• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ

November 10, 2012 02:47 am by Editor 1 Comment

“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው።

የትግራይ ህዝብ “ያንተ ነው” ስለሚባለው ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የሚያውቀው ነገር እምብዛም የለም። አስራ ሶስት ሰፋፊና ስትራቴጂክ ኩባንያዎችን ያቀፈው ኤፈርት በቅርቡ የእህት ኩባንያዎቹን ቁጥር እንደሚጨምር ምልክቶች አሉ። ኤፈርት ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ በስፋት ይነገርበታል። ከዚሁ ከሚታማበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ ወ/ሮ አዜብ በድንገት ይፋ ያደረጉት ምስጢር አነጋጋሪ ሆኗል።

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ኤፈርት ቀውስ ውስጥ እንደነበር በማስታወስ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የባለቤታቸውን የአቶ መለስን ማንነት የሚያጋልጥ አስገራሚ መረጃዎችን ሰጥተዋል። “ኢትዮጵያ ህዳሴ ባለቤትና ባለራዕዩ መሪ” በመባል በራሱ በህወሓትና በመላው የኢህአዴግ ሰዎች “የሚመለኩት” አቶ መለስ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ በጎሳና በቀበሌ ደረጃ ወርደው የሚያስቡ “የጎሰኛነት አባት” መሆናቸውን ባለቤታቸው አሳብቀዋል። ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ መታሰቡን ምንጮቹን በመጥቀስ የስዊድን የኢትዮጵያ ሬዲዮ ከዓመት በፊት የዘገበውን ምስጢር ወ/ሮ አዜብ ይፋ አድርገውታል።

ከሃዘን ያገገሙ የማይመስሉት ወ/ሮ አዜብ ትግራይን በመነጠል የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ አቶ መለስ የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ነድፈው እንደነበር ይፋ ሲያደርጉ ትግራይን ያጥለቀልቃሉ ስለተባሉት ኢንዱስትሪ ዓይነቶች ዝርዝር ግን አልተናገሩም። የስዊድን የኢትዮጵያ ራዲዮ ከዓመት በፊት ኤፈርት በትግራይ የምግብ ማቀናበሪያ ፋብሪካዎችና እጅግ ግዙፍ የሚባል የፒቪሲ ጥሬ እቃ ማምረቻ ፋብሪካ በመክፈት ትግራይን በመነጠል የኢንዱስትሪ ከተማ የማድረግ እቅድ እንዳለው  ምንጮቹን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። (ፒቪሲ በጣም ተፈላጊ የሆነ እና እጅግ በርካታ ለሆኑ የእርሻ፣ የኮንስትራክሽን፣ … ሥራዎች በቀጥታ ወይም እንደግብዓት የሚውል ነው)

ኤፈርት ቀውስ ውስጥ እንደነበር፤ በ2004 ግምገማ ተካሂዶ ከነበረበት “ክራይሲስ” እንደወጣና በበጀት ዓመቱ 357 ሚሊዮን ብር የትርፍ ግብር መክፈሉን ያስታወቁት ወ/ሮ አዜብ በዚህ መግለጫቸው ኤፈርት በእርሳቸው አመራር ያስመዘገበውን ትርፍ ይፋ በማድረግ የቀድሞውን ሃላፊ አቶ ስብሃት ነጋ ለማሳጣት ያለሙ መስለዋል።

“በተዘዋዋሪ የህዝብ ንብረት ናቸው” ሲሉ የገለጿቸው የኤፈርት እህት ኩባንያዎች ለአስራ ሰባት ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ወ/ሮ አዜብ አመልክተዋል። መስፍን ኢንጂነሪንግ በሶስት፣ አልሜዳ ጨርቃጨርቅ በአምስት እጥፍ እንደሚያድግ፣ መሰቦ ሲሚንቶ የማስፋፊያ ስራውን በማጠናቀቁ ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ያስታወቁት ወ/ሮ አዜብ ሱር ኮንስትራክሽን የያዘው አዲስ ፕሮጀክት ሲጀመር አስር ሺህ ለሚሆን ሰራተኞች ስራ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ወ/ሮዋ የተፈጠረውን የስራ እድልና ሰራተኛ ብዛት ለይተው በክልልና በብሄር ግን አልገለጹም።

ኤፈርት የሩብ ዓመት የስራ እንቅስቃሴውን ሲገመግም በአቶ መለስ “መሰዋት” ምክንያት ኤፈርት ውስጥ ከፍተኛ ሃዘን ሰፍኖ ስለነበር በተወሰነ ደረጃ የስራ መፋዘዝ ቢከሰትም በተያዘው የበጀት ዓመት 16.57 ቢሊዮን ብር የሚገመት ምርት ገበያ ላይ ለማቅረብና 1.7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ለማግኘት መታቀዱን የወ/ሮ አዜብ መግለጫ ያስረዳል።

