የአማራ ብሔረተኝነት ለስር ነቀል ለውጥ መሰረት፣ ለኢትዮጵያም መዳኛ መድሃኒት ነው

የአማራን ህዝብ በቃላት መሸንገል የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል። የህዝቡ ንቃተ ህሊናው በስልጣን ላይ ከሚገኙት ከፓለቲከኞቹ ቀድሞ ሄዷል። ወጣቱ የነብር ጣቱ – እሳት ትውልድ ሆኗል።

ገና ከመነሻው ወያኔ/ትህነግ በ1967 ዓ.ም ባፀደቀው በማኒፌስቶው ላይ አማራ ጠላቴ ነው በማለት የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ የትግራይን ሪፕብሊክ እመሰርታለሁ፣ የአማራን ህዝብ ማህበራዊ ሰላም አሳጠዋለሁ ብሎ ሸፈተ። በርሃ ሳለ በአማራው ተወላጅ ላይ ከፍተኛ በደልና ወንጀል ሲፈጽም ከቅምየ በኋላ በተለት የአለም አቀፍና የሃገር ውስጥ ሁኔታዎች በደርግ መንግስት ላይ በፈጠሩት ጫና በለስ ቀንቶት የመንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በጥናትና በእቅድ በተጠናከረ ሁኔታ በአማራ ህዝብ ላይ የሙፈጽመውን በደልና ቀጠለበት።

ጫካ እያለ ያፀደቀውን ፀረ አማራ ፕሮግራሙን ለማታለያነት ከካናዳና ከሌሎች መንግስታት ህገመንግስታት ላይ የሚገኙ የሰብዓዊ መብቶች አንቀፆችን copy – paste አድርጎ  ህገመንግስት በማለት በራሱ ምክር ቤት በማፅደቅ የአማራን ህዝብ ሲገድል፣ ሲያፈናቅል፣ ሲያሰድድ፣ ያባቶቹን ርስት ሱቀማና የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ ሱፈጽምበት ቆይቷል። አሁንም ይህንን ፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ የወያኔ ህገ መንግስት ተግባራዊ ለማድረግ አዲሱ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በመሆኑም አዲሱ ጠ/ሚር በጎንደርና በባህር ዳር ላይ ያደረጉትን ንግግር የተመለከትን እንደሆነ በአማሩ ቃላቶች የአማራን ህዝብ ቁጣ ለማብረድና ትግሉ ላይ ውሃ ለመቸለስ የተነገሩ እንጂ ፍሬ ያለውና የአማራን ህዝብ ጥያቄ የሚመልስ ሆኖ አይታይም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አንድነትና ወንድማማችነት መስበክ ይገባቸው የነበረው ለሃገሩና ለህዝቧ አንድነትና ነፃነት ከጫፍ ጫፍ እየተወረወረ ደሙን ሲያፈስ ለኖረው ለአማራ ህዝብ በተለይም በዚህ በህወሃት የአገዛዝ ስርዓት ላለፋት 27 ዓመታት በጋራ ጠላትነት ተፈርጆ ነፍጠኛና ትምክህተኛ እየተባለ ሲገደልና ሲፈናቀል ለኖረውና ይህንኑ በትእግስት ላለፈው የአማራ ህዝብ ስለአንድነትና ወንድማማችነት መስበክ የሚገባቸው በፀረ አማራነትና በፀረ ኢትዮጵያዊነት ተሰልፎ ሃገር ሲያፈርስ፣ ህዝቦቿን ነገር እየሰራ እርስ በርስ ሲያባላ የኔረው፣ ኤርትራን ላስገነጠለ፣ መሬታችንን ለሱዳን እየቆረሰ ለሚሰጠው፣ በአጋዚ ጦሩና በፌዴራል ፓሊስ የህዝብን ደም ለሚያፈሰው ለትግራዩ የወንበዴ ድርጅትና ተከታዮቹ ወርቅ ናችሁ ማለት ሳይሆን ሃቁን መንገርና ማስተማር ነበረባቸው።

