ጉሮሮህን ጠራርገህ፤ ምላስህን ሳልና እንደ ሽንኩርት የምልጠው እንደ ኪኒን የምውጠው ጥሩ ቃላት ምረጥና እንደ እበት ሳትለድፍ እንደ ጭቃ ሳትለጥፍ ልክ ልኬን ንገረኝ ደስ ይበልህ…ስደበኝ ባንተ መለኪያ ተለክቸ ባንተ መነፀር ታይቸ ሙሉ እንደማልሆን አውቃለሁ ባልተገራ ምላስህ ባዶ በሆነው ራስህ ማንነቴን ስትናገር፤ ማንነትህን አያለሁ እና…አንተን ደስ እንዲልህ የተጫንከው እንዲቀልህ ……………..ስደበኝ ለአቶ ዓልምነው መኮነን የአማራ ክልል ም/ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ … [Read more...] about ስደበኝ
118ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል
ተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ያገኛሉ:: … [Read more...] about 118ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል
ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤ እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ … [Read more...] about ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ
በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና
ባሳለፍነው ሃሙስ የወላጅ መምህራን ስብሰባ ላይ ስለጅዳው አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤት አስተዳደር ፍትሃዊነት የቅጥር ሂደት እና በትምህርት ጥራቱ ዙሪያ ላይ አንድ በኢኮኖሚክስ ትምህት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ ወጣት የሰላ ሂስ አቀረበ። በቀረበው የወጣቱ የዩኒቨርስቲ መምህር ስደተኛ ስራ ፈላጊ አስተያየት ድጋፍና ተቃውሞ ቤቱን በየተራ ናጠው። በትምህርት ጥራት አለመኖር የሚስማማው ወላጅ በጭብጨባ ድጋፉን ሲገልጽ የትምህርት ጥራቱን አንድ ከኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የ12 ኛ ክፍል ተማሪ ጋር በእንግሊዝኛ ትምህርት እውቀታቸው የኤርትራ ኢምባሲ የ7ኛ ክፍል ተማሪ እንደሚልቅ በንጽጽር ማቅረቡ የተከፉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖርቲ አባላትና ደጋፊዎች ውግዘት አስከተለበት። አንዲት የወላጅ መምህራን ህብረቱ አባል ለትምህርት ጥራቱ ንጽጽር "ኤርትራ" የምትባለውን ሃገር ከአፉ … [Read more...] about በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና
የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች
በዓለማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን በማወዳደር ደረጃ የሚያወጣው (4 International Colleges & Universities (4icu)) የአፍሪካ ምርጥ የተባሉትን ዩኒቨርሲቲዎችን ዝርዝር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ ነበር፡፡ ድርጅቱ በርካታ መረጃዎችን በመሰብሰብ እንዲሁም ለማንም ወገን ያላዳላ ጠለቅ ያለ ሒሳባዊ ትንታኔ በማድረግ ደረጃውን እንደሚያወጣ በድረገጹ ላይ ጠቁሟል፡፡ ከአንድ እስከ ሃያ ባሉት ዝርዝር ውስጥ የደቡብ አፍሪካና የግብጽ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃውን በብዛት ተቀራምተውታል፡፡ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ቦትስዋና እና ኬኒያ እስከ ሃያ ባለው ደረጃ በመግባት የአገራቸውን የትምህርት ተቋማት ብቃት አስመስክረዋል፡፡ ከተመሠረተ 60ዓመታት ያለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (በቀድሞ ስሙ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ) እስከ መቶ ባሉት ዝርዝር ውስጥ … [Read more...] about የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች
በሪያድ የኢትዮጵ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራር ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ እመራር ኮሚቴ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በታደሙ አባላት እና የአምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ በሚታወቁት የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ደጋፊዎች መሃከል ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ወደ ግጭት አምርቶ እንደነበር ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል። የስብሰባውን ታዳሚ ግራ ያጋባው ይህ ግጭት መነሻው የቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሼክ ሙሰጠፋ ሁሴን ለምን ከስልጣኔ ተነሳሁ በሚል በምከትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ላይ ቡጢ መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሼክ ሙስጠፋ ከስብሰባው በፊት ሲያስተባብሯቸው የነበሩ ከ 50 የሚበልጡ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት ሁከት የመስብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ማምሸቱን ጠቅሰዋል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራር ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !
