* በሶስት ወራት ብቻ ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰድዋል" - የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ አውራ መንገዶች "ልጄ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ሲሄድ በአጋቾች ተይዞ ይህንን ብር ክፈል፣ ካልከፈልክ ትገደላለህ ብለውኛል እርዱኝ" የሚሉ በትልቅ ባነር በተቀመጠ የወጣቶች ፎቶ አስደግፈው እርዳታ የሚለሙኑ ወላጆች ተበራክተዋል። ከነዚሁ ወላጆች የአክሱም ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ኣስካለ ውብኣንተ አንድዋ ሲሆኑ፤ ይጦረኛል ብለው ኮስኩሰው አስተምረው ያሳደጉት ወንድ ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት የነጠቃቸው እናት ናቸው። "ልጄ በጦርነቱ ማግስት በአከባቢው የስራ እድል በማጣቱ በህገ-ወጥ መንገድ የተለያዩ ሃገራት ደንበር አቋርጦ ሊብያ ሲደርስ ለሰው ህይወት ቁብ በሌላቸው ሽፍቶ እጅ ወድቆ ቁም ስቅሉን እያሳዩት ነው" ብለዋል። "አካል … [Read more...] about በትግራይ ከሞትና ከአካላዊ ጉዳት የተረፉት ለስደት ተዳርገዋል
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው
* ኃላፊዋ በዕለቱ አለመገኘታቸው “ለወደፊቱ እንዳይደገም” ማሳሰቢያ ተሰጣቸው በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2015 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ላይ ለመወያየት ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ነገር ግን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ስብሰባው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ቁጣን ፈጥሯል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ምን አሉ? "በመሰረቱ ምክር ቤቱ ተመርምረው የቀረቡለትን የዋና ኦዲት ሪፖርቶችን ይፋዊ ውይይት የሚያደርግባቸው የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ነው። “እኔ የመጣችሁትን የተመርማሪ … [Read more...] about የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው
ደም ጠጥቶ “አልጸጸትም” – የጃዋር አዲስ መጽሐፍ
ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አህመድ ግራኝ ነኝ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነኝ፤ “የአማራ ብሔርተኝነት ማነሳሳታችን ትልቁ ስኬታችን ነው”፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሥልጣን ያበቃሁት እኔ ነኝ፤ የምርጫውን ቀመር (ካልኩሌሽን ሠርቼዋለሁ)፣ ቁርአን ይዤ ዐቢይን ጅማ ላይ እንዳይመረጥ አደርገዋለሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት መንግሥት ነው ያለው - የዐቢይ እና የቄሮ መንግሥት፣ እኔ ከታሰርሁ ኦሮሚያ ድብልቅልቁ ነው የሚወጣው፣ የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ፣ ብዙ ዕውቀት አለኝ፤ ብዙ ችሎታ አለኝ፤ ወዘተ በማለት ያለማቋረጥ ከመትፋት አልፎ “ተከበብኩኝ፤ ልገደል ነው” የሚል የሃሰት መረጃ በማውጣት፤ ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ለመተግበር የሞከረውን ዕቅድ እንደፈለገ የሚነዳውንና ማሰብ የተሳነውን የቄሮ ኃይል በመጠቀም ለማስፈጸም ባደረገው ሙከራ እጅግ በርካቶች በግፍ … [Read more...] about ደም ጠጥቶ “አልጸጸትም” – የጃዋር አዲስ መጽሐፍ
“የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል” አለብን
