ከደምቢዶሎ ከጠፉት 17 ተማሪዎች

° 14’ቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መሆናቸው

° 2 ተማሪዎች በግቢው ውስጥ መኖራቸው

° 2 ተማሪዎች ጎንደር እና ጎጃም ቤተሰቦቻቸው ጋር መመለሳቸው

° 10 ተማሪዎች በፍለጋ ላይ መሆናቸው

የተቀሩት ስማቸው እየተጠቀሱ ያሉት ተማሪዎች ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አይደሉም ተብሏል፡፡

በወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የተመራ የልዑካን ቡድን ከደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በስፍራው ውይይት እያካሄደ ነው፡፡ በስፍራው የሚገነኘው የኢቢሲ ሪፖርተር የመንግስት ቃል አቀባዩን አቶ ንጉሱ ጥላሁንን እና የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት አነጋግሯቸዋል፡፡

አቶ ንጉሱ ከዚህ ቀደም ሌሎች 21 ሰዎች ታግተው መለቀቃቸውን በድጋሚ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እየተሰጡ ያሉ የተዛቡ መረጃዎችንም በሂደት እያጠራን እንሄዳለን ብለዋል፡፡ የፍለጋውን ሂደት ዝርዝር መረጃዎች ግን ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ለጊዜው አንናገርም ብሏል መንግስት፡፡

(EBC/ጋዜጠኛ ታምራየሁ )

Speak Your Mind

*