ግብፅ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀመረች
የግብፅ መንግሥት በታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ በተመለከተ ሱዳን ለኢትዮጵያ የሰጠችውን ድጋፍ ለማጨናገፍ፣ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ መጀመርዋን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ የተለያዩ የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ሰሞኑን እንደዘገቡት፣ የግብፅ መንግሥት የተለያዩ የመንግሥት አመራሮችና ፖለቲከኞች ከሱዳን መንግሥት አቻዎቻቸው ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል፡፡ ለአብነት ከተጠቀሱት መካከል የግብፅ አል ዋፍድ ፓርቲ ሊቀመንበር ሳይድ አል ባዳዊ በካይሮ ከሱዳን አምባሳደር ከማል ሐሰን ዓሊ ጋር በሁለቱ አገሮች ድንበር የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በዋነኝነት መክረዋል፡፡ በሁለቱ አገሮች ድንበር የጦር መሣሪያ ዝውውር ለማስቆም የተነጋገሩት ሁለቱ ባለሥልጣናት፣ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው የታላቁ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብና በሱዳን አቋም ላይ ተነጋግረዋል፡፡ ከውይይታቸው በኋላ … [Read more...] about ግብፅ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀመረች
አልበሽር ከተቃዋሚዎች ጋር ለመሥራት እፈልጋለሁ አሉ
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ባለፈው ሰኞ በቀጥታ የአገሪቱ ቴሌቪዥን የተሰራጨ ንግግር አድርገዋል፡፡ የአልበሽር ንግግር በሶስት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ለመጀመርያ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን ያካተተ ነበር። በቻይና መንግስት ትብብር በተሰራው የብሉ ናይል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከተሳተፉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል አልበሽር ወደ ስልጣን የመጡበትን የ1989ኙን መፈንቅለ- መንግስት በማቀነባበር ወሳኝ ሚና የተጫወቱትና በ2000 ዓ.ም ከገዢው ፓርቲ የ“ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ” ተገንጥለው “ኦፖዚሽን ፖፑላር ኮንግረስ” ፓርቲን ያቋቋሙት ሀሰን አልቱራቢ፣ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የአልበሽር አማካሪ የነበሩትና ታህሳስ ላይ የ“ለውጥ ፓርቲ”ን የመሰረቱት ጋዚ ሳላሀዲን አትባኒ እና የ“ኡማ ፓርቲ” መሪ ሳዲቅ አልመሃዲ ይገኙበታል፡፡ አልበሽር በንግግራቸው ላይ ሶስት የለውጥ … [Read more...] about አልበሽር ከተቃዋሚዎች ጋር ለመሥራት እፈልጋለሁ አሉ
ጐፋ ገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 መደብሮች ወደሙ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቄራ ጐፋ የገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 መደብሮች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡ ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 7፡15 ሰዓት ላይ የእሳት ቃጠሎው እንደተከሰተ የገለጹት፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ ናቸው፡፡ የእሳቱ መነሻ ምክንያትና በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡ በቄራ ጐፋ የገበያ ማዕከል ውስጥ ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ንጋቱ፣ ከቤቶቹና ከሱቆቹ አሠራር አኳያ ሲታይ 19 መደብሮችና መኖሪያ ቤቶች ብቻ ተቃጥለው ሌሎቹ መትረፋቸው አስገራሚ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቤቶቹ ከተሠሩበት ግብዓትና መቀራረብ አኳያ መሆኑን አክለዋል፡፡ ከ53 ሺሕ ሊትር በላይ … [Read more...] about ጐፋ ገበያ ማዕከል ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 19 መደብሮች ወደሙ
ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ …!
የመምህራን ማስጠንቀቂያ ... ሰሞነኛው የጅዳዎች ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድን በማስተካከል ዙሪያ ቢሆንም ከ 3000 (ከሶስት ሽህ) በላይ ታዳጊዎችን የሚያስተናግደው የጅዳው አለም አቀፍ ት/ቤት አሁንም አደጋ ላይ መሆኑን እየሰማን ዝም ብለናል! ከሳምንታት በፊት መምህራን አመጽ አድርገው ነበር። ከቀናት በፊትም 25 መምህራን ስብሰባ ተቀምጠው፣ በአንድ አቋም ጸንተው ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ላለፉት 8 ወራት በትምህርት ቤቱ ባለቤት በኮሚኒቲው ጉዳያቸው ቢያዝም እስካሁን ከወሬ ያላለፈ አርምጃ አለማየታቸውን ገልጸዋል። 25 ቱ መምህራን ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ ለኮሚኒቲው፣ ለጅዳ ቆንስልና ለወላጅ መምህራን ህብረት ባስገቡት ደብዳቤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት የሁለተኛው የትምህት አጋማሽ መጀመሪያ የመኖሪያና የስራ ፈቃዳቸው ተስተካክሎ ካልተሰጣቸው በማስተማር መደበኛ ስራቸው … [Read more...] about ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ …!