ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!

“ዳግም የመኖር እድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩ” “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጋቸው ሁሉ “አለሁ” የሚሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን አጥብቀው ይዋጋሉ። ይጸየፉታል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልማቸውና የመጨረሻ ግባቸው ነው። ሰብዓዊነት ለአፍታም ከአንደበታቸው የማይለይ፣ በሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ የሚወደዱ፣ ግልጽ ተናጋሪነታቸው ልዩ የሚያደርጋቸው ኦባንግ በዚሁ ባህሪያቸው “አባ ነቅንቅ” የሚል […]

Read More...

“ግድያው ተገቢና ሕጋዊ ነው” የህወሃት “ሰብዓዊ” ኮሚሽን

ህወሃት/ኢህአዴግ በንፁሐን ደም ላይ ማላገጡን ቀጥሏል!! በኢትዮጵያ ለሩብ ክፍለ ዘመን የተከማቸው የግፍ አገዛዝ  በምሬት የታጀበ ህዝባዊ አመጽ አስነስቷል። ህዝባዊ አመጽ ደግሞ ለኢትዮጵያ አዲስ ክስተት ባይሆንም በአገሪቱ ዉስጥ በሁለንተናዊ ዘርፍ ተጽዕኖ መፍጠር ከሚችሉት ሁለቱ ክልሎች (የኦሮሞና የአማራ፤ የደቡብ ኮንሶንና ጌዴኦን ተቃውሞዎች ሳንዘነጋ) ተከታታይነት ባለው መልኩ የአገዛዙን ማህበራዊ መሰረት በሚንድ ሁኔታ አመጽ መቀስቀሱ ይህኛዉን ክስተት የተለየ ያድርገዋል። […]

Read More...

ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል! (ክፍል ሁለት)

የማጠቃለያው መግቢያ እስኪ አንድ ጥያቄ እንመልስ፤ እንዴት መሽቶ ይነጋል? እነዚህ ወገኖች እንዴት ቻሉት? እንዲህ ያለው ስቃይ እንዴት ሌሎችን ያስደስታል? በህይወት ያለ ሰው በኤሌክትሪክ ማቃጠል ምን ማለት ነው? ሰውን ማኮላሸት ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ሰውን ሰቅሎ መርሳት፣ ገልብጦ ሲደበድቡ ማደርና ማቃጠል፣ ተነግሮ፣ ተወርቶ፣ የማያልቅ ጉድ! እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የሚያስቡት? ሕዝብ ስሜት ያለው አይመስላቸውም? የወላድንና የህጻናትን […]

Read More...

መዘጋቱ ታቅዶ የተከፈተው የአህያ ቄራ

በህወሃት ፈቃድ በቢሾፍቱ የተከፈተው አህያ ማረጃ (ቄራ) መዘጋቱ በእንግሊዝኛ የሚታተመው ፎርቹን ጋዜጣ ከሁለት ቀናት በፊት ዘግቧል፡፡ ቄራው የተከፈተ ሰሞን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ድጋፍ እንደነፈገው አብሮ ተዘግቧል፡፡ ቄራው የተከፈተው እንደሚዘጋ ታቅዶ ነበር፡፡ የዛሬ ሦስት ሳምንት አካባቢ በቻይናዊ ባለሃብት ከአዲስ አበባ 48ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ የአህያ ማረጃ መከፈቱ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በብዙዎች ዘንድ የመወያያ ርዕስ […]

Read More...

በበዓል ዋጋ ንረት የምትታመሰው አዲስ አበባ!

ተባዕት ዶሮ ከ280 – 360 ብር እየተሸጠ ነው! በግ ከ2,200 – 3,800 ብር የሽያጭ ዋጋ ደርሷል! ድልብ በሬ ከ25,000- 37,000 እየተሸጠ ነው! በረዥም ጊዜ ሂደት እየተዋረሰ የመጣው ኃይማኖታዊ በዓል አከባበራችን ከምግብ እና መጠጥ ጋር በጽኑ የተቆራኘ ነው፡፡ የአጽዋማትን ፍች በተመለከተ ከተቀመጡ ኃይማኖታዊ መርሆች ይልቅ ተለምዷዊ ድርጊቶች ገዥ ሐሳብ ሆነው ቀርበዋል፡፡ በዓላትን የታከከ ከፍተኛ የዋጋ ንረት […]

Read More...

“… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ ‘ወደ ችሎት’ አልመጣም” በቀለ ገርባ

“… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ አልመጣም” በፍርድ ሂደቱ ሲሉ መሰላቸታቸውን አቶ በቀለ ገርባ ተናገሩ። አቶ በቀለ ይህንን የተናገሩት ሃሙስ ባስቻለው ችሎት የመናገር እድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው ሲፈቀድላቸው ነው። ከሁለት ቀን በፊት አቃቤ ህግ በማስረጃነት አቀርበዋለሁ ሲለው የነበረውን የድምጽ ከምስል ማስረጃ አስተርጉሞ እንዲያቀርብና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ሃላፊ ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። […]

Read More...

ማዕከላዊ፤ የዜጐች ዋይታ ማማ! የስቃይ ማዕከል!

በማዕከላዊ ስቃይ ተፀንሶ ይወለዳል፤ ጡት ጠብቶ ዳዴ ብሎ ጐልምሶ ያረጅበታል!! እንደገና አዲስ የማሰቃያ ስልት ይወለዳል!! በማዕከላዊ በንጹሐን ዜጐች ደም የጨቀዩ ገራፊዎች ይርመሰመሱበታል!! ከዝግጅት ክፍሉ፡- ማዕከላዊ አገዛዙን በወታደራዊ የበላይነትና በደህንነቱ አቅም በቁጥጥር ስሩ ያዋለው ህወሓት፤ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ እያደረሰ ያለውን ቃላት የማይገልፁት የዜጐች ስቃይ በተመለከተ ጎልጉል ድረገጽ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን ዜጐችና ቤተሰቦቻቸውን በማነጋገር ይህን ዘገባ […]

Read More...

“ኢጂኣኦ” – የቻይናና አህያ ፍቅር – ቻይና በዓመት 4 ሚሊዮን የአህያ ሌጦ ትፈልጋለች

“አህያ ሲጠፋ እህል ማን ሊሸከም ነው? ሴት?!” የአህያ ሥጋና ቆዳ ንግድ እንደ ህገወጡ የአውራሪስ ቀንድ ንግድ እንዳይሆን ተሰግቷል “አህያ ልባችን ነው። አህያ ህልውናችን ነው። አህያ ቤተሰባችን ነው። አህያ ውለታውና ተግባሩ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ገዢዎቻችንም ቢሆኑ የአህያን ጥቅም በአግባቡ ያውቁታል። በበረሃ ሁሉን ችሎ እዚህ ያደረሳቸው አህያ ነው። እናም ጉዳዩ ከወሬ በላይ ነውና በሰከነ መልኩ ለማሰብ ፍላጎቱ […]

Read More...

ተራዛሚው የኦሮሚያ ድርቅ እና ያዘለው አደጋ!

በኦሮሚያ በሦስት ዞኖች ብቻ 241 ት/ቤቶች ተዘግተዋል፤ 114,751 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል! በቦረናና በጉጂ ዞኖች 127,010 ከብቶች በዘንድሮው ድርቅ ሞተዋል! ድርቅ ከፍ ሲልም ችጋርና ረሃብ ለኢትዮጵያ ተጠባቂ የስጋት ምንጭ ሆነው እንደቀጠሉ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ በተለይም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ካሳለፍነው አስከፊ የርስ በርስ እና ከጐረቤት አገራት ጋር ከተደረጉ ጦርነቶች ጐን ለጐን ድርቅ፣ ችጋር፣ ረሃብ ሌላኛው የኢትዮጵያ አስከፊ የታሪክ […]

Read More...

የብአዴን መክዳትና የ“በቀል” ፍርሃት የወለደው “የኢኮኖሚ አብዮት” በኦሮሚያ፤

“ህወሃት የፈጸመው ግፍ በየትኛውም ዘመን የሚረሳ አይሆንም” በህወሃት ገደብ የለሽ የሥልጣን ፍቅርና የቁስ ሰቀቀን ውልቅልቋ እየወጣ ያለችው ኢትዮጵያ ከፍታው ርቋት የቁልቁለቱን ጉዞ ተያይዛዋለች። ለወጣበት ዘውግ ልዕልና የሚተጋው ህወሃት ህግና ሞራል በማይዳኘው ድርጅታዊ ቀኖናው እየተመራ ኢትዮጵያን ማድማቱን ቀጥሎበታል። እስር፣ ቶርቸር፣ ስቃይ፣ ስደት፣ ሞትና የግዞት ኑሮ ከህወሃት ዘውግ ጥላ ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እድል ፈንታ ሆኗል። ከነዚህ […]

Read More...