ሌላው ደግሞ የአማራን ህዝብ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል፣ በትግራይና በመሳሰሉት ክልሎች ሲገድሉና ሲያፈናቅሉ ለኖሩት እንደ ኦነግ፣ ኦህዴድ፣ ደህዴን፣ ህወሃትና ለመሳሰሉት በአማራ ጥላቻ ለተለከፋ ለጠባብ ጎጠኛ ድርጅቶች ስለ አንድነትና ወንድማማችነት ቡያስተምሩ በተሻለ ነበር።

እንደኔ እምነት የአማራው ችግር የሚፈታው በስብከት ወይም በመንገዳገድ ላይ ያለውን ወያኔን በጥገናዊ ለውጥ ማቆም ሳይሆን ጨቋኞችን እስከ ስርዓታቸው ጠራርጎ በሚጥል በስር ነቀል ለውጥ ብቻ ነው። ይህ ስር ነቀል ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በችግሩ ፈጣሪ በሆነው በወያኔ/ኢህአዴግ ሳይሆን በህዝብ ትግል ነው። ለዚህ ዘረኝነት ማክሸፊያው ደግሞ የአማራ ብሔርተኝነት ነው። የአማራ ብሔርተኝነት እንደ ወያኔ በአማራ ጥላቻና ለዝርፊያ የቆመ ወይም እንደ ኦነግ በተረት ተረት በተገነቡ በውሸት ሃውልቶች ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በማይናወጥ እውነት ላይ የቆመ  ወያኔዎች፣ ኦነጎችንና የእነሱ ተባባሪ የሆኑ ጠባብ ዘረኞች  በአማራው ህዝብ ላይ የከፈቱትን መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመመከት የሚደረግ የማንነትና የህልውና ትግል ነው።

የአማራ ብሔረተኝነት ለስር ነቀል ለውጥ መሰረት፣ ለኢትዮጵያም መዳኛ መድሃኒት ነው።

ደረ ተፈራ (derejepol@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Comments

 1. ” በጎንደር እና በባሕርዳር ከተሞች ለወያኔ ኢሕአዴጉ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀረቡት አቤቱታዎች ፥ አስተያየቶች እና ቡራኬዎች የነዚህ ከተሞች ኗሪዎች ብልህ ኣእምሮ የተመሰከረበት አጋጣሚ መሆኑን ታዝቤአለሁ።ባሕርዳር ከተማ የተደመጠው እማ ደግሞ እጅግ የበሰሉ ያስተሳሰብ እና የአቤቱታ አቀራረብ ምጥቀት የታየባቸው ሕሊናዎች ናቸው። አማራዎች ለ27 አመት በእንደዚያ ያለ ለመስማትም ለማየትም በሚዘገንን የጭካኔ ግፍ ተፈጽሞባቸው እያለ፤ ብሶታቸውንና ውስጣዊ ቁጣቸውን ተቆጣጥረው ሰብሰብ አድርገው በስሜት ሳይሸነፉ በሳላ ንግግሮችን እና ጥያቄዎችን ለወያኔው ጠ/ሚኒስትር አብይ ሲያቀርቡአድምጬአቸው የተሰማኝን አድናቆት በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል። እውነትም እነዚህ ዜጎች የጥንታውያን ገዳማት ፍሬዎች መሆናቸውን የሚያሳው አንደበተ ርቱእነታቸውና ያቀራረብ ስልታቸው ያስሰሙዋቸው ስሞታዎቻው በማራኪ ውብ ቃላት ተደግፈው ያለ ምንም መንገራገጭ ሰተት ብለው ወደ ጆሮ ሲገቡ ሄደውየሚለጠፉባቸው ዘጋቢ ግድግዳዎች በቀላሉ የሚደመጡ ለዝንተ ዓለም የማይረሱ ነበሩ። ያ ሁሉ ብሶት አስሰምተው ፥ ጠይቀው ካበቁም ቢሆን አብይ “አማራ አማራ”
  የምትሉት ነገር ትቼ…..የኢትዮጵያን ነገር እንዲህ እያንገበገባችሁ መልሳችሁ አማራ አማራ ስትሉ ታፈርሱታላችሁ!” የሚለውን አስቀያሚ ረገጣው ለኔ
  ከአስቀያሚም አስቀያሚ መልስ ነበር።
  አብይ እንደሚለው፤- “ኢትዮጵያ ውስጥ ስዞር የታዘብኩት ነገር የኢትዮጵያውያን የስሜት መራራቅ ይገርመኛል” ይላል።ለምን እንደገረመው ለኔ ግራ ገብቶኛል። የኢትዮጵያውያኖች በስሜትናበሃሳብ መራራቅ ማን ነው ምንጩ? እንዲህ እንዲራራቅ ማን ነው ተጠያቂው? አብይ መጀመሪያ ወደ ሥልጣን ሲወጣ ‘ይቅርታ ሲጠይቅ’ ታድያ መነሻው ምን ነበር? ድርጅቱ ስላላራቀን፤ስለገደለን አይደለም እንዴ ይቅርታ የጠየቀው? አብይ እንዲህ ይላል፤- “ያለው መራራቅ እንዴት ተደርጎ እንደሚሰበሰብ ይጨንቀኛል።” ይላል። ለዚህ ነበር እኛ ወያኔ ሲገባ ይህ የመራራቅ ስሜት የሚሰብክ ቡድን የኋላ ፥ የኋላ በሕዝቡ ላይ “መራራቅን ፥ የእርስ በርስ የጥላቻን ስሜት ስለሚያመጣ”መሰብሰቡ ሊያስቸግር ነው እና ካሁኑኑ ይህ ድርጅት አትቀላቀሉት፤ አስወግዱት፤ አውግዙት፤ አትከተሉት ስንል የነበረው። ግን እነ አብይ ሊሰሙን አልቻሉም እና “ወያኔን” አድንቀው የወያኔ ወታደሮች ሆኑ! ዘለግ ሲልም የስለላው መ/ቤት አዋቃሪ ሆነ ፥ ከዚያም “የወያኔዎች አሽከር” የሆነውን የጥላቻ ፥ የመራራቅና የግድያ ድርጅት መሪ የሆነውን “ኦሆዴድን” ተቀላቅሎ የዚህ ድርጅት መሪ ሆነ። አሁን ሥልጣን ላይ ሲወጣ፤ ሕዝቡ በመረረው ሰዓት መጥቶ የሕዝቡን መራራቅ እየዞረ ሲመከት “ያለው መራራቅ እንዴት ተደርጎ እንደሚሰበሰብ ይጨንቀኛል” ይላል። አንቺ ያመጣሺው አንቺው ፍቺው! ሕዝቡ በመረረው ጣራ ላይ ስለመጣህ ምሬቱ ከመጠን በላይ ነው እና አንተንም ማስጨነቁ አልገረመኝም። አንዱን ያዝ፤ ጨክነህ ወያኔዎችን እና ስርዓታቸውን አፍርስ፤የጎሳ ክልሎችን እንዲፈርሱ አደርግ (ተከራከር) (እነ ለማ መገርሳ እና የሮሞ ጤነኛ ክፍሎችን እንዲሁም ሌሎችን አስተባብረህ ግብህን ምራ) አልፈታውም ስትል ግን “ፈቺዎች ይመጡና” በወንጀል ትከሰሳለህ ወይንም ከተገንጣዮች ጋር ትወግናለህ። ብዙዎቹ እንዲዚያ ነው ያደረጉት። አግልግለው አገልግለው፤ ወንጀሉ ወደ እነሱ ሲያዘነብል ወደ ውጭ እየሸሹ “ኦነግን” ወይንም “ኦብነግን” ይቀላቀላሉ። እነ ጁነዲን ሳዶ እና መሰል የኦሮሞ ወንጀለኞች እያደረጉት ያሉ ይህንን ነው። እነዚህ ድርጅቶች ደግሞ ማንም ግሳንግስ ወንጀለኛን ሁሉ የሚጠራቀምበት ነው (አውጭ አገር ያሉት ተቃዋሚ ተብየ ድረገጾች ፥ ራዲዮኖች እና ቲቪ ሚዲያዎች ሳይቀሩ እነ ጅነዲን ሳዶዎችን ከማጋለጥ ይልቅ እንግዶች እያደረገ ይክባቸዋል) ። አትገባም ማለት የለም። ብዙዎቹ ተገንጣዮች የወንጀል ድርጅቶች ስለሆኑ፤ ተባባሪን ይፈልጋሉ። የሚገርም ነው። ይላል እና ሥልጣን የወጣበት መንገድም “ይህች ሰላማዊ የሥልጣን ሽገግር” ይላታል። አገር የሚያፈርስ ሥርዓት “በሕገመንግሥቱ” ተደንግጎ ያውም እንዳንደመር ፥አንድ እንዳንሆን ፥ ደደቢት በረሃ ውስጥ ተጽፎ፤ በወንጀለኛው ኦነግ ሊጥ “አቡኪነት” ተጋግሮ የተደነገገው ከፋፋይ በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ላይ የዘመተ የስደብ ውርጅብኝ የሰነዘረ ፥ የናዚዎች ሕገ መንግሥትን ከሃይለማርያም ደሳለኝ እጅ ተረክቦ ሰግዶ “መርዘኘውን መጽሐፉ” ለሕዝብ እያሳየ ፥ ተለያይተን መቆየታችንን እራሱም ጭምር ያስገረመው መራራቅን እንደገና “መራራቅን” የሚሰብከው መርዘኛውን መጽሐፍ በአክብሮት ተቀብሎ “እፈጽማለሁ” ሲል ምን እንበለው? ለዚህ ደግሞ “ሠላማዊ” የሥልጣን ሽግግር ይለዋል። አልገረማችሁም?አንድ መሪ ወደ ሌላ ስርዓት ሲሸጋገር ሌላ ሕገመንግሥት ይጽፋል እንጂ“ ያንኑአከብራለሁ” ብሎ እጅ ነሥቶ ይሰግዳል? የአብይ ሥልጣን ሽግግር ትርጉም ምንይሆን? የሚገርመው ደግሞ ‘ከኛ የተለየ ሃሳብ ካላችሁ ወይንም ማንም ሰው ካለው እናንተም እኛም ሃሳባችን እናቅርብና አንከራከር….” ይላል። እኛ የሚለው ወያኔ እና እሱ የወከለው ደርጅት ማለት ነው። በሌላ አነጋጋር “ኢሕአዴግ” የሚባለውን ፋሺስቶች ጥርቅም ድርጅትን ነው “እኛ” እያለ ያለው። ለዚህም “ሠላማዊ ሽግግር” እያለ ይቀልድብናል። አንድ ልትዘነጉልኝ የማልፈልገው ነግረ አለ። አብይ ከውስጡ ኢትዮጵያዊነትን ለማንሰራራት ፍላጎት አለው ወይ ? ብትሉኝ በሚገባ ከሌሎቹ የትግሬ እና የሶማሊ ፋሺሰት መሪዎች በበለጠ በጣም በራቀ ስሜት አውንተኛ ስሜት አንዳለው አልክደውም። ግን ከማን ጋር ሆኖ ነው ይህንን ሊያጎለብተው የሚችለው የሚለው ጥያቄ ነው የሚያከራክረን። እሱም ዓላማው ግልጽ ማድረግ አለበት። ለለውጥ ነወ የመጣው “መሠረታዊ የሆኑ” ለውጦች አስቸኳይ እንዲታዩ ያድርግ። ደጋፊ አለው፤ ተባበሪዎች አሉት ፥ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዘዎቹን ንግግረሮቹ ለገበያ ቀርበው ተወድደውለታል ፥ ስለዚህ ወያኔን የሚፈራበት ምን መንገድ አለ? ሕዝብ ከጎኑ ቆሟል! ምን ይጠብቃል? “ቀስ በሉ ዝግ በሉ” መልካም መልካሙን እንነጋገር…..” ምን ማለት ነው?