ኤፈርት በቅርቡ ይፋ ከሚያደርጋቸው ፋብሪካዎች መካከል ለፒቪሲ ምርቶች ግብአትነት የሚያገለግለውን ጥሬ እቃ የሚያቀናብረውን ፋብሪካ እንደሚሆን ይገመታል። ሪፖርተር ባለፈው ዓመት እንደገለጸው ፋብሪካው የኤፈርት አስራ አራተኛ እህት ኩባንያ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል። በቻይና ባለሙያዎችና ቴክኖሎጂ የሚገነባው ይህ ፋብሪካ ለግንባታው ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረግበታል። ማምረት ሲጀምር ለአገር ውስጥ የፒቪሲ አገልግሎት የሚውለውን 40 ሺህ ሜትሪክ ቶን ጥሬ እቃ በማምረት ለአገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ብቸኛ አቅራቢ ይሆናል።

ከሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ግዙፍ የንግድ ተቋም ሚድሮክ ግሩፕ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የንግድ ስትራቴጂ የሚከተለው ኤፈርት በአሁኑ ወቅት ያሉት ቁልፍ የንግድ ተቋማት መሰቦ ሲሚንቶ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል፣ ባባ ዳይሜንሽናል ስቶን፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ኤክስፕረስ ትራንዚት፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ አዲስ ፋርማሲዩቲካል፣ ጉና ትሬዲንግ፣ ሂወት አግሪካልቸር፣ ሼባ ታነሪ፣ ኤክስፔሪየንስ ኢትዮጵያ፣ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅና ኢዛና ናቸው፡፡

ዜናውን ተከትሎ አስተያየት የሰጡ የደቡብ፣ የአማራ፣ የኦሮሚያ የፓርቲ የንግድ ተቋማት በክልላቸው እንኳ መነገድ ያልቻሉ የሙስና ተቋማት ሲሉ ወቅሰዋቸዋል።በከባድ የሙስና ድብታ ውስጥ ወድቀው እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ በማሳፈር ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የአማራው የልማት ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አገኘሁ በማለት እነ ህላዊ ዮሴፍ ሸራተን ከበሮ ሲያስደበድቡ መስማታቸው እንዳሳዘናቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪ “ብአዴን ከአፈጣጠሩ ጀምሮ አሳፋሪ ሰለሆነ ልንታገለው ይገባል። ከብአዴን ጋር መቀጠል ወደፊት ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ችግር ላይ ይጥለናል” ብለዋል።

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ከህወሃት መስራቾች መካከል አንዱ ናቸው። ትግል ሲጀመር የነበሩትና ስለኤፈርት በመጠየቃቸው መባረራቸውን የሚጠቁሙት አቶ አስገደ ከፍትህ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስለ ኤፈርት የተናገሩትን ቃል በቃል አቅርበነዋል።አቶ አስገደ የአረና ትግራይ አባል ናቸው።

ፍትህ፡-እርሶ በአመራርነት እየሰሩበት ያለው አረና ፓርቲ በትግራይ ህዝብ ዝም ነው የተደራጀው፡፡ ታዲያ በትግራይ ህዝብ ስም የተቋቋመው ኤፈርት የሚያስገባው ገቢ የት እንደሚውል ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ያደረጋችሁት ጥረት አለ?
አቶ አስግደ፡- መጀመሪያ ነገር አረና ምንም እንኳን ብሔራዊ ፓርቲ ሆኖ ቢመሰረትም ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገል ፓርቲ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ወደ ጥያቄው ስንመለስ ይህንን ጥያቄ እንኳ እኛ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ቀርቶ ተራው ህዝብ ሳይቀር የሚያነሳው ነው፡፡ እኔ በግሌ እስከ 1993 ድረስ የኤፈርት ሰራተኛ ነበርኩ፡፡ በዋናነት ከህወሓትም ከስራዬም እንድወጣ ያደረኝ ከ84ዓ.ም ጀምሮ ይሄንን ጥያቄ ስለማነሳ ነው፡፡ እናም አረና በተለያየ መድረክ ላይ ጉዳዩን ያነሳዋል፡፡ ነገር ግን ከነሱ ጋር ፊት ለፊት ቀርበን ለመከራከር መድረኩን አላገኘንም፡፡ በራሳችን መድረክ ግን እንደ አጀንዳ እያነሳነው ነው፡፡ … ይሄ ገንዘብ ለልማት አልዋለም…፣ … በዚህ ገንዘብ የትግራይ ህዝብ ሳይሆን 45 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ለምን ፈላጭ ቆራጭ ይሆናል?…፣ …ገቢ እና ወጪው በውስጥ እና በውጭ ኦዲተር ይመርመር… እያልን ደጋግመን አንስተናል፡፡ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ህዝብ ይሄ ንብረት የማነው? እያለ ቢጠይቅም መልስ የሚመልስለት ግን አላገኘም፡፡ እነሱም ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ እያሉ ከማፌዝ ውጭ መልስ አይሰጡትም፡፡

