙ ሠራተኞች በድለላ ሥራ የተሰማሩ አካላት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ እንዳሉም … [Read more...] about 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ
በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ
የትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መመዝገብ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በጥናት ለይቶ እንዲያቀርብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠየቀ። በይህ የተጠየቀው በምክር ቤቱ የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ሚኒስቴርን የ2016 እቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ዛሬ ሲገመግም ነው። በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ " ቀደም ሲል ሲሰጡ የነበሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤቶች የተማሪዎችን ትክክለኛ ችሎታ ያሳዩ አልነበሩም" ብለዋል። የፈተና አሰጣጡን በመቀየር የተመዘገበው የተማሪዎች ውጤት በዘርፉ ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች ማሳያ መሆናቸውን ጠቁመው ለዚህም ከወላጆች ጀምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ … [Read more...] about በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ
ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል”
የዓባይ አጀንዳ ሲቋጭ የቀይ ባህር ጉዳይ መነሳቱ አጀንዳው እጅግ ተደርጎ የታሰበበት ለመሆኑ ማሳያ ተደርጓል። “የቀይባህር አጀንዳ ሃሳብ ማስቀየሪያ ነው” በማለት ለፕሮፓጋንዳ የሚነሱ የማይሳካላቸው በዚሁ መነሻ እንደሆነም ተመልክቷል። እጅግ ሰላማዊ በሆነና በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጮችን አቅርበው ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን እንዳለባት ያመለክቱት ዐቢይ ቀይ ባሕር “ጉዳይ የኅልውና ነው” ብለውታል። የወንበዴው መሪ መለስ ዜናዊ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ” ሲል አሰብ ወደብና ቀይ ባህርን አስመልክቶ ለተከራከሩ የሰጠው መልስ ነበር። ኢትዮጵያን የሚያክል አገር የተቆለፈባት እንድትሆን የተስማማው ትህነግ፣ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብቷን እንድትበትን ፈርዶባት ኖሯል። የድርጅቱ መሪ መለስ “አሰብን ከኢትዮጵያ ከመውሰድ ከኤርትራ መቀማት ይቀላል” በሚል ሥጋት … [Read more...] about ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል”
“አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች
“አቋጥሬ አይጫረሰ ነው” አሉ አንድ አዛውንት መላው እንደጠፋቸው በመግለጽ። “አቋጥሬ ምንድን ነው?” ሲባሉ፣ በአጭሩ ደምን መበቀለ ወይም ነብስን በነብስ ማካካስ የሚባለው የቆየ ልማድ ነው። “ጎበዝ ተጫረሰ” ያሉት የጎጃም ብቸና ከተማ አቅራቢያ ነዋሪ አዛውንት “እንደው መላም የለው” በማለት ብዙም ማብራራት አይፈልጉም። ዜናውን ያጋራን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን ቤተሰቦቻቸው ጋር መጥተው ያገኛቸው አዛውንት ክፉኛ ሃዘን ገብቷቸዋል። አማራ ክልል እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፋኖ ሃይሎች ወደ ከተማ ሲገቡ እስር ቤት ተከፍቶላቸው የወጡ ታራማሚዎች ቀደም ሲል የከሰሷቸውን ሰዎች መበቀላቸውን አዛውንቱን ጠቅሶ የዘገበው ተባባሪያችን፣ አንዱ ሌላውን እያደፈጠ ምላሽ በመስጠት በቀሉ ሳይታሰብ ተስፋፍቷል። የማቆሚያው መላም ቀላል አይመስልም። እሁድ ተለቅልቆ ሰኞ ተበራዬ፥ተሰው ሚስት አይሄድም … [Read more...] about “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች
በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል
በወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ከ1.1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ምርት የሚጠበቅ በመሆኑ ያንን ለመሰብሰብ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሠራተኛ እንደሚፈለግ ተገለጸ። “ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም ያለው እዚህ ነው። ለሠራተኞች እንደ ቤተሰብ ዝግጅት አድርገናል። ኑ” ሲሉ የተሰሙት አምስት መቶና ሶስት መቶ ሄክታር ሰሊጥና ማሽላ ያመረቱ ባለሃብቶች ናቸው። የዞኑ ግብርና ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ስለሚጠበቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሠራተኛ ሃይል ያስፈልጋል። የዞኑ አርባ በመቶ በሰሊጥ ምርት መሸፈኑን ያመለከቱት የዞኑ የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ አወቀ መብራቱ “ሰሊጥ ሲሰበሰብ በቂ የሰው ኃይልና ጥንቃቄ ስለሚሻ ይህን ባገናዘበ መልኩ አጨዳ ለመጀመር ዝግጅት ተደርጓል” ብለዋል። ከዝግጅቱ መካከልም ሠራተኞችን … [Read more...] about በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል
በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል
“በተፈጠረው የሰላም እጦት ክልሉ ከፍተኛ ገቢ እያጣ ነው” ሲል የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ እየታየ ያለው የሰላም እጦት በኢንቨስትመንቱ ላይ ቀጥተኛ የኾነ ተጽእኖ እያሳደረ እንደኾነ ነው የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የገለጸው፡፡ እየታየ ያለው አለመረጋጋት ወደ ክልሉ እየገባ ያለውን እና ለመግባት በሂደት ላይ የነበረውን ኢንቨስትመንት እንደሚያስቀር ተገልጿል። ይህ ደግሞ በክልሉ ምጣኔ ሃብት ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ነው ቢሮው ያስገነዘበው። የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ይሄነው ዓለም እንዳሉት ሰላም የሌለው ክልል አልሚዎችን ሊስብ አይችልም፡፡ አልሚዎች ለዳግም ኢንቨስትመንት በተለይም አዳዲስ ማሽኖችን ለማስገባት ያላቸውን ፍላጎት እንደሚቀንስም አብራርተዋል፡፡ ሰላም ከሌለ … [Read more...] about በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል
ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ሊተላለፉ የነበሩ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ጌታሁን አስፋው ጌታሁን የተባለ እና በአማራ ክልል የህዝብ ሰላም እና ጸጥታን ለሚያውኩ ጽንፈኛ ሀይሎች የሎጀስቲክስ አቅራቢ እንደሆነ የተጠረጠረ ግለሰብ በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት የሚገኝ ቤትን በመከራየት የተለያዩ ወታደራዊ ቁሰቁሶችን በማከማቸት ለጽንፈኛ ቡድኖቹ ለማቅረብ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል ሊደረስበት ችሏል፡፡ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የጸጥታ ዘርፍ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ባካሄዱት ኦፕሬሽን ግለሰቡ ከተከራየው ቤት የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች፣ የመካከለኛ እና የረጅም ርቀት ወታደራዊ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ ትጥቆች … [Read more...] about ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