አብርሆት የትውልዶችን ልቦና በእውቀት ለማብራት የተቋቋመ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሕንፃው ምሰሶዎች ጥበብ የሚለው ቃል በ18 የራሳቸው ፊደል ባላቸው ቋንቋዎች ተፅፎ የሚገኘውም ለዚህ ተልዕኮ ያለውን ቁርጠኝነት ለማመላከት ነው ብለዋል። አብርሆት ቤተመፃህፍት በብልሃት ክህሎት የተጎናፀፉ ወጣቶችን የማብቃት አላማውን በትጋት በመወጣት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ ዛሬ በአብርሆት ያገኘኋቸው ወጣቶች እንደ ሮቦቲክስ እና የፈጠራ ትግበራ ሥራዎች ላይ ተጠምደው ስላገኘኋቸው አድናቆት እና ማበረታቻ ይገባቸዋል ብለዋል። መጪው ትውልድ ከኢትዮጵያ የልማት ግቦች ጋር በተናበበ ሁኔታ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮዲንግ፣ በሳይበር ሴኩሪቲ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ክህሎታቸውን … [Read more...] about “የድህነት መጠሪያችንን በልጆቻችን መበቀል” አለብን
“ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ ነው” ከ190 ሀገራት 2ኛ የወጡት ተሸላሚዎች
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 ሀገራት በላይ የተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር በቅርቡ በግሪክ አቴንስ ታካሂዷል፡፡ 7 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ የፈርስት ግሎባል ቡድን በውድድሩ ተሳትፎ ከዓለም 2ኛ ደረጃ በመያዝ የብር ሜዳልያ ተሸልሟል፤ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ስሟን ማስጠራት ችሏል፡፡ ተማሪዎች የሳይንስ የቴክኖሎጂ የኢንጂነሪንግ እና የሂሳብ እውቀትን በመጠቀም ለአሁናዊ የዓለም ችግሮች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም መፍትሄ እንዲያመነጩ የተለያዩ እድሎች ይፈጠራሉ፡፡ እድሎችን በመጠቀም የራሳቸውን የቤተሰባቸውን የአከባቢያቸውን የሀገራቸውን እንዲሁም በዓለም ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ያፈላልጋሉ፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሶፎትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ ዳግማዊ ግሩም የቡድኑ መሪ ሲሆን ስለ ውድድሩ ሲናገር የዘንድሮው ውድድር ትኩረት የወደፊቷን ዓለም … [Read more...] about “ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ ነው” ከ190 ሀገራት 2ኛ የወጡት ተሸላሚዎች
የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን
"ዝምታ ነው መልሴ" ሲሉ ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ድምጻቸውን በቲውተር በኩል በዘፈን ምርጫ አጅበው ብቅ ያሉት ለስንብት ሁለት ቀናት ሲቀራቸው ነው። "የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው" ሲሉ የተቀኙት ፕሬዚዳንቷ "ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" በሚል ሐረግ መልዕክታቸውን አስረውታል። ይህኔ ነው "የኔታ መስፍን ወልደማርያምን ነብሳቸውን ይማረው" ሲሉ ፋይል ያገላበጡ ፕሬዚዳንቷ በኤክስ ይፋዊ ገጻቸው ላይ ላሰፈሩት ቅኔ ምላሽ የሰጡት። አንዳንዶች "ክብርት ሆይ ሕዝብም መንግሥትም መሆን አይቻልም" ሲሉ ቀልደውባቸዋል። ግልጹ፣ ያመኑበትን ለመናገር ወደኋላ የማይሉት፣ የአደባባዩ ምሑር ፕሮፌሰር መስፍን "ለሦስት መንግሥት ያገለገለች" ሲሉ በሎሌነት የመሰሏቸው የሳህለወርቅ ዘውዴን ሹመት በፍጹም እንደማይቀበሉት ተናግረው … [Read more...] about የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን
የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
ከበረሃ ውንብድና አገረ መንግሥትን ወደመምራት ሳያስበው የተቀበለው ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት በነጻ አውጪ ስም አንዲት ሉዓላዊት አገር ጠርንፎ በአናሳዎች በግፍ ሲገዛ የነበረው የወንበዴዎች ቡድን ጎራ ለይቶ በአደባባይ መካሰስ ከጀመረና ውዝግቡም እየተካረረ መጥቶ ትግራይን እንደ አፍጋኒስታን ወይም ኢራቅ በጦር አበጋዞች ከፋፍሎ ወደለየለት ደረጃ እየወሰዳት መሆኑ በቅርቡ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የቡድኑ መሪ የሆነው ደብረጽዮን እነ ጌታቸው የሚከሱኝ በፊትም ጦርነት ውስጥ ያስገባንና ሚሊዮኖችን ያስጨፈጨፈው ትህነግ ነው፤ አሁንም መልሶ ጦርነት ውስጥ ሊከተን ነው፤ ጦርነት ናፋቂ ነው እያሉ ነው፤ ነገር ግን ተጨፈጨፈ የተባለው ሕዝብ ማስረጃ የታለ? ባለተጨበጠና ባልተረጋገጠ፤ ማስረጃ በሌለው እኔን መክሰስ ብቻ ስለፈለጉ ባልሞተ ሕዝብ ይከስሱኛል በማለት … [Read more...] about የትግራይ አበጋዞች ሽኩቻ
