…ቅምሻ…

በቀረችው ትንፋሽ … አገሩን አስታሞ …
እሱም እንደ ሌሎች … ሊያሸልብ ነው ደግሞ!
………………………………………………….
እንደ ሸረሪት ድር … ነገር ተወሳስቦ…
እውነትን ማን ያውጣት … ከመሃከል ስቦ…?
…………………………………………………
አገር ተሰቃየች…ጣሯ ብቻ በዛ..
ግማሹ እየሸጣት…ግማሹ እየገዛ…!
…………………………………………………
የሰው ዘር መገኛ … ብለው ሲጎበኙን…
በብሄር ተጠምደን … ተከፋፍለን አዩን::
…………………………………………………
ማን እንደዘረፈኝ … ልቤ እያስተዋለ
የለመደው አፌ … ”የመንግስት ያለህ!” አለ::
………………………………………………….
ሳምሶን ጌትነት

Comments

  1. ዓለሙ ይስማው says:

    እንትፍ…ትፍትፍትፍ… ይበል…ይበል… ብዕር ይባርክ!

Speak Your Mind

*