“የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ አለበት” የሐዋሳ ነዋሪ

ኤጄቶ ሁከት የሚያስነሳው ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ነው

አንድ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ አሁን በስልክ የነገረኝን ላካፍላችሁ። እሱ በሚኖርበት አከባቢ የተወሰኑ የሲዳማ ወጣቶች አንድ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች መስሪያ ድርጅትን በእሳት ለማቃጠል ጥረት ያደርጋሉ። ነገር ግን የአከባቢው ማኅብረሰብ ተሯሩጦ ድርጊቱን ለመከላከል ይሞክራሉ። በዚህ መሃል የደቡብ ክልል ፖሊሶች በፓትሮል መኪና ከቦታው ይደርሳሉ። በድርጊቱ የተሳተፉ ወጣቶችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፈፅሞ አልሞከሩም። ከዚያ ይልቅ በዚህ የወንጀል ተግባር የተሰማሩትን ወጣቶች ከአከባቢው በቶሎ እንዲሸሹ በምልክት ይነግሯቸዋል። ወጣቶቹም መንገድ ለመዝጋት የደረደሩትን ድንጋይ እያነሱ ወደ ሌላ ቦታ ሄዱ። በኋላ ላይ የሌላ ምስኪን ነዋሪን ሃብትና ንብረት በእሳት ያወድማሉ። በአጠቃላይ ሐዋሳ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ የሚቀሰቀሰው ከክልሉ ፖሊሲ አቅምና ቁጥጥር በላይ ሆኖ አይደለም። ከዚያ ይልቅ ከፖሊሶች ጋር በመቀናጀትና በመተባበር ነው። ስለዚህ የሐዋሳና አከባቢውን ሕዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስከበር ሲባል በአከባቢው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ አለበት። በዚህም የክልሉ ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ወይም የፌደራል ፖሊስ ዕዝ ስር መግባት አለበት።

©የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ – @ThinkAbyssinia

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Speak Your Mind

*