“[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል” ወለላዬ

"...ሁሉም አለቦታው ተቀምጦ አገራችንም እኛም መቀለጃ የሆነው ለዚህ ነው"

ሰላም ጎልጉሎች . . . እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ከኢትዮጵያ ዛሬ ጋር በግጥሞቼ ሳቢያ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር። እናንተም ግጥሞቼን በተገቢው ሁኔታ ያስተናገዳችሁልኝ ስለሆነ እናንተም (ዘንድ) ቢታተም እወዳለሁ። በድጋሚ መልካም በዓል ይሁንላችሁ። ወለላዬ መዝጊያ ትሁንልኝ መቶ ራት ግጥሞችን – ተሸክሜ ይዤ፤ ረብዕ ረቡዕ ስጥል – አንድ አንዷን መዝዤ በዚች ባሁኗ ቀን – በጨበጥናት ሳምንት፤ […]

Read More...

የዛ ሰውዬ ድምጽ . . .

(ወለላዬ)

ፊቱ አሸቦ መስሎ፣ እንደደነገጠ፣ ተጎልጉሎ ወጥቶ፣ ዓይኑ እንደፈጠጠ፣ ባንኮኒው ጋ ሄዶ፣ ቢራውን ጨበጠ። የሆነውን እንጃ! ሁኔታው ያስፈራል፣ እንባው በጉንጩ ላይ፣ አቋርጦ ይፈሳል አልቅሶ ሲበቃው፣ ውጪ እየሰለለ፤ ያየውን በውስጡ፣ እያሰላሰለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ። ወደ ተናጋሪው፣ አፍጠን እያየን፤ እንደልማዳችን፣ ዝም ተባባልን። ሰውዬው ቀጠለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ! ዘለው ያልጠገቡ፣ እህል የተራቡ፣ አገር የተቀሙ፣ ፍትሕ […]

Read More...

ለጀግናው አትሌት ስንብት!

(ትዝታ ዘ ምሩፅ)

. . . በዚያ ቀውጢ ጊዜ – በዚያ ቀውጢ ዘመን፣ ከአገር በራቀበት – የደስታ ሰመመን፤ ያገር ፍቅር ስሜት –  መገለጫ ፈርጦች፣ ብቸኛው አማራጭ – የደስታችን ምንጮች፣ ነበሩን! ነበሩ! “አረንጓዴ ጎርፎች”. . .፤ እንዲህ እንደዛሬው – ሳይዘምን ዘመኑ፣ ያለም መገናኛ – ሳይራቀቅ ኪኑ፣ ዩ ቲዩብ፣ ኢንተርኔት፣ ስማርት ፎን..ሳይኖር፣ ዜና መቀበያው – ራድዮናችን ነበር፤ “. . . […]

Read More...

በማወቅና በማድረግ እውነትን መኖር?

ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ወገኖቼ በሙሉ!

የሕይወትን እውነትና ትክክለኛ ትርጉም ተረድተን በሰላምና በፍቅር ለመኖር የሚያስችል የአእምሮ መታደስ ለማድረግ የሚከተለውን ላካፍላችሁ፡ ከሁሉ አስቀድሜ ልረሳው የማልችለውን መልካም ባህላችንን ተጠቅሜ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን እላለሁ፤ እኔም ከሃገር፣ ከቤተሰብ፣ ከዘመድና ከጓደኛ ተለይቼ ባህሉንና ወጉን ጠንቅቄ ከማላውቀው ሕዝብ ጋር በእኛ አቆጣጠር ባለፈው ታሕሳስ 16 ቀን 2009 ዓ/ም የፈረንጆችን የገና በአል አክብሬ አሁን ደግሞ የእኛን ታሕሳስ 29 […]

Read More...

The TPLF Hired a Rubbish Writer to Defend it against Prof. Al Mariam

(LJDemissie)

With an open mind, I read an article titled “TEACHING ALMARIAIM HOW TO WRITE” on the Aiga Forum website, the Tigrayan People’s Liberation Front’s (TPLF’s) mouthpiece. The article was written by Yenieta A, who claimed that Ethiopian political writers don’t know how to write. To make his point, he used Professor Al Mariam’s commentary titled […]

Read More...