አሜሪካ ኢሳያስንና ሻዕቢያን የማስወገድ ዓላማዋን ይፋ አድርጋለች
የሻዕቢያና የኢሳያስ አፈወርቂ ማብቂያቸው እየተቃረበ ይመስላል። ይህንኑ የሚያረጋግጡ ምልክቶች እዚያም እዚህም እየተሰሙ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር የመመለሷን ጉዳይ አጥብቀው በሚፈልጉ ጡነቸኞቹ አገራት ዘንድ አቋም የተያዘ ይመስላል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ፍጹም የማይፍለገውን ትህነግን እንደ ሕጻን አዝላ የኖረችው አሜሪካ አሁን ላይ ሁለቱም እንደ አመጣጣቸው እንዲሰናበቱ አቋም ስለመያዟ ከምልክት በላይ መረጃዎች እየወጡ ነው። ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ኢሳያስን፣ መለስን፣ ሙሴቪኒንና ካጋሜን አንድ ላይ "የአዲሱ ትውልድ መሪዎች" ብለው ለምስራቅ አፍሪቃ ሲያጩ በድጋፍ ስልጣን ላይ የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ካርዳቸው አልቋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ የገነባችው ኃይልና ዘመናዊ የውትድርና ቴክኖሎጂ ሻዕቢያን ለማስወገድ ከትህነግ በላይ አስተማማኝ በመሆኑ አሜሪካ ትህነግን መሽከም … [Read more...] about አሜሪካ ኢሳያስንና ሻዕቢያን የማስወገድ ዓላማዋን ይፋ አድርጋለች
በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ
በአዲስ አበበ ከተማ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ። የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት፦ 1ኛ. ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ 2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 3ኛ. ዮሴፍ ባቡ ሆራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 4ኛ. አቤኔዘር ቶሎሳ ሙሉ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 5ኛ. ለሚ ሲሌ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር እና 6ኛ. መቅደስ አረጋዊ ገንዘብ ተቀባይ የሆኑት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም በሙስና ወንጀል … [Read more...] about በአዲስ አበባ ገቢዎች የታክስ ኦዲት ባለሙያ ሌቦች ተያዙ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጣለበት ዕግድ ተነሳለት
በፓሪስ ኦሊምፒክ ዋዜማ የተቀሰቀው የእነ ኃይሌና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውዝግብ ወደ ሕግ ማምራቱ ይፋ ሲሆን “ቀድሞም ቢሆን መሆን የነበረበት ጉዳይ ይህ ነበር። አበጃችሁ” ሲሉ ጉዳይን በረጋ መንፈስ የሚከታተሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር። በሕግ ሕግን ማስከበርና፣ በሕግ መብትን ማስጠበቅ እንደሚቻል የሚያሳይ፣ ለሌላው ወገን ደግሞ በሕግ ራስን መከላከልና በሕግ መጠየቅ እንዳለ የሚያስተምር አግባብ እንደሆነ አመልክተው ነበር። ሻለቃ ኃይሌና አትሌት ገዛኸኝ አበራ የሚመሩትና ሁለት ፌዴሬሽኖች የተካተቱበት ወገን ዶክተር አሸብር የሚመሩትን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከስሰው ኮሚቴው የሚያንቀሳቅሳቸውን የባንክ ሂሳቦችና፣ የዕለት ተለት ክንውን ማካሄድ እንዳይችል አስወስነው የነበረው በሕግ በመሆኑ ዜናው ፍሞ ነበር። ጅማሮውን የትግላቸው ውጤት አድርገው ያቀረቡም ጥቂቶች … [Read more...] about የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተጣለበት ዕግድ ተነሳለት