ፕሮግራም አልባ “የሕዝብ አደራ” ተሸካሚዎች

ባላፈው ሳምንት “ከዘቀጥንበት ወጥተን እንዴት ወደ ፊት እንራመድ?” በሚል ርዕስ ያቀረብኩት ጽሁፍ በተለያዩ የሚዲያ ገጾች ላይ ከታተመ በኋላ፣ በቅርጽ የተለያዩ በይዘት ግን የሚመሳሰሉ ብዙ አስተያየቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ደርሰውኝ ይዘታቸውን ከገመገምኩ በኋላ ያነሳሁት ጉዳይ ተጨማሪ ትኩረት የሚያስፈልገው መስሎ ስለታየኝ ይህንን ተከታይ ጽሁፍ ለማሳተም ወሰንኩ። በዚህ ጽሁፌ ሁለት ቁም ነገሮችን ማለትም “ሕዝባዊ አደራና” “የፖሊቲካ ድርጅቶች ፕሮግራም ግልጽ አለመሆንን” በተመለከተ አንዳንድ አስተያየት ሰጥቼ ሌሎችም የየበኩላቸውን አንዲያዋጡ ለመጋበዝ እሻለሁ። የኔ ሃሳብ ብቻ ትክክል ነው ከሚለው ፊውዳላዊና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ተላቅቀን በየበኩላችን የሚሠማንን ወደ ውይይት መድረኩ ካመጣን አንድ ታላቅ ታሪካዊ እርምጃ የወሰድን መሆኑን አውቀን ሁላችንም እንድንካፈልበት ከወዲሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

“ሕዝባዊ አደራ”

ያገራችን የፖሊቲካ ድርጅቶች የተቋቋሙት በማህበረሰቡ ውስጥ የተሻለ ንቃት ባላቸው ጥቂት ግለሰቦች ስብስብ መሆኑ እሙን ነው። በመላው ዓለም ያለው ልምድም ከዚህ የተለየ ስላልሆነ ድርጊቱ ብዙም አያሳስብም። ሕዝቡ መድረክ ወይም አቅም ከማጣት የተነሳ ለየብቻው ሆኖ በየቤቱ የሚያጉረመረምበትን ጉዳይ በአደባባይ ይዞ ለመቅረብ የነቁ የማሕበረሰቡ አካላት ተሰባስበው ድርጅት ማቋቋም ለሕዝብ ከመቆርቆር የመነጨ የዜግነት ግዴታ ነውና። የኛን የፖሊቲካ ድርጅቶች ልዩ የሚያደርጋቸው ግን በጓደኝነት ተሰባስበው ድርጅቱን ከመፍጠርና በጣም መሠረታዊ የሆነ የመህ መግለጫ ፕሮግራም ገና ከመጀመርያው ለሕዝብ በአደባባይ ከማሰማታቸው ባሻገር ያገሪቷን ማህበረሰባዊና ኤኮኖሚያዊ ችግር ሥልጣን ላይ ካለውና ከሚቃወሙት መንግሥት በተሻለ መንገድ እንዴት አድርገው እንደሚቀርፉት የሚይሳይ አንዳችም ፍኖተ ካርታ ለሕዝብ አለማቅረባቸው ነው። አንድ ሁላቸውም በድፍረት የሚናገሩት፣ ግን ደግሞ አሳሳች የሆነው፣ ይህ “ህዝባችን አደራ ሰጥቶናል” “ሕዝባችንን እንወክላለን” የሚሉት ፖሊቲካዊ ቅጥፈት ነው።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣአቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Comments

  1. After so many years, this is by far the most genuine and practical analysis of the current political climate in Ethiopia. These ideas are very necessary to help solve our political objectives. Finally, i would like to correct your use of the word “mekerfe”. This word belongs to Weyane.

Speak Your Mind

*