  (አማራ አማራ የሚለውን ብሶት) እሱ <>
  ሲል ብሶት የባሰውን ሕዝብ ወደ ውስጡ እንዲመለከት መክሯል። እንግዲህ ወደ ውስጥ እንዲመለከት ማለት ወደ ልባችሁ ተመለሱ ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች ከልባቸው ወጭ አልሄዱም።በነገዳችን ስማችን እየተጠቀሰ “አማራ አንተ ሽንታም ፤ገና እናሳያሃለን”እያሉ ትግሬ ገራፊዎች የወንዶችን ብልት እየቀጠቀጡ እንዳይወልድ አኮላሽተውታል፡ ሴት እህቶቻችን አማራ ስለሆኑ እርቃናቸው ወጥተው አንዲገረፉና አንዲዋረዱ ተደርጓል፡ ይህ ይቁም ነው እያሉ ያሉት። መልካም መልካሙን ከየት ተከስቶ ነው፤ሕዝቡ ወደ ውስጣችሁ እዩ፤ መልካም መልካሙን እንነጋር የሚለው? ከልባቸው ውጭ ቢሆኑ ኖሮ አበሮ የተቀመጠው አለምነው መኮንን እና፤ ደመቀ መኮንን እንዲሁም የመሳሰሉ አድር ባዩ እና ወንጀለኛው ብእዴን መሪዎችን በጥይት ይፈጃቸው ነበር።የሰደቡትንም እሺ ብሎተቀብሎአቸው፤ ብሶት የባሰውን አንጀቱን ተቆጣቀጥሮ አዳራሽ ውስጥ ተገቢውን ጥያቄና ብሶት ነው ያስተጋባው። “ወደ ውስጣችሁ እንድታዩ” ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም። አኖሌ ሃውልት አፍርሰው ማለት “ስሜታቸውን እንዲያረግቡ” መምከር አልገባኝም። እንዲህም ይላል፦ የሚለው ንግግሩ አሁንም ገርሞኛል። እርግጣ ነው ያስመሰግናል፤ ግን ሙሉውን ስዕል ይገልጸዋል ወይ? ለመሆኑ በምን መመዘኛ ነው አሁን የተፈቱ ጥቂት ሰዎችን በሺዎቹ በየእስር ቤቱ ታጉተረው እየተገረፉ ያሉትን መለኪያ የሚሆነው?አንዲት ቀንም ቢሆን እዛ ውስጥ መታጎር የሌላቸውን ሁሉ አሉ። አገሪቱ የምትፈልጋቸው እናያስተማረቻቸው የታወቁ የልብ ጥገና ዶክተሮችን ሁሉ አፍኖ እስር ቤት የሚጥልን ሰርዓት እንዴት ነው አብይ ይህንን ጥቂቶች የመፍታትን መመዘኛ የሚያደርገው? ጥቂቶችን መፍታት ያራከሰ የለም፡ ግን ተፈቺ እስረኞች በተፈቱ በማግስቱ እያታፈኑ ወደ እሰር የሚወረውራቸውን “የጎስታፖ” ቡድን አብይ በምን ይገልጸዋል? ተፈትተው ወደ ውጭ ለሥራ ጉዳይ ለሚንቀሳቀሱ ፓስፖርታቸው በቦሌ አየር ማረፊያ አንዲታገድ ማድረግ ምን እሚሉት ነፃነት ነው? በኛ እና በአብይ ያለው ልዩነት እኛ ሥርዓቱን የምንተረጉመው “ፋሺስት፡ ነው እንላለን፡ እሱ ደግሞ ጥቂት ሰዎች ፈትተናል እና ዲሞክራት ነን እያለን ነው። ለዚህ ምን እንበል?