የምሥራች ነፃነት ላጣው

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን «እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሓ…» « ትልቅ የምሥራች ዜናን እነግራችኋለሁ..»ሉቃ ፪፦፲-፲፬፤ ነገር ከሥሩ ውኃ ከጥሩ እንዲሉ የምሥራች ህገ ወንጌልን ለመታወጅ ያበቃውን ስንመረምር ፤ እግዚአብሔር አምላክ በጥንተ ፍጥረት የሰውን ልጅ ወደዚህ ምድር ፈጥሮ  እንዲያስተዳድረው ከማድርጉ  አስቀድሞ፤የሚተዳድርበትን የሥነ ፍጥረት ህግ አዘጋጀለት፤ ሥጋዊ አካሉ እንዳይዝል የሚያርፍበት ሌሊት ተሐድሶ የሚነሣበት […]

Read More...

“ሐሩርም ይሁን በረዶ እኔ ከማሸነፍ የሚገታኝ አንዳች ኃይል የለም” – “Yifter the Shifter”!

"ሽልማቶቼ የኢትዮጵያ ሕዝብ ናቸው፤ ለሽያጭ አይታሰቡም" ምሩፅ

ከሠላሳ ሰባት ዓመት በፊት የተካሄደው የሞስኮ ኦሊምፒክ ሲነሣ ቀድሞ የሚመጣው የሚወሳው ረዥም ርቀት ሯጩ ምሩፅ ይፍጠር ነው፡፡ የድል ቁርጠኝነት የተሞላበት አሯሯጡ የመላው ዓለምን ምናብ ሰንጎ መያዙ አይረሳም፡፡ በሞስኮ ኦሊምፒክ በሁለቱ ርቀቶች በ5,000 ሜተርና በ10,000 ሜትር ለተቀናቃኞቹ ዕድል ሳይሰጥ ተፈትልኮ የሮጠበትና ያሸነፈበት መንገድ ‹‹ይፍጠር ዘ ሺፍተር›› (ማርሽ ለዋጩ ምሩፅ – አካለ ማርሹ ምሩፅ) የተባለበትን ዳግም ያረጋገጠበት […]

Read More...

“ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን እንገነጥላለን”

በበታችነት ሕመም የተጠቁ አሳዛኝ ፍጡሮች ባዶ ጩኸት!

“ሀገር አጥፊው አረም በሀገሬ ሲስፋፋ፣ ሁሉም ተዳከመ የሚያርመው ጠፋ፣ የጊዜ ጉዳይ ነው እኔ አለቆርጥም ተስፋ፣ ሀገሬ ነው የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣ ጥቃቱ ይሰማው ሲቆረስ አካሉ።” ከሊቀ ማዕመራን አበባው ይግዛው “ወይ ሀገሬ” ከሚለው ግጥም የተወሰደ። የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመቀራመት በተነሱበት ወቅት በተለያዩ ሀገሮች እገራቸውን ያስገቡት በሀይማኖት አስተማሪነት ሰም የቄስ ካባ አልብሰው የመረጃ (ሰላይ) […]

Read More...

ለማንነታችን መከታ ያልሆነን፣ ለመጠቃታችን ምክንያት እየሆነ ነው!

ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በሕዝባችን ላይ፣ በተለይም በዐማራው ነገድ ላይ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በ«አርበኞች ግንቦት 7» እያመካኘ ነው። ለዚህም ምክንያት የሆነው አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በሚቆጣጠረው የብዙኃን መገናኛ ያላደረገውን አደረኩ፣ ያላዘመተውን ወታደር አዘመትኩ፣ «የክተት አዋጁ ፊሽካ ተነፋ»፣ በሁሉም ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴዎች እኔ አለሁበት፣ የምመራው እኔ ነኝ፣ […]

Read More...

በኢንተርኔት መቋረጥ 9 ሚሊዮን ዶላር፣ በሞባይል ኢንተርኔት ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ኪሣራ!

የህወሃት ሹሞች “ስብሠባ ላይ ናቸው”

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅና ከዚያ በፊት በነበረው ሁኔታ የኢንተርኔት መቆራረጥና መታገድ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማድረሱ የተጠቀሰ ሲሆን  ባለፈው አንድ ዓመት አገሪቱን 9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማሣጣቱን የአሜሪካው ብሩኪንግስ ኢንስቲቲዩት ይፋ ያደረገው ጥናት አመልክቷል። ዴልዮት የተባለው ዓለማቀፍ አማካሪ ተቋም በበኩሉ፤ የሞባይል ኢንተርኔት መዘጋት ሀገሪቱን በቀን 5 መቶ ሺህ ዶላር እያሳጣት ነው ብሏል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች […]

Read More...