በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) በቁጥጥር ሥር ውለዋል

በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት። ዜናው በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተዘገበ ሲሆን ከመኖሪያ ቤታቸው እንደተያዙ መረጃው ጨምሮ ገልጾዋል።

ታደሰ ካሳ ጥረት ኮርፖሬትን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ለበርካታ ዓመታት የመራ ሲሆን በረከት ስምኦን ደግሞ ከበርካታ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች ባሻገር የጥረት ኮርፖሬት የቦርድ ኃላፊ ሆኖ ሲመዘብር የነበረ ለመሆኑ ብዙዎች ይናገራሉ።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Comments

  1. ትልቁ እባብ ሌዋታን ከተያዘ ትናንሾቹ አይጦች አድኖ ለመያዝ ቀላል ነው። በረከት ሰምሆን በኢሕአፓ የትግል ስሙ አንበርብር። ተለዋዋጭ አውሬ አስፈሪው ዘንዶ ከተያዘ ኢትዮጵያ አረፈች ማለት ነው ። ከዚህ ሰው ጀርባ የነበረው ዋናው ሳጥናሄል ነበርና ለምድሬ ሕዝብ እረፍት ይሁን።

  2. እኔ ያልገባኝ ግን፡
    በረከት ህውሓት ነው? ወይስ ባእደን።

Speak Your Mind

*