ፍትህ፡-ግን እኮ ኤፈርት ሲቋቋም እርሶን ጨምሮ አቶ ገብሩ አስራት፣ ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ፣ አቶ ስዬ አብርሃ እና የመሳሰሉትን አመራሮች እንደነበራችሁበት የሚጠቅሱ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች … እናንተም ህወሓት ውስጥ በነበራችሁበትም ጊዜ ቢሆን የኤፈርት ገቢ ለህዝቡ አይውልም ነበር… ሲሉ ይወቅሳችኋል፡፡ ታዲያ ይህ ሁኔታ እናንተንስ ተጠያቂ አያደርጋችሁም?
አቶ አስግደ፡- ምን መሰለህ ኤፈርት ገና ሲቋቋምም የአገሪቱን ህግ ተከትሎ እና አክብሮ እንዳልተቋቋመ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም መሰለኝ አንድ ጊዜ የህዝብ ነው ይሉታል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ የህወሓት ነው ይላሉ፡፡ ተሸፋፍኖ ነው ያለው፡፡ እናም በወቅቱ ድርጅቱ ህግ አክብሮ አለመስራቱን መቃወም እና ማረም ነበረባቸው፡፡ በዚህ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ በደረጃችን እኛም የምንጠየቅበት ካለ ልንጠየቅ እንችላለን፡፡ ሆኖም በወቅቱ ልንናገር የምንችልበት አንደበት የለንም ነበር፡፡ አፈና ነበረብን፤ በተለይም ለታጋይ ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህም በየደረጃው ሊጠየቅ የሚገባ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ምክንያቱም 20 ዓመት ሙሉ ከኤፈርት ለማህበራዊ አገልግሎት የዋለው አንዲት ትምህርት ቤት በ17 ሚሊዮን ብር ተሰርቷል፡፡ ማን ይጠቀምበታል እንጂ አንድ የአካል ጉዳተኞች ህንፃ 11 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ አውጥተው ሰርተዋል፡፡ በዋጅራትም አራት ሚሊዮን ብር የሚፈጅ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እየሰሩ ነው፡፡ ወደ 4 ሚሊዮን ብር ገደማ የሚሆንም ለአካል ጉዳተኞቹ እንደተሰጠ ይነገራል፡፡ ከዚህ ውጭ በቢሊዮን የሚቆጠረው ገቢ የት እንደሚገባ አይታወቅም፡፡ ይሄ ገንዘብ ለግድብ ቢውል የተከዜን መጋቢ ወንዞች እየገደቡ የተሻለ ስራ መስራት ይቻል ነበር፡፡

በተያያዘ ዜና ሰንደቅ 8ኛ ዓመት ቁጥር 374 ረቡዕ ጥቅምት 28 ቀን 2005 አንድ ሚሊዮን የመጠጉ የትግራይ ተወላጆች የተሳተፉበት ስብሰባ መካሄዱን በመጠቀስ ባስነበበው ዜና በክልሉ ይበልጥ ተግባራዊ እንዲደረግ ከታቀደው ፖለቲካዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በተያዘው ዓመት 750 ሺህ አርሶ አደሮች በመስኖ እንዲያለሙ፣ በክልሉ 50 በመቶ የሚሆነው መሬት እንዲታረስና ከግብርና ምርት በተጨማሪ ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ኩንታል አትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል። ለዚህ እቅድ ተግባራዊነትም ሁሉም አርሶ አደር ማዳበሪያ እንዲጠቀም መመሪያ መውረዱንም አመልክቷል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: azeb al amoudi, effort, Full Width Top, Middle Column, midroc

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    December 18, 2012 05:52 pm at 5:52 pm

    EFFORT is an Ethiopian property established from money looted from Ethiopia and Ethiopian banks. When there be an Ethiopian government, it should be nationalized/privatized.

    http://www.ethiomarket.com/effort/effort_companies.htm

    http://articles2u.wordpress.com/2010/03/09/corruption-and-tplf how Azeb loots AIDS money

    http://gce.etc.tripod.com how Ethiopian telecom is being looted by woyane ethnic fascists

    http://vimeo.com/18242221

    http://www.peri.umass.edu/fileadmin/pdf/ADP/SSAfrica_capitalflight_Oct23_2012.pdf

    http://www.ethiotoday.eu/politics.html

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ October 30, 2023 10:27 am
  • የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ October 26, 2023 01:30 pm
  • ጥቅምት 15 ለምን? October 26, 2023 01:29 am
  • “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” October 26, 2023 12:57 am
  • “ውትድርና ሕይወቴ ነው” October 26, 2023 12:13 am
  • መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው October 20, 2023 05:07 pm
  • “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ October 20, 2023 04:47 pm
  • 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ October 18, 2023 04:29 pm
  • በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ October 18, 2023 04:00 pm
  • ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” October 13, 2023 10:04 pm
  • ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም October 10, 2023 01:51 pm
  • “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች October 10, 2023 09:07 am
  • እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ! October 7, 2023 06:47 am
  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule