ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ይገናኛሉ

ሐሙስ ዕለት የአሜሪካ ጉብኝታቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ነገ (አርብ) እንደሚገናኙ ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ያገኘው መረጃ ጠቁሟል።

ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት ማክሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ወይም ሰኞ ይዘልቃል ተብሎ ታስቦ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጉብኝት ባጭር ቀናት እንደሚጠናቀቅ ከተሰማ ወዲህ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወገኖች ቀናቱ እንዲረዝሙ ብዙ ሲጥሩ ቆይተው ነበር። በተለይ የጠ/ሚ/ሩ ጉብኝት ዋናው ዕቅድ ከኢትዮጵያውያን ጋር መገናኘት ነው ተብሎ ከአገር ቤት ከተነገረ ወዲህ እነዚሁ ወገኖች ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መገናኘት አለባቸው በሚል ሲጥሩ ቆይተው ነበር።

የጠ/ሚ/ር ዐቢይ ጉብኝት ከኢትዮጵያውያን ጋር ብቻ ከሆነና በዚህ የመጀመሪያ በሆነው ጉብኝት ከትራምፕ አስተዳደር ሹሞች፤ ከመከላከያና ከውጭ ጉዳይ መ/ቤት ባለሥልጣናት ጋር ሳይገናኙ ከሄዱ ሊፈጠር የሚችለውን የዲፕሎማሲ ክስረት የተገነዘቡ ወገኖች በርካታ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ባለፉት አስተዳደሮች “ነጭ ወያኔ” ደጋፊዎች የነበሩት ህወሓት አሁንም የእነዚህን “ወዳጆቹን” ሥልጣን በመጠቀም ዶ/ር ዐቢይ የአሜሪካ ወዳጅ አይደሉም የሚለውን ስም በማሰጠት ለማጠልሸት የፈለገው ሙከራ እንደፈለገው እንዳልተሳካ የመረጃው ባለቤቶች ገልጸዋል። እንዲያውም ይህ በኤምባሲ በኩል መጠናቀቅ የሚገባው ጉዳይ በተገቢው ሁኔታ አለመሠራቱ፤ ጠ/ሚ/ሩ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጀምሮ በተዋረድ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ፖለቲከኞችን እንዲያገኙ አለመደረጉ አሁንም ሥርነቀል ለውጥ በኤምባሲዎቻችን ውስጥ እስካልተደረገ ድረስ በጠ/ሚ/ር ዐቢይ የውጭ ፖሊሲ ላይ ትልቅ ጋሬጣ ይሆናል የሚል አስተያየት ተሰጥቶበታል።

በሰብዓዊ መብቶች ረገጣና መሰል ጉዳዮች ስማቸው ብዙም ያላማረውን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ከሚያገኙ ይልቅ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስን ጋር ውይይት ማድረጋቸው የተሻለ ነው የሚሉ ወገኖች፤ ሚ/ር ፔንስ የኋይት ሐውስን ፖለቲካ በመዘወር ከበስተጀርባ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ።

“አሸባሪነትን መዋጋት” በሚል ሽፋን የአሜሪካ ወዳጅ ነኝ ሲል ለቆየው ህወሓትና “ነጭ ወያኔዎች” ይህ የዶ/ር ዐቢይና የሚ/ር ፔንስ ግንኙነት ከዲፕሎማሲ አኳያ የመጀመሪያው ሽንፈቱ ሊወሰድ እንደሚችል የመረጃው ባለቤቶች ያስረዳሉ። ጠ/ሚ/ር ዐቢይም በዚህ ውይይት ባለፉት አራት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት በማስረዳት በአሜሪካ በኩል (በተለይ “የቀን ጅቦቹ”ን በተመለከተ) ሊያገኙ የሚችሉትን ድጋፍ የሚወያዩበትን መድረክ እንደሚከፍትላቸው ከወዲሁ ተጠቁሟል። (ፎቶ፤ ከኢንተርኔት የተገኘ፤ በጎልጉል የተቀናበረ)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።

Comments

 1. In my opinion, within this short period of time, this is extra ordinary achievement, with full of hope, bright future, and oneness journey, to make Ethiopia greater, for better understanding, and development. In Amharic there is a saying, “Yameytgib Injera kemetedu yestaweqle.” Fearful thoughts should be abolished, it is a good beginning and should be proceeded without any wavering. At the end, all the efforts will not be for personal fame, it will be to make Ethiopia on top of a map, to eradicate poverty, and for a better place to live peacefully, and in harmony for all without any discrepancies. Present and future generations should be honorable, hard workers, and responsible to be proud citizens. To insult one another is not acceptable and not in the blood of Ethiopians. I appreciated the opportunity.

 2. I said it before, I will say it in the future, Ethiopia has a big place in my mind. In short:
  My Birth Land, Ethiopia
  On high plateau
  On ragged mountain
  Surrounded by hills and valley
  You are scalded by your droughts

  Through no fault of yours
  All your beauty covered with swift dust
  Your hospitality changed
  To second degree begging bread for the hungry

  You raised me with milk and honey
  Something went wrong
  Can you tell me?

  Your journey to Democracy a priceless effort
  You a mother of burnet face
  Call them to change your nick-names
  I know you will be blessed again
  Now and then always my country

  Yeshi Gemaneh

 3. Back in my years, we never knew division by tribes, we all were speaking one language, and one aim that was one Ethiopia. Again, the slogan should be “One Ethiopia” let the new generation learn this language of oneness and all work and think for the people at large, and for development of that beautiful one Ethiopia. Educators should work hard to abolish the hatred messages, and draw pictures of love and respect of one another. That can be happen when there is love, peacefulness, and trust in God. All should think for their country without any discrepancies to make and, with full heartedness pull that country out of poverty.

Speak Your Mind

*