  አማራ ተበድሏል፤ የዱር ባሕር ዛፍ ደናችን ተዘርፎ እኛ ተከልክለን፤ ወደ ትግሬ እየተጫነ ነው፡እና አማራ በመሆናችን ተጠቅተናል ፥ አገር ያቀናውን አማራ “ነፍጠኛ” መለያ ስም ተለጥፎበት ለጥቃት ተጋልጠናል ብሎ ላለ ሆድ ለባሰው አቤት ባይ። እንዲህ ሲል መልስ ይሰጣል። “አማራ አማራ የተባለውን ትቼ፤ ለሁላችን ፍትሕ ያስፈልገናል፤ዲሞክራሲ ያስፈልገናል፤ኢትዮጵያውያን በሕግ የምንዳኝበት ሥርዓት የሚል ከሆነ እቀበላለሁ። “የኛ ብቻ” የሚል እንዳይሆን። ”>> እነዚህ ሰዎች እውድየውም ላይ በግልጽ እየተናገሩ እንደተደመጡት “ከማንም ዜጋ እኩል እንድንታይ” ፍትሕ ይሰጠን ነበር ያሉት እንጂ “የኛ ብቻ” ብለው ሲሉ የተደመጡበት አንዲት ዓረፍተ ነገር አልተሰማም። ለኛ ብቻ አንዳይሆን፤አማራ አማራ የሚለውን…… ብሎ ማሳነስ ፡ጠባብ አመለካከት ሆኖ መተርጎም “መነሻው” ምንድ ነው? ይላል አብይ። ካለ ብቻ ሳይሆነ “አለ”። እንዲህ ማለትም ጥሩ ነው። ግን እነሱም የሚሉት እኮ የጠፋ ብቻ ሳይሆን አንተ ያቆምከውን ፥ የፈረምክብት ፥ ፎቶግራፍ የተነሳህበትን ዛሬም ህያው ሆኖ ለጥፋት ቆሞ ያለውን የጥላቻ ሃውልት “አኖሌ” እና በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ከተሞቹና ገጠሮች የቆሙ በርካታ የጥላቻ ሃውልቶች ይፍረሱ ከዚያ ይቅር ይቅር እንባባል፡ ካልሆነ ሃውልቶቹ ቆሞው እንዴት “የይቅር ይቅር የቃላት ሽምገላ እንቀበል” ነው እያሉ ያሉት። ይህ ትከክለኛ አባባል ነው! ለጠቅ ብሎም ፤<“ከእነ ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎች ጓዶች ጋር ተረባርበን መልካም ነገር ማምጣት እንችላለን”ይላል። እነ ገዱ እና ጓዶቹ የጥፋት ምንጮች እና በአማራ ላይ ብትር ሲወርድ ምንም ያላደረጉ የውም
  አማራውን መልሰው ሲዘልፉት የነበሩ የወያኔ አሽከተሮች ናቸው እና ከላይ እስከ ታች ያሉትን በሕዝባዊ አስተዳዳሪዎች ይተኩልን እያሉ ነበርሲጠይቁት የነበሩት። ከነ አለምነው መኮነን እና ደመቀ መኮንን ፤ከነ በረከት ስምኦን እና የደቡቡ ሰው አዲሱ ለገሰ…..ትብብር እንዴት ተብሎ መልካም ነገር ሊመጣ ይችላል። 27 አመት የችግሩ ምንጮች እነዚህ ነበሩ። አሁን ድግሞ አብይ ‘እነሱ ጋር ተባብረን መልካም ነገር ማምጣት ይቻላል” ይላል። ይልቁኑ የሕዝቡን ጥያቄ በተገቢው አስተናግድ እና ስምህን አሳድስ እንጂ በነበረው ቦይ እየተጓዝክ “እኛ” ኢሕአዴጎች የሚለው የሸተተ ግም ነገር ለ27 አመት አፍንጫችንን ሲያስከፋ ስለነበር “እኛ ኢሕአዴጎች” የሚለው ዳግም ልንሰማው ኣንፈልግም!።(በሳል ትችት ነው በለው!)
  አመሰግናለሁ – ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

Speak Your Mind

*